አዶናይ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


ኢየሱስን ልበሱት

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


ሀያላን መፀለያቹን አታቋርጡ ዝም ብላቹ ያለ ምክንያት ፀልዩ 🔥


አንድ ነገር ልበላቹ...

ሃያላን ሃያላን እረ አቤት በሉኝ ሃያላን እሺ ሃያል🧒 ሃያል ነሽ👩‍🦰 አቤት ኤርሚ የሚለኝ ሰዉ ይጥፋ... ወይ የዘንድሮ ልጆች😀🥰 እሺ ወደ ቁም ነገሩ ልግባ🏃ቁም ነገሩ ቆይ ቁም ነገሩ ምን ነበር አያቹ የናንተ ነገር አስጠፋቹኝ ቲሽ 🙆... ምን ነበር 🤔 ቆይ ምንነበር ልላቹ ያሰብኩት 🤔 አዎ አስታወስኩት ስለ ወጣቱ ዮሴፍ ላወራቹ ነበር ትዝ ይላቿል ዮሴፍ በጴጢፋራ ሚስት የተፈተነውን ፈተና ? የጴጢፋራ ሚስት ዮሴፍን " ና አብረን እንተኛ " ስትለው እርሱ ግን እግዚአብሔርን ፈርቶ እንቢ ስላላት ብቻ በሀሰት ከሳው እስር ቤት አስገባችው፤ ቆይ ግን ነገሩን እሺ ብሎ ቢያደርገው ኖሮ ምን ይፈጠር ነበር ? ቢያደርገውማ ኖሮ በተቃራኒው ጥሩ የሚባል ህይወት እንዲኖር ታደርገዋለች ነገር ግን ይሄ ለዮሴፍ ምን ያደርግለታል እግዚአብሔር ካዘጋጀለት ንግስና የሚያስቀረው ከሆነ፤ ወዳጆቼ ሰይጣን በኃጢአት የሚፈትናቹ የታየላቹን ክብር ሊያስጥላቹ አስቦ እንደሆነ አትርሱ ፣ ሰይጣን እግዚአብሔር ለእኛ የያዘውን መልካሙን ሀሳብ ሊያስቀይር አይችልም ነገር ግን እኛን በኃጢአት ይዞ ያንን ሀሳብ እንዳንፈፅም ማድረግ ይችላል ፤ ለዚህም ነው እግዚአብሔር ከሀሳቡ እንዳንጠፋበትና ያየልንን ክብር እንድናየው ስለሚፈልግ አስር ጊዜ ተቀደሱ የሚለን።

ውዶቼ እናንተ ብቻ እንደ ዮሴፍ ኃጢአትን እንቢ በሉለት እንጂ እግዚአብሔር እናንተ ከእስር ቤት አውቶ ንጉስ ማድረግ አይከብደውም።

@thedayofPentecost
@thedayofPentecos
t


እግዚአብሔር ዝም ሲል 😢

አስተውላቹ ከሆነ እግዚአብሔር ዝም ሲል ተናጋሪ ይበዛል ኢዮብ ትዝ ይላቿል ምንም በማያውቀው ጉዳይ ምክንያት ያለው ንብረት ሁሉ አንድ በአንድ ሲጠፋበት፣ የገዛ ሚስቱ እንኳን ስትክደው ፣ ሰውነቱም በገል ብረት ሲቆሳስል እግዚአብሔር ግን በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ዝም ሲለው ነበር ፤ ነገር ግን ኃላ ላይ እግዚአብሔር በኢዮብ ላይ የነበረውን ሀሳብ ሲጨርስ በታላቅ ክብርና በብዙ ደስታ እንደ ገና እንዳሰበው መጽሐፍ ይነግረናል። የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች የእግዚአብሔር ድምጽ በጣም አስፈልጓቹ ድምጹን ግን ሳትሰሙት ስትቀሩ እግዚአብሔር በህይወታቹ ላይ እናንተ ሳታውቁ የሆነ ትልቅ ስራ እየሰራ እንደሆነ አስቡ፤ አንዳንዴ ደግሞ በእግዚአብሔር ዝም ውስጥ እናንተ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ልታልፉ ትችላላቹ ነገር ግን ከብዙ ዝምታዎች በኋላ የሚመጣውን የእግዚአብሔርን ድምፅ ስትሰሙ የቀድሞ ዝምታው ለምን እንደነበር ይገባቿል።

ዝምታው ውስጥ ክብር አለ 🔥

@thedayofPentecost
@thedayofPentecos
t

3k 0 48 1 75

አጉል ስሜታዊነት ☛ በ R/Ship ህይወት ውስጥ

ሁሉም ሰው ማለት በሚቻል መልኩ R/Ship ለመጀመር እንደ ትልቅ መስፈር የሚወስደው በአይን የሚታየውን ነገር ነው አብዛኛውን ጊዜ የሰውነት መልክ ፣ የሀብት ደረጃ እና አለባበስን ሰዎች እንደ መስፈርት ያዮቸዋል አነኚን ነገሮች አይተው የፍቅር ግንኙነታቸውን የሚጀምሩ ሰዎች ደግሞ ለስሜታዊነት ቅርብ ይሆናሉ በዚህም ምክንያት የ R/Ship ህይወታቸው ከሁለት እና ከሶስት ወር በላይ የመዝለቅ አቅም አይኖረውም ምክንያቱም ቀድሞም ቢሆን ግንኙነቱ ከእውነተኛ ፍቅር ይልቅ ለስሜታዊነት ቅርብ ስለነበር፤ የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች የፍቅር ግንኙነት ከስሜትና ከጊዜያዊ ፍላጎት ያለፈ ትርጉም እንዳለው ልነገራቹ ፈልጋለው ከምንም በላይ ደግሞ ትዳር ወደሚባለው ወደ እግዚአብሔር ሃሳብ የሚወስደን መንገድም ጭምር ነው፤ ስለዚህ ነገ ላይ " ምነው እንዲ ባላረኩ " የምትሉበትን ውሳኔ እንድቶስኑ ከሚያደርጋቹ በጊዜው ከሚመጣ አጉል ስሜታዊነት ይልቅ የእግዚአብሔር ሃሳብ ያለበትን ትክክለኛ የሆነውን ህይወት እንድትመርጡ መክራቿለው።

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost


አባት ሆይ እስከ ዛሬ የጠየቋቸውን ጥያቄዎቼን ሁሉ ተዋቸውና ይሄን ጥያቄዬን ብቻ መልስልኝ.. “እባክህ፤ ክብርህን አሳየኝ”😭😭 ክብርህን ብቻ😭😭
— ዘጸአት 33፥18

2.2k 0 24 16 121

ይሄን puzzle Game ተጫውታቹ ታውቃላቹ ?

ዛሬ አንድ ህይወቴ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣውን የመንፈን ቅዱስን ትምህርት ላካፍላቹ..ይሄ ከላይ የምትመለከቱት የምስል ጨዋታ Puzzle Game ይባላል ጫወታውን ከመጀመራቹ በፊት ፐዝሎቹን ገጣጥማቹ ምን አይነት ምስል ማምጣት እንዳለባቹ ታያላቹ ከዛም እንደምታዩት ብዙ puzzle ይሰጣቹና የአንድ ሰው ምስል ስሩ ትባላላቹ እናንተም አንድ በአንድ የሰውነቱን ክፍል እየፈለጋቹ አይኑን በአይን በቦታው ላይ አፍንጫውንም በአፍንጫው ቦታ ላይ እያረጋቹ ትክክለኛውን ምስል ለማምጣት ትሞክራላቹ አንዳንዴ ግን ተሳስታቹ ቅንድቦቹን በጺም ቦታ ላይ ልታደርጓቸው ትችላላቹ እንዲህ ከሆነባቹ ደግሞ ትክክለኛው ምስል ስለማይመጣላቹ የግድ አፍርሳቹ ማስተካከል ይኖርባቿል አሁን ነገርዬውን ወደኛው ህይወት ላምጣው የተወደዳቹ ልክ እንደ ምስሉ እኛም ብዙ የህይወት ፐዝሎች አሉን ነገር ግን የእኛን የህይወት ፐዝሎቹ እየገጣጠመ ትክክለኛውን የእኛነታችንን ምስል የሚያመጣው አላማችንን የሚያውቀው እግዚአብሔር ነው፤ ትምህርት ፣ ስራ ፣ ትዳር ፣ ልጅ ፣ አገልግሎት ፣ ጥቂቶቹ የህይወት ፐዝሎቻችን መካከል ናቸው፤ እነዚን ፐዝሎች እግዚአብሔር ለእኛ ቢሰጠን ኖሮ ደስ ባለንና እንደሚመቸኝ አድርገን በገጣጠምነው ነበር ለምሳሌ ትዳሩን ከስራ በፊት እናደርግና አንዱን ጥለን ደስ ያለንን እንጨምር ነበር ነገር ግን እግዚአብሔር ትክክለኛ ማንነታችንን እኛ እንድንሰራው አሳልፎ አልሰጠንም፤ ስለዚህ የተወደዳቹ ትክክለኛው ምስላቹ በእግዚአብሔር ተሰርቶ እስኪያልቅ ድረስ " ለምን እንዲ አልሆነ፣ ለምን ህይወቴ እንዲ ሆነ "አትበሉ ይልቁኑስ ሳትፈጠሩ በፊት የሚያውቃቹ እግዚአብሔር እናንተ መሆን ያለባቹን ያንን ሰው እንድትሆኑ እየሰራቹ እንደሆነ አስቡ።

@thedayofPentecost
@thedayofPentecos
t


ምን አይነት ፍቅር ነው 🙆

መግደላዊት ማርያም ትባላለች ኢየሱስን በጣም ከመውደዷ የተነሳ " በቃ ጌታሽ እኮ ሞቷል " ተብላ እንኳን ሽቶ ልቀባው ነው በሚል ሰበብ የሞተ ስጋውን ለማየት ለሊቱ እስኪነጋላት አጠብቅም ፤ ባይገርማቹ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርቶች ኢየሱስ በህይወት እያለ " አንተ ጌታችን ነህ " ብለውት ነበር ነገር ግን ኃላ ላይ እንደ ሰው ሲሞት ሀሳብ ቀይረው ሁሉም ወደ ኋላ ተመለሱ ይቺ ድንቅ ሴት ግን በህይወት እያለ በራሷ ላይ ብቸኛ ጌታ ያረገችውን ኢየሱስን ሞቶም እንኳን ልትቀይረው አልፈለገችም፤ ምን አይነት ፍቅር ነው 😭 ምን አይነት መረዳት ቢኖራት ነው ኢየሱስ ሞቶም እንኳን ለእርሱ ያላት ፍቅር አልቀዘቅዝ ያለው እናንተዬ ለካስ ኢየሱስ እንዲም ይወደዳል....ትዝ ካላቹ ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላም ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን የገለጠው ለዚች ድንቅ ሴት ነበር 🔥የተወደዳቹ ትናንት ላይ ይቺን ሴት የነካት ይሄ ታላቅ ፍቅር ዛሬ ላይ ሁላችንንም እንዲነካን ፀሎቴ ነው 🔥🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecos
t


🎙️ ውዴ 😭

አውቃለው ደጅ እንዳስጠናሁህ😢
በውድቅቱ ለሊት እንዳስቆምኩ😔
ይገባኛል ብዙ እንደታገስከኝ😭
ጠልን ብርድን ችለህ እንደጠበከኝ😢

እባክህን አትሂድ ጠብቀኝ...🙏🙏

የመዝሙሩን ግጥሞች አስተውላቹ ስሙ

@thedayofpentecost
@thedayofpentecos
t


Almost ከግማሽ በላይ ልጆች ለመንፈሳዊ ህይወታቹ መድከም ምክንያት ነው ያላቹት የገዛ ስልካቹን ነው... ታዲያ ለምንድነው የመድከማቹን ምክንያት እያወቃቹ ዝም የምትሉት ? ? እናንተ መፀለይ ፈልጋቹ ስልካቹ ግን እንድትፀልዩ ካላደረጋቹ፣ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ህብረት ከከለከላቹ ፣ ውዱን ለእርሱ ትርፍራፊውን ደግሞ ለጌታ እንድትሰጡ ካደረጋቹ በእርግጠኝነት እኮ ይሄ ነገር እየገደላቹ ነው ለዚያውም ሳይታወቃቹ... Social media ይጠቅማቿል እርሱ ምንም ጥያቄ የለውም ነገር ግን መንፈሳዊ ህይወታቹን የሚጎዳባቹ ከሆነ ቢቀርባቹ ትጠቀሙ ይሆናል እንጂ በፍፁም አትጎዱም....

@thedayofpentecost
@thedayofpentecos
t


ታውቃላቹ አይደል ከኢየሱስ ሌላ የሚራራልን ፣ እንደ አባት የሚሰማን ወዳጅ ፈልገን እንደማናገኝ... ባይገርማቹ ሰው ድካማቹን አይቶ ፊቱን ያጠቁርባቿል ሰው አለባበሳቹን ፣ የኑሯቹን ደረጃ አይቶ ይንቃቿል ኢየሱስ ግን..ኢየሱስ ግን😭 ብቻ እንዲህ ነው አልላቹም ታውቁታላቹ ፤ ዘማሪዋም ይሄ እውነት ገብቷት ይመስለኛል " ማንም የለኝ ከኢየሱስ በላይ ስመላለስ በዚች ምድር ላይ ነፍሱን ለኔ ቤዛ ያረገው እውነተኛ ወዳጄ እርሱ ነው " ብላ የዘመረችው፤ አዎ ልክ ብላለች ማንም የለም እንደ ኢየሱስ ፣ ህመማችን የሚገባው 😭😭ማንም የለም እንደ ኢየሱስ ሸክማችንን የሚሸከምልን 😭😭 " ኢየሱስ" ከማንም በላይ የቅርባችን ነው

@thedayofpentecost
@thedayofpentecos
t

3k 0 27 2 67

ውሀው ባህሪውን ቀየረ...

አንድ ጊዜ ጴጥሮስ ኢየሱስ በውሀ ላይ ሲራመድ ያይና " ጌታ ሆይ እኔም በውሀ ላይ እንድሄድ ጥራኝ " ይለዋል ኢየሱስም "ና "ብሎ በአንዲት ቃል በውሀ ላይ እንዲሄድ ፍቃድ ይሰጠዋል፣ ጴጥሮስም ውሀ ያሰጥማል የሚለውን እውቀት ወደ ጎን ትቶ ያሰምጥ በነበረው ውሀ ላይ እየተራመደ ወደ ኢየሱስ ይሄዳል ነገር ግን መሀል ላይ ሲደርስ አይኖቹን "ና "ብሎ ከጠራው ከጌታ ላይ አንስቶ በመአበሉ ላይ ማድርግ ሲጀምር ያ የቆመበት ውሃ ከድቶት መስመጥ ጀመረ፤ እናንተዬ🥰 ለካስ መጀመሪያም ውሀው ባህሪውን የቀየረው ጴጥሮስ ኢየሱስን ማየት ስለጀመረ ነው እንጂ ውሀው ከቀድሞ የተለየ ሆኖ አይደለም... እስቲ ይሄን ነገር ወደ እናንተው ህይወት አምጡትና እስከ ዛሬ ስንት በህይወታቹ ላይ መሆን የሚችሉ ነገር ግን እናንተ ኢየሱስን ማየት ባለመቻላቹ ብቻ ሳይሆኑ የቀሩትን ነገሮቻቹን አስቡ...የተወደዳቹ እኛ እስከ ዛሬ ጌታን ባለማየታችን ምክንያት ብዙ ነገሮች አቅም አግኝተው አሸንፈውን ይሆናል ነገር ግን አይናችንን ከሚታየው መአበል ይልቅ ኢየሱስ ላይ ማድረግ ከቻልን የሚያሰምጠው ውሀ ራሱ ባህሪውን ቀይሮ መንገድ ይሆነናል

@thedayofPentecost
@thedayofPentecos
t


እንደ ወንድም አንድ ነገር ልበላቹ ያው ብዙዎቻቹ ወጣቶች ናቹ ወጣት ደግሞ በየቀኑ ፈተና ውስጥ ነው በተለይ ደግሞ በዚህ ጊዜ .... ለምን ከጌታ ቤት Back አታደርግም፣ ለምን Porn አታይም ፣ ለምን ከአለም ጋር አትመሳሰልም፣ የሚሉ ድምጾች በየቀኑ የያዛቹትን ታላቅ እውነት ከእጃቹ ላይ ነጥቀው ተራ ሰው ሊያደርጓቹ
ይታገላሉ ... አዎ ልክ ነው በዚህ ዘመን ሁሉም መጥፊያው መረብ ውስጥ ሊያስገባቹ ይሞክራል ነገር ግን የተወደዳቹ ምን ያህል ጥላት ሊያጠፋቹ ቢሞክርም እናንተን የያዛቹ ጌታ ግን ፈፅሞ
እንደማይጥላቹ እወቁ ብዙ ልብ ሰራቂዎች፥ ብዙ በኃጢአት እንድትወድቁ የሚፈልጉ ሀሳቦች ቢኖሩም ከሁሉም በላይ ግን ፀንታቹ እንድትቆሙ የሚያደርጋቹ የምህረት እጅ እንዳለ አትርሱ ፤ በዚህ ሰዓት ደክማቹ፣ አቅም አታቹ ይሄን መልዕክቴኝ የምታነቡ የአባቴ ልጆች ካላቹ እግዚአብሔየደከሙበትን ልጆቹን ወደ እርሱ የሚጠራበት ምህረት የሚባል የፍቅር ቋንቋ እንዳለው ልነገራቹ ፈልጋለው።

@thedayofPentecost
@thedayofPentecos
t

6k 0 30 7 93

ከልባቹ ደጋግማቹ ስሙት

ፊትህን ማየት ባይኖር 😭🥺
ፀሎት ባይሆን መደበቂያ🥺🥺
ፀጋህ ባይደግፈኝ😭😭
ምን ቃል ያፅናናኝ ነበረ?🤷‍♀🤷‍♀

አላገናኘውም ጥያቄና ፊትህን🥺
አኩርፌ ልርቀህ ስፍራዬን ልለቅ🥺
በእንባ ነገሬ ላንተ ስሞታ😭
አልፈን የለ ወይ አባጣና ጎርባጣ🥺


@thedayofPentecost
@thedayofPentecos
t


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የበሰበሰ ሬሳ 🔥🔥እንዴት ?

እግዚአብሔር በእኔ ተጠቅሞ የበሰበሰ ሬሳ ራሱ አስነስቷል 😱ሐዋሪያው ንጉሴ ሮባ.... ከላይ ሙሉ ምስክርነቱን ስሙት ርሀቡ ካላቹ ደግሞ የዚህን ትልቅ የእግዚአብሔርን ሰው የህይወት ታሪክ YouTube ላይ ፈልጋቹ ብታዩት ይጠቅማቿል.... እግዚአብሔር ዛሬም ይሰራል🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecos
t


እረ ተዉዉዉ 🗣️

በየቀኑ በየ Social media ው ምንም ቁም ነገር ለሌው ነገር Like እና Comment 💌እየሰጣቹ " እረ የዚህ ልጅ ቀልዶች አይጠገቡም .... ዛሬ ደግሞ እንትና ምን ሆና ነው እንዲህ የለበሰችው... አየክ YouTube ላይ የተለቀቀውን የእከሌን ጉድ ... Instagram ላይ የዛችን ልጅ አለባበስ እየሽው አይደል እንዴት እንደሚያምር 💃.... እያላቹ ከቆያቹ በኋላ ራሳቹ መስሚያ ጥቂት ጊዜ ስታገኙ ደግሞ ኤርሚ ባይገርምህ መንፈሳዊ ህይወቴ እኮ ደከመብኝ ፣ እንደ ዱሮም መፀልይ አቁሚያለው ትሉኛላቹ ☺️ የተወደዳቹ እናንተ በየ እለቱ እንደ ቀላል እያያቿቸው የምታደርጓቸው ነገሮች የእናንተ መንፈሳዊ ህይወት የማድከምም የማጠንከርም አቅም እንዳላቸው ማወቅ አለባቹ... ቁኑን ሙሉ በመንፈስ እንዳትሆኑ በሚያደርጓቹ ሁኔታዎች ተከባቹ ቆይ እንዴት ነው ከጌታ ጋር ጊዜ ማሳለፍ የምትችሉት ? በፍፁም አትችሉም ! ሲጀመር ቀልድ ቀልድን እንጂ ፀሎትን የመሳብ አቅም የለውም ለዚህ ነው ውሏቹን ቃሉን እንድታጠኑና እንድትፀልዩ በሚያደርጓቹ ነገሮች መካከል ማድረግ ያለባቹ።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecos
t


እንደ ልማድ ሳይሆን ከልባቹ ይሄን ቃል እንድትሉት ፈልጋለው

ትናንትናቹን አስቡና እግዚአብሔር ታማኝ ነው በሉ! የነገራቹን እያሰባቹ እግዚአብሔር ታማኝ ነው በሉ... በሉ እያላቹ አይደለም ድምፆቹን ከፋ አድርጋቹ እግዚአብሔር ሆይ አንተ እኮ ታማኝ ነክ በሉት... እግዚአብሔር አልዋሸንም ለዚህ ነው ታማኝ ነክ የምንለው በቃ ዝም ብላቹ አንተ ለኔ ታማኝ አባት ነህ በሉት፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው

@thedayofPentecost
@thedayofPentecos
t


የዚህን ሰው የፀሎት ህይወት ያነበበ ሰው Normal መሆን አይችልም🔥

APOSTLE JOSEPH AYO BABALOLA ይባላል🔥
🔥

APOSTLE BABALOLA በናይጄሪያ አገር የተነሳ የመጀመሪያው ሐዋርያ ነበር፤ ከላይ የምታዩት የጉልበት አሻራ የዚህ ድንቅ የእግዚአብሔር ሰው የጉልበት አሻሮች ናቸው፤ እግዚአብሔር ለዚህ ሀያል ሰው በፀሎት ስፍራው የጉልበቶቹ አሻራዎች በአለት ላይ ለታሪክ አስቀምጦለታል፤ እንዴት አንድ ሰው ለ 7 ቀናት ሳይነሳ ያለማቋረጥ መፀለይ ይቻላል? ለሐዋርያው አዮ ባባሎላ ግን የተለመደ ነው፤ ይህ ብቻ አይደለም እጅግ ብዙ ተራሮችን እየመነጠረ የፀሎት ስፍራ እንዲሆኑ ያደረገ ሰው ነበር፤ በዚህ ሀያል ሰው እጅ በአንድ ሳምንት ብቻ 100 ለምፃሞች ተፈውሰዋል፣ ከ50 በላይ አንካሶች ዘለዋል፣ 30 የሚያክሉ አይነስውራን አይኖቻቸው አይተዋል፤ አሁን ላይ የዚህ ሰው የፀሎት ስፍራ በመንግስት ጥበቃ እየተደረገለት ብዙ ቱሪስቶች ይጓበኙታል።

ፀልዩ የሚፀልይ ሰው ክብር ያያል🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecos
t


🎙️እንዳትተወኝ 🙏

ሁላቹም በዚህ መዝሙር ራሳቹን እዩ... የምትችሉ ከሆነ ደግሞ ብቻቹን ስቶኑ ስሙት

@thedayofPentecost
@thedayofPentecos
t


እረኛዬዬዬ

🐑 ቆይ እረኛዬዬ እኔን ምን ያህል ቢወደኝ ነው እስካሁን ሳይሰለቸኝ በእቅፉ ሊይዘኝ የቻለው ? ጥሩ ፀባይ ኖሮኝ ነው ወይስ ከቤቱ የሚያባርረኝ ከባድ በደል ሳይገኝብኝ ቀርቶ ? እኔንጃ ብቻ አንድ ነገር አውቃለው እረኛዬ ለእኔ ምህረቱን አብዝቷልኛል 😭 ብዙ ጊዜ የአለም ነገር አማሎኝ እረኛዬ ካሰማራኝ ስፍራ ጠፍቼ ሩቅ መንገድ ሄዴ አውቃለው እና በዚህ ጊዜ ያ የሚፈልገኝ ተኩላ 🐺 ከመንጋው ተለይቼ ብቻዬኝ አቅም እንደማይኖረኝ አውቆ ሊበላኝ ይመጣ ነበር ነገር ግን ይሄ ይወደኛል ያልኳቹ እረኛዬ ድንገት መጥቶ ከበላተኛው እጅ ነጥሎ ይወስደኛል😭 እረኛዬዬዬ... እረኛዬ ካሰማራው መንጋ መካከል ለአንድ አፍታም ቢሆን ርቄ እንድሄድበት አይፈልግም ፤ አንዳንዴ እንደውም ከመንጋው መካከል የእኔ ልቤ በአለም ነገር መሰረቁን ሲረዳ ቀረብ ብሎ ስሬ ይቀመጥና በዛ ውብ እጆቹ ያሻሻኛል ወደ እቅፉም አስጠግቶ አይን አይኔን እያየ " ለአንቺ መልካም እረኛ እኔ ነኝ ለዘላለም እጠብቅሻለው ከእጄ ማንም አይወስድሽም ብሎ ይነግረኛል 😭

ኢየሱስ የእኔ እረኛ 💯

@thedayofPentecost
@thedayofPentecos
t

5k 0 72 7 87

አንድ ሰሞን 💪🔥..... 😞🙇

መፀለይ ታዞትራላቹ ፣ ውስጣቹም በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ይቀጣጠላል የሚደንቁ ህልሞችንና ራዕዮችንም ማየት ትጀምራላቹ ፣🔥 ነገር ግን ይሄ ከአንድ ሰሞን አያልፍም ደግሞ ወደዛ ወደማቶዱት ህይወት ትመለሳላቹ... መድከም ትጀምራላቹ🙍 ያንን ትጋታቹን ትጥሉታላቹ፣ ኃጢአት Normal ይሆንባቿል ብቻ ብዙ ነገር... አሁን በዚህ አይነት ድካም ውስጥ እያለፈ ያለ ሰው ካለ የምለው ነገር በደንብ ይገባዋል ብዬ አስባለሁ ፤ " ግን ለምንድነው ምደክመው ? " የብዙዎቻቹ ጥያቄ ነው እስቲ ላንዳፍታ ይሄ ጥያቄ በውስጣቹ የሚፈጠርባቹ ልጆች ጥቂት ጊዜ ወስዳቹ ዙሪያቹን ተመልከቱ...የአባቴ ልጆች እናንተ አላስተዋላቹም እንጂ እኮ የእናንተ አድካሚዎች በዙሪያቹ ነው ያሉት ለምሳሌ ጓደኞቻቹ ፣ የ social media አጠቃቀማቹ እና ሌላም... የተወደዳቹ እንደ ወንድም የምትሰሙኝ ከሆነ አንድ ምክር ልምከራቹ፤ እንድትደክሙ ከሚያደርጓቹ ነገሮች መካከል ራሳቹን አርቁ በቃ ወስኑ አውቃለው ከለመዳቹት ነገር መለየቱ ያማል ነገር ግን እያመማቹም ቢሆን
ሳታውቁት አቅማቹን እየበሉባቹ ካሉ ነገሮች
ጥናቹ ራሳቹን አግልሉ።

@thedayof
Pentecost
@the
dayofPentecost

Показано 20 последних публикаций.