ይሄን በምስሉ ላይ የምታዩት ቢራቢሮ የመሆን ሂደት Metamorphosis ይባላል እንደምታዩት ቢራቢሮው መጀመሪያ አካባቢ ላይ በደንብ መሄድ አይችልም ፣ መልክም ብትሉ የሚስብ መልክ የለውም ብቻ ንፁ ትል ነው ነገር ግን ይሄ ትል የሆነ ጊዜ ላይ ከከበቡት ነገሮች ተለይቶ ብቻውን ራሱን ለመቀየር ይሞክራል ከዛም ትናንት ላይ ሰውነቱ ላይ ተጣብቀው አላስኬድ ያሉትን ነገሮች ሁሉ አወላልቆ ተአምር በሚመስል መልኩ ክንፍ ኖሮት ስሙን ቀይሮ ዲራቢሮ ይሆናል፤ ይሄን እንደምሳሌ ያየነውን Metamorphosis የሚባለው የለውጥ ሂደት በእኛው ህይወት ስርዓት ውስጥ እንደ ትልቅ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን ፤ በዚህ ሰዓት ይሄን መልዕክቴን የሚያነቡ በህይወታቸው ተስፍ የቆረጡ ፣ በኃጢአት ልምምድ ውስጥ የሚገኙ ፣ በህይወታቸውም በፍፁም ሊቀይሩት በማይችሉት መጥፎ ሁኔታ ውስጥ የገቡ የሚመስላቸው ብዙ ልጆች ይኖራሉ ፣ የአባቴ ልጆች ዛሬ እኔ አንድ ጥያቄ ልጠይቃቹ የእውነት ለፍጥረት ይሄን የሚያስደንቅ የለውጥ ስርዓት የሰጠ እግዚአብሔር የእናንተን የልጆቹን ድካም የሞላበትን ህይወት መለወጥ የሚከብደው ይመስላቿል ? በፍፁም አይከብደውም። ብቻ እናንተ እግሩ ስር ቆዩለት እንጂ እርሱ የእናንተን ደካማ ማንነት ከላያቹ አውልቆ የእርሱን ጥንካሬ ለመስጠት ዛሬም ዝግጁ ነው።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
እግሮቹ ስር ቆዩና ራሳቹን ቀይሩ !
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost