ሰውዬው አይነ-ስውር ነው፤ ስራውም ቢሆን ልመና እንደነበር መጽሐፍ ይነግረናል የሰፈሩ ሰዎችም ለምልክት ካልሆነ በስተቀር የእርሱን ስም መጥቀስ አይፈልጉም፤ ቢበዛ ያ የለማኙ ሰፈር ቢባልለት ነው ብቻ ምን ልበላቹ ሰውዬው ባጭሩ ብዙ ማማረሪያ ምክንያቶች ነበሩት ነገር ግን አንድ ቀን ኢየሱስ አይኖቼን ያበራቸዋል የሚል ተስፍ ነበረው ደስ የሚለው ተስፍውም ባዶ አልቀረም የሚፈልገው ኢየሱስ አንድ ቀን ይለምንበት በነበረበት ስፍራ በኩል አለፈ፤ እና ይሄም ሰው ይጠብቀው የነበርው እድል እንዲያመልጠው ስላልፈለገ የዳዊት ልጅ ሆይ ማረኝ ብሎ መጣራት ጀመረ 🗣️ የሰውዬውም ድምፅ ድንገት ባለመፍትሄው ኢየሱስ ጆሮ ደረሰ፤ ኢየሱስም አይነስውሩን ሰው አስጠርቶ አይተው የማያውቁትን አይኖቹን አበራለት ጉዳዩ ተአምር ተባለ ፣ የሚያውቁት ሁሉ ግራ ተጋቡ፣ ቀስ በቀስ የዚህ ሰው ታሪክ ከተማውን አዳረሰ... እድሜውን፣ ክብሩን ያጣበት ጉዳይ ኃላ ላይ የእግዚአብሔር ክብር የሚታይበት መንገድ ሆነ፤ የተወደዳቹ ጣፋጩ በለስ ሁሉ ጊዜ በመጥፎ እሾክ የተከበበ እንደሆነ አትርሱ፤ የትኛውም እናንተ የምታልፉባቸው መጥፎ የሚመስሉ ወቅቶች ሁሉ አንድ እግዚአብሔር የሚከብርበትን ጣፋጭ የምስጋና ርዕሶችን በውስጣቸው ይዘዋል።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost
የዛሬ ችግሮቻቹ ነገ ላይ ማመስገኛ ርዕሶቻቹ ይሆናሉ ።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost