በሥነ መለኮት መምህር በግሩም ድፈቅ
በአገልግሎት ረጅም ለመሄድ ካሰብክ እነዚህን አትርሳ!!
አላማ ላላቸው ሰዎች አራት ምክር አለኝ!!
1ኛ ፀልይ
ፀሎት ለአንድ አማኝ መሰረታዊ ነገር ነው የክርስትና ፈር ቀዳጅ የሆነው መስራች ኢየሱስ የፀሎት ሰውም ጭምር ነበር ። ያልፀለየበት ቀን ያለ አይመስለኝም ደቀመዛሙርት ሲደክሙ እሱ ግን ከፀሎት አይለይም ሲለው አዳር ይፀልያል ። ጳውሎስ የፀሎት ሰው ነበር የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በፀሎት የታሸ ሕይወት ነበራቸው ። በምስጋና እና በሚፈጠሩ አሁናዊ ጉዳዮች ላይ ሁሉ ይፀልያሉ ። ፀሎት የማታያቸውን የጥላት ስራዎች ያመክናል !! ስለዚህ መፀለይ መሰረታዊ ነገር መሆኑን አውቀህ ፀልይ !!
2ኛ ቃሉን አንብብ
መፅሐፍ ቅዱስ እንድናነበው እና የእግዚአብሔር ዘላለማዊ አጀንዳ እና ፍቃድ ተረድተን ለእዚህ አጀንዳ ምላሽ ሰጥተን እንድንኖርበት የተሰጠ ሰነድ ነው ። ይህንን ካላነበብን ከእግዚአብሔር አጀንዳ ጋር ፍቃዱን ከመረዳት ጋር እንተላለፋለን ። ኢየሱስ በእዚህ ምድር እያለ እጅግ የሚያነብና በእዚህም የእውነት ተቃዋሚዎችን ፀጥ የሚያደርግ ብርቱ ነበር ጳውሎስ በሽምግልና ወራቱ እንኳ መፅሐፍ አምጣልኝ ብሎ ጢሞቲዮስን የሚጠይቅ አስገራሚ ሰው ነበር ።
"ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖስ፣ ጥቅልል መጻሕፍቱን በተለይም የብራና መጻሕፍቱን አምጣልኝ።"
2 ጢሞቴዎስ 4:13
3ኛ ተጠንቀቅ
በአገልግሎት በክርስትና ሕይወት ውስጥ ብዙ ሰዎች በታላቅ ክብር ጀምረዋል በትልቅ ተነሳሽነት ተስፈንጥረዋል ነገር ግን ሁሉም አልቀጠሉም የተወሰኑ ሰዎች ሩጫውን አቋርጠው ተመልሰዋል የቱ መሆን ትፈልጋለህ ? ከሚቀጥሉት ወይስ ከሚያቋርጡት ? ከሚቀጥሉት ካልከኝ ይሄንን አስብ!! ራስህን ከተንኮለኞች ጠብቅ በፀሎትህ ይሄንን አትርሳ ጌታ ከተኮለኞች እንዲጠብቅህ ፀልይ የዋህ እንጂ አጉል የዋህ አትሁን ከቻልክ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የመከረውን አንብብ !!
4ኛ ልብህ አይውረድ
በክርስትና አገልግሎትህ ውስጥ ብዙ ያልጠበካቸው ነገሮች ሊገጥሙህ ይችላሉ ። የከበረ ያልከው ወርዶ ጥሩ ያልከው ተቀይሮ ልታገኝ ትችላለህ ። ለመልካም ያደረከው ለክፉ ይተረጎማል ።ያቃኑልኛል ያልካቸው የሚያጣምሙ ሊሆኑ ይችላሉ ። ይሄ አዲስ አይደለም ጴጥሮስ ስለ ጳውሎስ ሲመሰክር እንዲህ ብሏል ።
"እርሱ ስለ እነዚህ ነገሮች በመልእክቶቹ ሁሉ ጽፎአል፤ በመልእክቶቹም ውስጥ በቀላሉ ለመረዳት የሚያዳግቱ ነገሮች አሉ። ዕውቀት የጐደላቸውና ጽናት የሌላቸው ሰዎች ሌሎችን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ፣ እነዚህንም ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።"
2 ጴጥሮስ 3:16
ስለዚህ በሰዎች ምክንያት ለአገልግሎት ልብህ አይውረድ መቀጠል ምትፈልግ ከሆነ ወደ ጎን ማየቱን ቀንስ እያደረክ ወደ እላይ እየተመለከትክ ቀጥል ...
ፀልይ አንበብ ተጠንቀቅ ልብህ አይውረድ ....
From facebook