ጠላ እየጠጣን ከጓደኞቼ ጋ ተሰባስበን እየቀደድን ሳለ ፦
ምድር ላይ የትኛውን ገጠመኝህን በይበልጥ ትወዳዋለህ የሚል ቀደዳ ጀመርን
ፍሬንድ ቀጠለ
"አንድ እለት እሁድ ጠዋት እናቴ ቡና እየጠጣች ፣ እየመከረችኝ ፣ እየመረቀችኝ ፣ እየሰደበችኝ ሳለ
በጣምምም ደስስ የሚልሽ ምን ብታገኝ ነው አልኳት አጠያየቄ ድንገት ነበር
ላሊበላ ፣ አክሱም ጽዮን ፣ ውቅሮ ማርያም ካዲ ብሄድ ደስ ይለኛል አለቺኝ
ፊቷ ላይ ያለው ምኞት የደስታ ዳር ይመስል ነበር። ። በነጋታው ስጣደፍ ሄጄ ቢሮ አንድ መቶ ሺ ብር ተበደርኩ ፍቃድ ወሰድኩ
ሎተሪ ደረሰኝ ብያት ላሊበላ ፣ አክሱም ጽዮን ፣ ውቅሮ ማርያም ካዲ ወሰድኳት ደስስ አላት ፀለየች ፣ ለነዲያን መፀወተች ፣ እጄን ይዛ መረቀቺኝ ።
ከዛ ከተመለስን በኋላ ሶስት ወርም አልቆየች ትንሽ አሞት ሞተችብኝ። ሳለቅስ ፣ ሳዝን ያፅናናኝ እና ያበረታኝ ህልሟን ማሳከቴ ነበር
ቀጠለ ሌላ ፍሬንድ ፦
"አንድ ቀን ክላስ ቀጥቼ ዩኒፎርሜን እንደለበስኩ ጠላ ቤት ደቅ ብዬ አባቴ ከጓደኞቹ ጋር ከች አለ ሳየው ስካሬ ጠፋ ።
ልጄ ነው ብሎ ለፍሬንዶቹ አስዋወቀኝ ። ሃይለኛ ስለነበር እዛው ካልገደልኩ ይላል ብዬ ነበር። ምንም አላለኝም ። እንደውም የጠጣሁበትን ከነ ፍሬንዶቼ ከፈለልኝ ። ቀድሜው ወጣሁ ፦
አላመንኩትም የሚገድለኝን አገዳደል እያሰብኩ ስፈራ ስቸር እቤት አምሽቼ ገባሁ ። እሱ ምንም አላለኝም ።
በሳምንቱ "ጋሻው ዛሬ ትምህርት የለህም አይደል "
"አዎ"
"በቃ ዛሬ አብረን እንዋል አለኝ" እሺ ብዬው የሚሰራበት
አብረን ሄድን
ውሎውን አዋለኝ ። የሆነ ህንፃ ይጠብቃል ፣ ህንፃው ጋ የሚቆም መኪና ይጠብቃል ፣ መኪና ያጥባል ።
የጠበቀበትን እና ያጠበበትን ብር እንዲሰጡት ደጅ ይጠናል ፤ ትንሹም ትልቁም ይጠራዋል ፣ ያዙታል ያን ቀን አባቴ በጣም አሳዘነኝ
ከፊቱ ገሸሽ ብዬ አለቀስኩ
እንዴት እንደሚያሳድገኝ ያኔ ነው የገባኝ ። ምን እያለ እንደመከረኝ ፣ በእኔ ጉዳይ ለምን እንደሚናደድ ገባኝ
የዛ ቀን ህይወቴ ተቀየረ ።
ሌላ ፍሬንድ ቀጠለ ፦
"አንድ ቀን እቃ ጠፍቶኝ ቤታችንን ሳምሰው
የታናሽ እህቴ ዲያሪ አገኘሁት በማላውቀው ምክንያት የማስሰውን ነገር ትቼ ደቅ ብዬ ማንበብ ስጀምር ።
ጥጋቤ ፣ ድፍረቴ እልሄ ተነፈሰ ። የግሩፕ ጠብ አጓጉል ውሎዬ ጣጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ገባኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ መፍራት ጀመርኩ ፤ ለቤተሰባችን ምን ያህል እንደማስፈልግ ማስታወሻዋ ነገረኝ"
ለካ አንዳንድ ቀን ብቻውን ዘመን ያህላል !!
©
Adhanom Mitiku