"I have to believe in a world outside my own mind. I have to believe that my actions still have meaning, even if I can't remember them." "ከራሴ አእምሮ ውጭ በሆነ ዓለም ማመን አለብኝ። ባላስታውስም እንኳ ድርጊቶቼ አሁንም ትርጉም እንዳላቸው ማመን አለብኝ።"
: Leonard Shelby
ፊልሙ ጊዜያቶች እንደ አሸዋ ከእጁ እየተንሸራተቱበት በራሱ ዓለም ውስጥ የሚጓዝ ሊዮናርድ ሸልቢ የተባለ ሰው አእምሮ ውስጥ የሚደረግ ረቂቅ ጉዞ ነው። ሊዮናርድ ሚስቱ ከሞተችበት እለት ጀምሮ የአምኔዥያ በሽታ ተጠቂ በመሆኑ ከዛን እለት በኋላ ያሉትን ቀናት አእምሮው ትውስታወችን መያዝ የሚችለው ለደቂቃወች ቢበዛ ለተወሰኑ ሰአታት ነው።
የሚስቱን ገዳዮች ለመበቀልም እያንዳንዱን ነገር በፎቶ እየያዘ ና በራሱ ቆዳ ላይ በፅሁፍ እያተመ ትውስታወችን ከአእምሮው ውጭ ለማስቀመጥ ይጥራል። ትዝታዎቹ እንደ ወንዝ ውሃ ናቸው፣ ያለፉት ብቻ ይታዩታል፣ አዲሶቹ ይፈሳሉ።
ፊልሙን ከሌሎች ለየት የሚያደርገው የታሪክ ፍሰቱ ወደ ኋላ የሚጓዝ በመሆኑ ነው። በተቆራረጡ ትዝታዎች መካከል በተስፋ መቁረጥ እና መቀጠል መካከል ላይ ሆኖ በሀዘን እየተነዳ፣ የበቀል ጥላ የሆነውን መንፈስ የሚፈልግ አንድን ሰው የበቀል ጉዞ ወደ ኋላ እያሳየን ይቀጥላል።
በተጨማሪም የእምነትን ኃይል፣ የራሳችንን እውነታዎች ስለምንገነባበት መንገድ እና በየጊዜው በሚቀየር ዓለም ውስጥ ትርጉም ለማግኘት ስላለው አሳዛኝ ትግል ያወሳል። እኛ እራሳችንን የምንገልፅበት መንገድ ና ለራሳችን የምንሰጣቸው የማንነት ትርጓሜዎች በትዝታ ከመገደባቸው በላይ በቀላሉ ሊፈርሱ እንደሚችሉ እያሳየ የእራሳችንን ትዝታዎች ጊዜያዊ ውበት እና ተፈጥሯዊ ጣዕም ያስቃኘናል።
"ሰው ማንነቱ ቋሚ ካልሆነ ሀሳቦቹ ሊቀያየሩ ይችላሉ። ነገር ግን ያሰው ቋሚ ትውስታ ከሌለው ቋሚ ማንነትም ሊኖረው አይችልም።"
📽️ : Memento
https://t.me/thoughts_painting