ስለአንዳንድ ነፃ አውጪ ፖለቲከኞች ስንሰማ እንደነሱ መሆን እንፈልጋለን፤ ስለአንዳንድ ጀግና ጋዜጠኞች ስንሰማ እንደነሱ መሆን እንፈለጋለን፤ ስለፊልም አክተሮች ህይወት ስንሰማ እንደነሱ መሆን እንፈልጋለን፤ ስለወታደር፣ ስለዶክተር፣ ስለፈላስፋ እና ደራሲ የህይወት ታሪክ ስንሰማ እንደነሱ የመሆን ፍላጎታችን ጣሪያ ይነካል።
እውነት ግን ለምንድነው..?
በአንዱ ሰውዬ እጅ ላይ ያለው ሲጋራ ክብሩን አዋራጅ ሆኖ ስናገኘው፤ በሌላኛው ሰው እጅ ላይ ያለው ሲጋራ የቅንጦት መለኪያ ይሆናል። ሲጋራው አንድ ቢሆንም ሰዎችሁ ይለያያሉ። ምን መሰላችሁ ይህ የካራክተር ገፀባህሪ ጉዳይ ነው። የሃብት ማማ ላይ ያሉ ሰለብሬት ነጮች የሚለብሱት ልብስና የሚበሉት ምግብ በጭራሽ አላጡም። ለዛም ነው ብዙ ሰዓቶቻቸውን ካራክተራቸውን በመስራት ግዜያቸውን የሚያጠፉት። የሚለብሱትን ልብስ የሚመስል ሰውን ለመስራት ወይም ደግሞ ለእራት በተቀመጡ ግዜ የአበላል ስርዓታቸውን ለመጠበቅ ብዙ ቴራፒዎችን ይወስዳሉ። ስፖርት መስራት፣ ተመስጦ ማድረግ፣ የጫካና የተራራ ጉዞ፣ መጾም እና ባህሪ ገዝ የሃይማኖት ስርዓትን ለመከተል ይገደዳሉ። ይህ ሁሉ ትክክለኛውን ወጥ የራስ ስታይል ለማምጣት የሚደረግ ጥረት ነው።
ከላይ የጠቀስኳቸው ከደራሲ እስከ ሰባኪ፣ ከእስፖርተኛ እስከ ፖለቲከኛ የተቀመጡ ሰዎች ማራኪነታቸው እስከ መመለክ ያደረሳቸው ይሄ የባህሪያቸው ውጤት ነጸብራቅ ነው። እኛም እነሱን ለመሆን ከመመኘት በዘለለ የራሳችን ማንነት ውጤት ለመሆን የተሰጠን ግልጽ ኃይል አለ። በብርጭቆ ላይ ያለችው ውሃን እንዴት ነው የቀዳችሁት? ከጠረቤዛው እንዴት ነው ያነሳችሁት? እንዴት ጠጣችሁት? ይሄ ጥቂት ጥቃቅን ልማድን ያቀፈ ነው። ይሄን በብርጭቆ ያለውን ውሃ ከጠረቤዛው አንስተው የሚጠጡ ሌዲስ ጀንትል ሜን ተመልከቱ እርጋታቸው አጠጣጣቸው እንዴት እንደሚያስጎመጅ።
እንግዲህ እነዚህን ካራክተር ሰርተን እራስን ለመውደድና በሌሎች ለመወደድ እነዚህ ሶስት ህግጋትን ማክበር ግድ ይላል፦በየቀኑ ያለውን የምግብ አበላል ስርዓታችንን፣ የአረማመድ ግርማ ሞገሳችንን፣ የአወራር እርጋታችንን መጠበቅ ነው።
ይቀጥል..?
@thoughts_painting