" ከ2 ሺሕ 500 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል " - አቶ አደም ባሂ
በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ አከባቢ በሚከሰት ተደጋጋሚ ርዕደ መሬት ከ100 በላይ ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸዉ ሲሆን 2 ሺሕ 560 ሰዎች መፈናቀላቸውን እና እንሰሳት መሞታቸውን የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ አስተዳደር አቶ አደም ባሂ አሳውቀዋል።
ለአሐዱ በሰጡት ቃል ፤ " ይህ ክስተት በሚድያ እንደሚባለዉ በቀን ሦስቴ እና ሁለቴ የሚከሰት ሳይሆን ከዚያም በላይ አስጊ እየሆነ ይገኛል " ብለዋል።
በአካባቢዉ ያለዉ የከሰም ግድብን ጨምሮ ሌሎች መሰረተ ልማቶችስ ጉዳት ደርሶባቸዋል ወይ ? ለሚለው ጥያቄ " ግድቡን በተመለከተ ራሱን የቻለ አደረጃጀት ተደራጅቶ እየተጠበቀ ይገኛል " ሲሉ ተናግረዋል።
" እስካሁን በተፈጠረዉ ርዕደ መሬት ምክንያት ምንም ጉዳት ባይደርስበትም፤ በተደጋጋሚ በአቅራቢያው እየተከሰተ በመሆኑ በጥብቅ እየተከታተሉ ነው " ሲሉ አክለዋል።
በተጨማሪም በአካባቢዉ ያለዉ ተፈናቃይ ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ መሆኑን አንስተው ፤ መጠለያ፣ ምግብ እና መሰረታዊ ግብአቶች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል።
የክልሉ የአደጋ ስጋት ድጋፍ እንዲያደርግም እንደጠየቁ ገልጸዋል።
በተደጋጋሚ ጊዜ በተከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦች ምክንያት፤ እስከ አሁን በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ሳቡሬ እና ዶኾ ቀበሌዎች ከ30 በላይ የመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱም ተነግሯል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአሐዱ ነው።
@tikvahethiopia