“ ቅልጥ አለቱ በመሬት ውስጥ የሚያደርገዉ እንቅስቃሴና ወደ ላይ የመውጣት ግፊቱ እንደቀጠለ ነው። ግን ቀዝቅዞ እዛው ሊቀር፣ ከመሬት በላይ ሊፈነዳ ይችላል ” - ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር)
በአዋሽ ፈንታሌና ዶፈን ቮልካኖዎች መካከል የሚከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ጠንከርና ከፍ እያለ መምጣቱ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ሰሞኑንም በተደጋጋሚ እየተከሰተ ተስተውሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለመሆኑ ምን መደረግ አለበት? ሲል ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ጥያቄ አቅርቧል።
ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ምን መለሱ ?
“ ስምጥ ሸለቆ አካባቢ ነው ያለነው። ስምጥ ሸለቆ የሚፈጠርበት ተፈጥሯዊ ሂደት ነው። ተፈጥሯዊ ስል፤ ርዕደ መሬት እያስጨነቀው ላለ ማህበረሰብም ሆነ ለእኛ ባለመያዎቹ ሲንቀጠቀጥ ያስጨንቃል።
ወዴትስ ያመራ ይሆን? የሚለው ያሳስባል። ግን መንስዔው ይታወቃል ተፈጥሮም የራሷን ሂደት እየሄደች ነው ያለችው ለማለት ነው። የስምጥ ሸለቆ አፈጣጠር አንዱ ሂደት ነው ለማለት ነው።
እናም ከዚህ ቀደምም እንደገለጽነው ቅልጥ አለት መሬት ውስጥ እየተንቀሳበሰ ነው። በፈንታሌና በዶፈን ተራራዎች መካከል። የምናየው ርዕደ መሬት የዛ ውጤት ነው።
የሰሞኑ ክስተት እየነሆነ ያለው የዛ እንቅስቃሴ የፈጠረው መንቀጥቀጥ ሞገድ በመሬት ውስጥ ተጉዞ ነው አዲስ አበባ ድረስ የሚሰማን።
መጠኑ ከፍ ሊል ይችላል ወይ? ለሚለው ጥያቄ፣ ሊልም ላይልም ይችላል። ማለትም ከዚህም በላይም ከፍ ሊል ይችላል።
ነገር ግን ይሄ በሚሆንበት ጊዜ እኛ ምን ማድረግ አለብን? የሚለው ነው መታወቅ ያለበት" የሚል ማብራሪያ ሰጥተዋል።
መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ ኤልያስ (ዶ/ር) ምን ተናገሩ?
“እስካሁን ድረስ ከፍ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥም አልመጣም። መደርግ ስለሚገባው ነገርም ሲጠቀስ አንዳንድ ሚዲያ ላይ ሰዎች መቀለጃ አድርገውታል። ‘ጠረንጴዛ ሊያድነን ነው ወይ?’ ይላሉ።
ግን ይሄ የዓለም አቀፍ ተሞክሮና ስታንዶርድ ነው። ብዙ ሰዎች በዚሁ መንገድ ከአደጋ ድነዋል።
ስለዚህ ከኮለን አካባቢ ሥር መቆም፣ ከጠረንጴዛ ሥር በፍጥነት መግባት፣ አሳንሰር አለመጠቀም፣ ፎቅ ላይ ለመውረድ አለመሞከር ያስፈልጋል።
እሳት ሊያቀጣጥሉ የሚችሉ እንደ ሻማ ያሉ ነገሮችን ማጥፋት የመሳሰሉት እርምጃዎች ቀላል ይመስላሉ ግን የብዙዎችን ሕይወት አትርፈዋል።
በጣም የአጭር ጊዜ ስለሆነ የሚሆነው ከቤት ለመውጣትም ጊዜ ላይሰጥም ይችላል።
የጊዜ አለማግኘት ብቻም ሳይሆን ቁልፍ ቆልፈን ቁጭ ብለን እንኳ እጃችንን እየተንቀጠቀጠ ለመክፈት ያዳግታል። በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ጥንቃቄዎች ማድረግ አለብን።
ማንም ሊያቆመው አይችልም ይሄንን ክስተት። ለኛ አሁን እዚህ ካለው የመሬት መንቀጥቀጥ በይበልጥ እያሰጋን ያለው ፈንታሌ አካባቢ ያለው ሁኔታ ነው። ጥፋት ካደረሰ ከኛ በበለጠ እዛ አካባቢ ነው ብዙ ጥፋት የሚያደርሰው።
እዛም ያለው የሰው ሕይወት ነው፤ እዚህም ያለው የሰው ሕይወት ነው። ሕይወት ነው የትም ቦታ ያለው። እዛ ላሉት ወገኖቻችንም እየተጨነቅን ነን ያለነው።
እዛ አካባቢ መሬት ውስጥ የሚጓዘው ቅልጥ አለት ወደ ላይ የመውጣትም እዛው የመቅረትም የሁለቱም ፓስቢሊቲ አለው።
ከቀን ወደ ቀን የምናየው መረጃ እንደሚያሳየው ቅልጥ አለቱ ወደ ላይ ለመውጣት በሚያደርገው ግፊት መሬት እየተወጣጠረች ነው፡፡
ይህ ማለት ግን እርግጠኛ ሆነን ይፈነዳል ማለት አይደለም። ቀዝቅዞም እዛው ሊቀር፣ መጨረሻም እዛው ሊቆም ይችላል።
ቅልጥ አለቱ ወደ ላይ የሚመጣ ከሆነ ምን ማድረግ አለብን የሚለውን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት፣ የመንግስት አካላት፣ መስሪያ ቤቶች፣ የግል ድርጅቶች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በሕብረት እየተሰራ እንደሆነ አውቃለሁ።
እኛ የምርምር ማዕከል ነን ሥራችን መረጃ ማቅረብ ነው። እነርሱ ደግሞ ያንን መረጃ ወስደው በተግባር ላይ ያውሉታል የሚል ሙሉ እምነትና ግምት አለን። አንዳንድ ሥራዎችም እንደተጀመሩ መረጃ አለኝ።
በኛ በኩል እንደ ምርምር ተቋም መንስኤው ምንድን ነው? መጠኑ ስንት ነው? ምን መደረግ አለበት? የሚለውን እያቀረብን ነው ያለነው።
ከዚህ በተጨማሪ ያለው ነገር መጠነ ሰፊ ሥራዎችን ናቸው የሚጠይቁት። መጠነ ሰፊ መስሪያ ቤቶችንም መቀናጀት ያስፈልጋል።
እኛ ብቻም ሳንሆን በዓለም አቀፍ በሙያው ዘርፍ ካሉት ባለሙያዎች ጋር እንደ ኢንስቲትዩት እየተገናኘና መረጃ እያቀናጀ ነው ያለው” ነው ያሉት።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia