#USA
" ታዳጊዋ በሕይወት ለመትረፍ ብዙ ታግላለች፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ወደ ቤቷ ስትሄድ ነው ይህ ገጠማት " - ሬስኪዩ ኤር አምቡላንስ
በአሜሪካ፣ ፔንሲልቫኒያ ግዛት፣ በፊላደልፊያ ከተማ ሰሜን ምሥራቅ ክፍል አንድ አነስተኛ የሕክምና ማጓጓዣ አገልግሎት የሚሰጥ ጄት በርካታ ሕንጻዎች በሚገኙበት ሰፈር ውስጥ ተከሰከሰ።
የሕክምና አውሮፕላኑ ድርጅት-ሬስኪዩ ኤር አምቡላንስ በሰጠው መግለጫ ፤ ጄቱ አርብ ምሽት አንድ ታማሚ ሕፃንና አስታማሚዋን እናቷን እንዲሁም 4 የበረራ አስተናጋጆችን አሳፍሮ እየተጓዘ ነበር ።
በአውሮፕላኑ ላይ ተሳፍራ የነበረችው ሕፃን ሕይወቷን አደጋ ላይ በሚጥል የጤና እክል የነበረባት ሲሆን በአሜሪካ ሕክምና አድርጋ ወደ ሜክሲኮ ቲጁዋና እየተጓዘች እንደነበር የአየር አምቡላንስ ድርጅቱ ለኤንቢሲ ኒውስ ተናግረዋል።
ከእናት እና ልጅ በተጨማሪም አብራሪው ፣ረዳት አብራሪው ፣ ዶክተር እና የመድሃኒት ባለሙያ በአውሮፕላኑ ውስጥ ነበሩ።
ድርጅቱ " ታዳጊዋ በሕይወት ለመትረፍ ብዙ ታግላለች፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ወደ ቤቷ ስትሄድ ነው ይህ ገጠማት " ብሏል።
አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት አካባቢም ቤቶች እና ተሽከርካሪዎች በእሳት የተያያዙ ሲሆን መሬት ላይ የነበሩ ሰዎችም ለጉዳት መዳረጋቸው ተገልጿል።
የግዛቷ አስተዳዳር " የሕይወት መጥፋት እንደሚኖር እናውቃለን፤ አደጋው አሳዛኝ ነው " ብሏል።
የፊላደልፊያ ከንቲባ ቺርል ፓርከር የከተማዋ ባለስልጣናት በአደጋው የደረሰው ጉዳት መጠን ምን ያህል እንደሆነ አለማወቃቸውን ገልጸው ፤ በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን በፀሎት እንዲታሰቡ ጠይቀዋል።
እስካሁን በህይወት ያለ ሰው ስለመኖሩ ማረጋገጥ አልተቻለም።
ከቀናት በፊት በዋሽንግቶን ዲሲ የመንገደኞች አውሮፕላን ከጦር ሄሊኮፕተር ጋር ተላትሞ ወንዝ ላይ ከተከሰከሰ በኃላ በህይወት የተረፈ ሰው አልተገኘም።
መረጃው ከቢቢሲ እና ኤንቢሲ ኒውስ የተውጣጣ ነው።
ቪድዮ ፦ ፌርበክ
@tikvahethiopia