#NationalExam
" ፈተናው ስታንዳርዱን ፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በተማሩበት ሥርዓተ ትምህርት ይዘት እየተዘጋጀ እንደሆነ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
አገልግሎቱ ፤ " የ2017 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ - 10ኛ በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣ ከ11ኛ - 12ኛ ደግሞ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው " ብሏል።
" ነገር ግን በ2015 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በናሙናነት በተመረጡ ት/ቤቶች የስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ላይ የተሳተፉ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው " ሲል ገልጿል።
በአማራ ክልል በ2016 የትምህርት ዘመን መፈተን ሲገባቸው በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም የሚፈተኑ እንዳሉም ጠቁሟል።
በዚህም " የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከላይ የተገለጹትን ሶስቱንም ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባ እና ሁሉንም የዘመኑን ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ ስታንዳርዱን ፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል " ሲል አሳውቋል።
የፈተና ዝግጅቱ፡-
1) ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣
2) ከ10ኛ ክፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣
3) ከ11ኛ ከፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣
4) ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ እንደሆነ ተገልጿል።
ከላይ የተዘረዘረው የዝግጅት ሂደት በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ላይ እንደተጠበቀ ሆኖ የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚዘጋጅ እንደሆነ ተመላክቷል።
በአጠቃላይ ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ -12ኛ ክፍል በየተማሩበት የሥርዓተ ትምህርት ይዘት ላይ መመስረት ፈተናው እንደሚዘጋጅ አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አገልግሎት መ/ቤቱ አሳስቧል።
ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ወላጆች፣ መምህራንና መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፏል።
የዘንድሮ ሀገር አቀፉ የ12ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና መቼ እንደሚሰጥ እስካሁን የተወሰነ ነገር የለም።
@tikvahethiopia