#MoE #AAU #ExitExam
አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ሰኞ ይፋ ባደረገው የተሻሻለ የአካዳሚክ ካላንደር በሰኔ ወር ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው የ2017 ዓ/ም ሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ ጠቁሟል።
ተማሪዎቹንም ሰኔ 21 እንደሚያስመርቅ ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተቋሙ ስም ይፋ ተደርጎ የተሰራጨውን የአካዳሚክ ካላንደር ትክክለኝነት ከሚመለከታቸው የዩኒቨርሲቲው አመራር ማረጋገጥ ችሏል። አንድ የተቋሙ አመራር " ከመጨረሻው ሐምሌ 2 ከሚለው ውጪ ሁሉም ትክክል ነው። የመጨረሻው ሐምሌ 8 ነው የሚሆነው " ብለዋል።
ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ይፋ ባደረገው ካላንደር የመውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ/ም ባለው ጊዜ እንደሚሰጥ ቢጠቁምም ትምህርት ሚኒስቴር እስካሁን ስለ ፈተናው ቀን በይፋ ያሳወቀው ቀን የለም።
በሌላ በኩል የመውጫ ፈተና በድጋሜ የሚፈተኑ ተፈታኞች በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " አሁን ላይ የመወጫ ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ ተፈታኞችን የምዝገባ ሁኔታ እየገመገምን እንገኛለን " ሲል ገልጿል፡፡
በድጋሜ የመውጫ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ለመጀመሪያ ጊዜ ከሚፈተኑት ጋር አብረው ፈተናውን እንደሚወስዱም አመልክቷል።
ከሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲከናወን የቆየው የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዳግም ተፈታኞች ምዝገባ ነገ ግንቦት 05 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡
እስካሁን ድረስ ምዝገባ ያልፈጸሙ ተማሪዎች የመመዝገቢያው አድራሻ / ሊንክ https://exam.ethernet.edu.et በአግባቡ እየሰራላቸው እንዳልሆነ በጠቆም የምዝገባ ጊዜው እንዲራዘም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት ጠይቀዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ከምዝገባ ጋር በተያያዘ ገምግሞ ይፋ የሚያደርገው አዲስ ነገር ካለ የምንከታተለው ይሆናል።
ከዚህ በተጨማሪ ደሞ " በዲሲፕሊን ምክንያት የመውጫ ፈተና ውጤታቸው ተሰርዟል " የተባሉ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ማዕከል ድጋሚ ተፈታኞች ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ ምዝገባ ማድረግ አለባቸው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia