#Hawassa
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ታቦር ክፍለ ከተማ አዲሱ ገበያ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በአንድ የገበያ ማዕከል ኮንቴነር ላይ የተነሳ የእሳት አደጋ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ መምሪያ አስታዉቋል።
የእሳት አደጋዉ የተከሰተው ጠዋት 1:30 አከባቢ ታቦር ክፍለ ከተማ ፋራ ቀበሌ በተለምዶ አዲሱ ገበያ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በአንድ የንግድ ሼድ ሱቅ ነው።
በከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ነፃ የስልክ መስመር (7614) በደረሰ ጥቆማ የከተማ አስተዳደሩ እሳት አደጋ እንዲሁም የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ እስት አደጋ መኪኖች ከፀጥታ አካላትና ከአከባቢው ሕብረተሰብ ጋር በመሆን የእሳት አደጋውን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተገልጿል።
"እንደ ወቅቱ ነፋሻማነትና ፀሐያማነት የእሳት አደጋዉን በቀላሉ መቆጣጠር አዳጋች ነበር"ያሉት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ቶርባ በከተማ አስተዳደሩ የተዘረጋዉ ፈጣን የመረጃ ልዉዉጥ አደጋውን ለመቆጣጠር አግዟል ነው ያሉት።
አደጋዉ የከፋ ጉዳት እንዳያደር ላደረጉ የአከባቢው ነዋሪዎች፣ፈጣን ምላሽ ለሰጡ የሀዋሳ ከተማ እና ሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እንዲሁም የፀጥታ አካላት የከተማ አስተዳደሩ ሠላምና ፀጥታ ምስጋና አቅርበዋል።
የእሳት አደጋው ትክክለኛ መንስኤ እየተጣራ ነዉ ያሉት መምሪያ ኃላፊው ወቅቱ በጋ በመሆኑ ፀሐያማና ነፋሻማዉ የአየር ፀባይ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ስለሚታሰብ ሕብረተሰቡ ተገቢዉን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
#TikvahFamilyHawassa
@tikvahethmagazine