የረሃብ ጠላት የተባለለት እንሰት . . .
ከአንድ የእንሰት ተክል እስከ 50 ኪሎ ግራም ምግብ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ታዲያ ለዚህም ይመስላል "Tree against hunger.” የሚል አዲስ ቅጽል ስም የወጣለት።
እስካሁን ባሉት መረጃዎች እንሰት የኢትዮጵያን ህዝብ አንድ ስድስተኛውን ወንም 20 ሚሊዮን የሚጠጋ የማኅበረሰብ ክፍልን ይመግባል ተብሎ ይታሰባል።
በመንግስት ደረጃ የእንሰት ተክልን በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልሎች ለማስፋፋት እቅድ መያዙ የተገለጸ ሲሆን እ.ኤ.አ እስከ 2031 ከላይ የተገለጸውን ቁጥር ወደ 40 ሚሊዮን ለማሳደግ ታቅዷል።
ሆኖም መንግስት ልክ እንደ ጤፍና ስንዴ የጀመረው ሀገር አቀፍ ተነሳሽነት እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገም። ይህ ተነሳሽነት በተያዘው አዲሱ ዓመት መጀመሪያ ይጀመራል ተብሎም ይጠበቃል።
የእንሰት ምርትን ለማስፋፋት የተለያዩ ንቅናቄዎች ያሉ ሲሆን ለአብነትም በፈረንሳይ ኤንባሲ ድጋፍ፤ በ5 ዓመት የሙከራ ፕሮግራም፥ አማካኝነት በአማራ ክልል 2,258 ችግኞች ተተክለው በርካታ አርሷደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ተብሏል።
ይህንን መነሻ በማድረግም የግብርና ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ 400 ሚሊዮን የእንሰት ችግኞችን ለመትከል የሚያስችል የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት እንደ USAID ካሉ ተቋማት ጋር እየተነጋገረ ይገኛል ተብሏል።
የእንሰት ምርት ከኢትዮጵያ ተሻግሮ ተፈላጊነቱ በሌሎች ሀገራትም ተስተውሏል። ለአብነትም ኬንያ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ድጋፍ ከ2023 እ.ኤ.አ የእንሰት ምርት ላይ ሙከራ በማድረግ ላይ ትገኛለች።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ2024 ባወጣው ሪፖርት መሰረት 733.4 የሚሆኑ ሰዎች ለረኃብ መጋለጣቸውን ጠቅሶ ይህም ከ5 አፍሪካዊ አንዱ ለረኅብ መጋለጡን አስታውቆ ነበር።
የምግብ ዋስትና ጉዳይ አሁን ላይ የዓለም መንግስታት ዋነኛ ጉዳያቸው ሲሆን ቁጥሮች እንደሚያሳዩት በዓለም 2.3 ቢሊዮን ሰዎች ለምግብ ዋስትና ሥጋት ተጋላጭ ናቸው።
Credit : La Croix international
@tikvahethmagazine