በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ ቦንብ ፈንድቶ በ8 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ።
በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ አሳሊ ቀበሌ ልዩ ስፍራው ዱቤ 02 ንዑስ ተብሎ በሚጠራበት መንደር ቦንብ ፈንድቶ በ8 ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን የደቡብ ምዕራፍ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፓሊስ አስታውቋል።
ኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት የቦንብ ፍንዳታው የተፈጠረው ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ ነው።
በዚህም ፍንዳታ በስድስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እና በሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በተርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ነግረውናል።
ፖሊስ ባደረገው ማጣራት የአደጋው መነሻ ምክንያቱ የአንድ ግለሰብ አሮጌ መኖሪያ ቤት አፍርሶ በአዲስ ለመስራት በአከባቢው አጠራር ዳጉዋ (በደቦ) ሥራ ላይ የነበሩ ስምንት ሰዎች በቁፋሮ ወቅት ያገኙትን F1 የተባለ የእጅ ቦንብ ባለማወቅ በድንጋይና በመዶሻ በመቀጥቀጣቸው ፍንዳታው መከሰቱን አስረድተዋል፡፡
ፖሊስ የእጅ ቦንቡ በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ተቀብሮ ሊገኝ እንደቻለ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውሎ ቦንቡ ከየት እንደመጣ፣ እንዴት ግለሰቡ ቤትስ ሊገኝ እንደቻለ ተጨማሪ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝና የምርመራ ውጤቱ እንደተጠናቀቀ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ኢንስፔክተር ደጀኔ ነግረውናል።
ህብረተሰቡ መሰል የፍንዳታ አደጋዎች እንዳይደርስ ምንነቱ የማይታወቅ ነገሮችን ሲያገኝ ከመቀጥቀጥ በመቆጠብ ለሚመለከተው አካል እንዲያሳውቅ እና ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሲሉም አሳስበዋል።
@tikvahethmagazine