#Update: በቴሌግራም የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽም የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።
የግለሰቦችን የቴሌግራም አድራሻ በተለያዬ ዘዴ በመጥለፍ በስማቸው ሲያጭበረብር የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ከሰሞኑ የግለሰቦችን የቴሌግራም አካውንትን በመጠቀም የማጭበርበር ወንጀል ስለሚፈጽሙ ወንጀለኞች መበራከት ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር።
በዚህም አንድ ወንጀለኛ የአንድ ግለሰብን የቴሌግራም አካውንት በመጥለፍ የተቸገረ በማስመሰል ገንዘብ ጠይቆ በማስላክ ለግል ጥቅሙ ሊያውል የነበረው ተጠርጣሪ በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።
የቢራሮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር መሀመድ ይማም እንዳሉት ከሰሞኑ አንድ የግል ተበዳይ የቅርብ ቤተሰቡ የሆነች ልጅ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳለችና ገንዘብ እንደሚያስፈልጋት በቴሌግራም አድራሻዋ 340 ሽህ ጠየቀችው ያለውን 180 ሺህ ብር ከላከ በኋላ ሲያጣራ አድራሻዋ መጠለፉ ተረጋገጠ ብለዋል።
በዚህ መነሻነት ፖሊስ ተከታትሎ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልፀው አሁን አሁን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የማጭበርበር ስራዎች እየጨመሩ መሆናቸውን አንስተዋል።
በመጨረሻም ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ሂደት ማህበረሰቡ ላደረገላቸው ጥቆማ ያመሰገኑት ም/ኢንስፔክር መሀመድ ይማም ወደ ፊትም ከፖሊስ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃው የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ነው።
@tikvahethmagazine