ከ1ወር በፊት በደረሰ ትራፊክ አደጋ 74 ሰዎች በሞቱበት ቦታ ላይ ተመሳሳይ አደጋ ደረሰ።
ሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከ1ወር በፊት በደረሰ ትራፊክ አደጋ 74 ሰዎች በሞቱበት ቦታ ላይ ተመሳሳይ አደጋ መድረሱን አስታወቀ።
በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ጥር 20 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሽቱ 5፡30 ሰአት ገደማ ሲኖትራክ መኪና ከሀዋሳ ወደ በንሳ ዳዬ በመጓዝ ላይ ሳለ መንገድ ስቶ ገላና ወንዝ ድልድይ ገብቷል።
በአደጋው ሾፌሩና ረዳቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በቦና ሆስፒታል ህክምና ላይ እየተደረገላቸው ይገኛል።
ከ1ወር በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በሲዳማ ክልል ቦና ዙሪያ ወረዳ በአይሱዙ የጭነት መኪና ተጭነው ከ75 በላይ ሰዎች ለሰርግ ሲሄዱ በደረሰ ሰቅጣጭ አደጋ 74 ሰዎች የሞቱ መሆኑ የሚታወስ ነው።
ከሟቾቹ ሰዎች ውስጥም ከ50 በላይ የሚሆኑት የአንድ ቤተሰብ አባላት እና ዘመዳሞች መሆናቸው መነገሩ ይታወሳል።
እንደ ፖሊስ ገለፃ ቦታው ጠመዝማዛና አደገኛ ቁልቁለትና ዳገታማ ቦታ በመሆኑ ዘላቂ መፍትሄ እስኪበጅ አሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
መረጃው የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው።
@tikvahethmagazine