በደቡብ ሱዳን በተከሰተ የአውሮፕላን አደጋ የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ
በደቡብ ሱዳን ዩኒቲ ግዛት አነስተኛ አውሮፕላን ከግዛቷ ተነስቶ ወደ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ በማቅናት ላይ እያለ በደረሰበት አደጋ የ20 ሰዎች ህይወት አልፏል።
የግዛቱ ኮሙኒኬሽን ሃላፊ ጋትዌች ባይፓል በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት የቻይናው ብሔራዊ ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን እና የደቡብ ሱዳን መንግስት ተቋም የሆነው ናይል ፔትሮሊየም በጋራ የመሰረቱት ግሬተር ፐዮኔር ኦፕሬቲንግ ካምፓኒ ሰራተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከሞቱት መካከል ሁለት ቻይናውያን እና አንድ ህንዳዊ ዜጋ ይገኙበታል ያሉ ሲሆን ስለ አደጋው ምክንያት ተጨማሪ ዝርዝሮችን አላቀረቡም።
መጀመሪያ ላይ የሟቾች ቁጥር 18 ተብሎ ሪፖርት ቢደረግም ኋላ ላይ የሁለት ተጨማሪ ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ የሟቾች ቁጥር 20 መድረሱን ኃላፊው ለሮይተርስ ተናግረዋል።
ከአደጋው የመትረፍ እድል የገጠመው አንድ ሰው ብቻ መሆኑንም ነው አክለው የገለጹት።
ከዚህ ቀደም በደቡብ ሱዳን እ.ኤ.አ 2018 ከዋና ከተማዋ ጁባ ወደ ይሮል ከተማ የሚያጓጓዝ ትንሽ አውሮፕላን ተከስክሶ ቢያንስ 19 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።
Credit : Reuters
@tikvahethmagazine