በማሊ ህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ በደረሰ አደጋ 48 ሰዎች ሞቱ
ከአፍሪካ ወርቅ በማምረት ግንባር ቀደም በሆነችው በማሊ ህገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ በደረሰ የመሬት መንሸራተት 48 የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልፀዋል።
የአካባቢው ባለስልጣናት በአደጋው አብዛኞቹ ሴቶች በሆኑበት ቢያንስ 48 ሰዎች መሞታቸውን ገልጸው የሟቾች ቁጥር ግን ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል።
በጉዳዩ አሳሳቢነት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የአካባቢው ባለስልጣን “ሁኔታው በጣም አሳሳቢ ነው፤ አሁንም በህይወት ሊኖሩ የሚችሉትን ለማዳን የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ነው” ብለዋል።
ከዚህ በፊት በጃንዋሪ 30፣ በደቡብ ምዕራብ ማሊ በኩሊኮሮ በምትገኘው ዳንጋ መንደር ውስጥ መደበኛ ባልሆነ የማዕድን ማውጫ ላይ በደረሰ የመሬት መንሸራተት ቢያንስ 15 ሴቶች ህይወታቸው አልፎ ነበር።
ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎችም አፍሪካ ሀገት ወርቅ ለማውጣት በሚደረግ ጥልቅ ቁፋሮ አማካኝነት በሚደርስ አደጋ በርካታ ዜጎች ህይወታቸው ያልፋል።
@tikvahethmagazine