''በርካታ የልብ ታማሚዎች ወረፋ ሳይደርሳቸው ህይወታቸውን ያጣሉ '' - ዶክተር ፈቀደ አግዋር
በኢትዮጵያ የልብ ህክምና በተሟላ ሁኔታ እየተሰጠ የሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ በመሆኑ ወረፋ ሳይደርሳቸው ህይወታቸው የሚያልፉ የልብ ታማሚዎች መኖራቸው ይነገራል።
ዶክተር ፈቀደ አግዋር በኢትዮጵያ የልብ ህክምና ማዕከል ''የልብ ቀዶ ጥገና'' ሀኪም ናቸው። 800 የልብ ቀዶ ጥገና አድርገዋል። በሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ ደግሞ (HVE) 25 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ነፃ የልብ ቀዶ ጥገና ለ30 ታዳጊዎች ሰርተዋል። በተጨማሪም "የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ" የተሰኘ መጽሐፍም ለአንባቢ አበርክተዋል።
ዶ/ር ፈቀደ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሀራ በርሀ በታች ባሉ ሀገሮች ላይ በአሁኑ ሰዓት በተደጋጋሚ በሚከሰት ቶንሲል ምክንያት የሚፈጠር የልብ ህመም ከህፃናት እስከ አዋቂዎች ድረስ በከፍተኛ ሁኔታ ለልብ ህመም መፈጠር ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ።
በቅርቡ በሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ (HVE) የነጻ ህክምና ተጠቃሚዋ መሆን የቻለችው የ18 አመቷ ታዳጊም የልብ ህመሟ በቶንሲል ምክንያት የተከሰተ ሲሆን 4 ሰዓታት በፈጀው አንድ የግራ ልብ በር ቀዶ ጥገና በቶንሲል ምክንያት ክፋኛ የተጎዳው የታዳጊዋ የልብ በር በመቀየር የተሳካ ህክምና አድርጋለች።
የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና የሚሰጠው ደረት ተከፍቶ፣ ልብና ሳንባ ቁሞ፣ የደም ዝውውር ለማሽን ተሰጥቶ በመጨረሻም ልብ ተከፍቶ ህክምናው እንደሚሰጥና በዚህም ብዙ የህክምና ሂደቶችን እንደሚያልፍ ዶ/ር ፈቀደ ያስረዳሉ።
የልብ ህመም በተፈጥሮ ሊከሰት የሚችል ሲሆን በዓለም ላይ ''ከ1 ሺ ሰው 10 ሰው'' በተፈጥሮ የልብ ችግር ይኖርበታል ተብሎ ይታሰባል።
በሌላ በኩል ደግሞ በደም ግፊት፣ በስኳር በሽታ ምክንያትም የልብ ህመም እንደሚከሰት የልብ ሀኪሙ ዶክተር ፈቀደ ገልፀዋል።
አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የልብ ህክምና በተሟላ ሁኔታ የሚሰጠው በአዲስ አበባ በመሆኑ ለታማሚዎች ፈተና እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ተሳክቶላቸው ወረፋ ሲደርሳቸው በጣም ያረፈዱና የተወሳሰቡ ህክምና እንድንሰጥ እንገደዳለን ሲሉ ዶ/ር ፈቀደ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።
እንደ መፍትሔ . . .
በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ሁሉንም ነገር ያሟላ የልብ ህክምና የሚሰጠው ተቋም የኢትዮጵያ የልብ ህክምና ማዕከል እንደሆነ ዶ/ር ፈቀደ አግዋር ይናገራሉ።
ይህን ማዕከል አሳድጎ ትምህርት ቤት በማረግ ብዙ የልብ ህክምና ባለሙያዎችን በማፍራት በየከተማው፣ በየክልሉ እንዲሄዱ በማረግ ችግሩን መፍታት የሚቻልበት መንገድ ቢፈጠር ሲሉ ኃሳባቸውን ያቀርባሉ።
በተጨማሪም አሁን ላይ ማዕከሉ ያለውን አቅም አሳድጎ ብዙ የልብ ቀዶ ህክምናዎችንም እንዲሰራ ቢደረግ ለበርካቶች መድረስ እንደሚቻልም ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ የልብ ቀዶ ህክምና እና በደም ስር ገብቶ የሚሰራ የልብ ህክምና የሚሰጡት ቅዱስ ጳውሎስ፣ ጥቁር አንበሳና ኢትዮጵያ የልብ ህክምና ማዕከል መሆናቸውን ከኢትዮጵያ የልብ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine

"በሽዎች እሚቆጠሩ ሰዎች ወረፋ ይጠብቃሉ፣ወረፋ ሳይደርሳቸው በርካቶችም ህይወታቸውን ያጣሉ'' ብለዋል።
በመጨረሻም ተሳክቶላቸው ወረፋ ሲደርሳቸው በጣም ያረፈዱና የተወሳሰቡ ህክምና እንድንሰጥ እንገደዳለን ሲሉ ዶ/ር ፈቀደ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።
"ለአንድ የልብ ህመምተኛ ህክምና ለመስጠት በርካታ ባለሙያዎች፣ ብዙ ማሽን ጥቅም ላይ ይውላላል ከዚህ አንፃር በአሁኑ ሰአት በኛ ሀገር የልብ ህክምና ገና ጅማሮ ላይ ነው ማለት እንችላለን" ብለዋል።