🔈 #የነዋሪዎችድምጽ
° በዚህ ሳምንት በሸቀጣ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ባደረግነው ምልከታ ለመረዳት ተችሏል።
° የመርሳ ከተማ ነዋሪዎች የዋጋ ንረቱን በተመለከተ ከሰሞኑ ቅሬታ አቅርበዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ እና በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በዚህ ሳምንት በሸቀጣ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ባደረግነው ምልከታ ለመረዳት ተችሏል።
በአዲስ አበባ ፣ በደሴ እና በመርሳ ከተማ እንዲሁም በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ከዚህ ቀደም 1300 ብር ይሸጥ የነበረው አምስት ሊትር የምግብ ዘይት አሁን ላይ 1600 ብር እየተሸጠ ሲሆን ከዚህ በፊት ከነበረው የመሸጫ ዋጋ ከ200 መቶ እስከ 300 ብር ጭማሪ አሳይቷል።
እንዲሁም 1 ኪሎ ምስር ከ200 ወደ 280 ፣ እንቁላል ከብር 11 ወደ 19 ፣ 1 ሊትር ዘይት ከ285 ወደ 310 ብር ከፍ ያለ ሲሆን ሌሎች ምርቶች ላይ በአንድ ሳምንት ውስጥ የተጋነነ የዋጋ ጭማሬ መኖሩን በምልከታችን ወቅት ለማየት ችለናል።
በሌላ በኩል ደግሞ በአማራ ክልል ደሴ ከተማ 3 ሊትር ዘይት ከ 700 ወደ 900 ብር፣ 5 ሊትር ዘይት ከ 1300 ወደ 1550 ብር፣ አንድ ኪሎ ድንች ከ 40 ወደ 80 ብር በእጥፍ መጨሩን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከሰሞኑ የሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ ነዋሪዎች በየጊዜው በመሰረታዊ ፍጆታ ቁሳቁሶች ላይ የሚታየውን የዋጋ ጭማሪ መቋቋም አልቻልንም ሲሉ ቅሬታ አቅረበዋል።
በተጨማሪም ቅሬታ አቅራቢዎች በከተማዋ ያለውን የዋጋ ንረት በዝርዝር ያስረዱ ሲሆን " እስካሁን 5 ሊትር ኡመር ዘይት 1300 ብር ነበር የምንገዛው አሁን ግን 1600 ብር ነው ፣ አንድ ሊትር ዘይት 225 ብር እስካሁን እንገዛ የነበረው አሁን ላይ 330 ብር ደርሷል " ብለዋል።
አክለውም 50 ኪሎ ነጭ ዱቄት እስካሁን 4ሺህ 200 ብር እንገዛ ነበር ያሉት ነዋሪዎች አሁን ላይ ግን 4 ሺህ 600 ብር እየገዛን ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ያቀረቡት የመርሳ ከተማ ነዋሪዎች በየጊዜው በመሰረታዊ ፍጆታዎች ላይ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ ኑሮአቸውን ፈታኝ እንዳደረገባቸው ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ መፍትሄ የሚሰጠን አካል ካለ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ በፍጥነት እርምጃ ይወሰድልን ሲሉ ጥሪም አቅርበዋል።
የመርሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ሃላፊን አቶ አራጋው ተስፉ ምን አሉ?
የመርሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አራጋው ተስፉ ማህበረሰቡ የቀረበው ቅሬታ አግባብነት ቢኖረውም በዚህን ያክል የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ የለም ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም በከተማዋ እስካሁን የነበረው የዋጋ ንረት አሁን ላይ በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል ብለዋል።
በተጨማሪም በዚህ ወር በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ያነሱት ሃላፊው በመርሳ ከተማም በአንዳንድ ምርቶች ላይ ጭማሪ መኖሩን ጠቁመዋል።
ይሁን እንጂ ይሄ የዋጋ ጭማሪ በነጋዴዎች የመጣ ሳይሆን ምርቶችን ከሚያመርቱት ድርጅቶች ስለመሆኑ ገልፀዋል።
ሃላፊው ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር የዋጋ ጭማሪ የሚታይባቸውን መሰረታዊ ፍጆታዎች ለምሳሌ ጤፍ፣ ማሽላ ፣ ነጭ ዱቄት፣ ዘይት፣ ስኳር፣ ፖስታ፣ መኮረኒ እና የመሳሰሉትን የእለት ከእለት ፍጆታዎች ከተለያዩ ፋብሪካዎች በማስመጣት ለማህበረሰቡ በቀጥታ በማድረስ የገበያ ሥርዓቱን አረጋግተነዋል ብለዋል።
በመሆኑም ከዚህ በፊት የ1 ኪሎ ጤፍ ዋጋ ከ185 ብር በላይ ነበር፣ ከጥር ወር ጀምሮ ከ130 እስከ 140 ብር እየተሸጠ ነው። 50 ኪሎ ዱቄት ከፋብሪካው የሚወጣው በ4500 ብር ነው እኛ ጋር እየተሸጠ ያለው የትራንስፖርት ተጨምሮ ከ4550 እስከ 4600 ብር ነው።
ከዚህ በፊት የአንድ ኪሎ ማሽላ ዋጋ ከ 130 እስከ 150 ብር ነበር ያሉት ሃላፊው አሁን ላይ ከ60 እስከ 120 ብር እየተሸጠ ስለመሆኑ ገልፀዋል።
በመጨረሻም ሃላፊው በመርሳ ከተማ አሁን ላይ ከሁሉም የአማራ ክልል ከተሞች በተለየ ታላቅ የሆነ የዋጋ ቅናሽ መኖሩን አመላክተዋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine