ኤሲ ሚላን አሰልጣኙን አሰናብቷል !
የጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን ፖርቹጋላዊውን የቡድኑ አሰልጣኝ ፓውሎ ፎንሴካ ከሀላፊነታቸው ማሰናበቱን ዘ አትሌቲክ አረጋግጧል።
አሰልጣኝ ፓውሎ ፎንሴካ ባለፈው ክረምት ሊልን በመልቀቅ አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊን ተክተው ኤሲ ሚላንን በሶስት አመት ኮንትራት መረከባቸው ይታወሳል።
አሰልጣኙ ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላ 1ለ1 ከተለያዩበት ከትላንት ምሽቱ የሮማ ጨዋታ በኋላ ከሀላፊነታቸው ተሰናብተዋል።
ኤሲ ሚላን በምትኩ አሰልጣኝ ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ በሀላፊነት መሾማቸው ሲገለፅ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ተነግሯል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe