የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአየር ላይ የታክሲ አገልግሎት ሊጀምር ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ Archer ከተሰኘና መቀመጫውን አሜሪካ ካደረገ ድርጅት ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አየር ላይ ታክሲ አገልግሎት ሊሰጥ ነው።
በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው ይህ አገልገሎት ለዜጎች ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ የትራንስፖርት አገልግሎት ከመፍጠር እና ጊዜን ከመቆጠብ ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው ተገልጿል።
ለዚህ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉት eVTOL ወይም electronic vertical take-off and landing የተሰኙ የአየር ላይ ተሽከርካሪዎች ሲሆኑ እነዚህም ከአውሮፕላኖች በተቃራኒ ለማረፍና ለማኮብኮብ ትንሽ ቦታ ብቻ ይበቃቸዋል። ከሂሊኮፕተር ጋር አንዳንድ ተመሳሳይነት ቢኖራቸውም ከሂሊኮፍፕተር አንፃር አነስተኛ ድምፅ በመኖራቸው እና በተለያየ ምክነያቶች ገበያ ላይ ተፈላጊነታቸው ጨምሯል።
ዘገባውን ያወጣው የairspace Africa የተሰኘ ድረገፅ ነው።