ስማርት ስልኮቻችን ቻርጅ እንዴት መሙላት አለብን…?በርካታ ተግባራትን የሚያከናውኑበት ስማርት ስልክዎ ባትሪ በፍጥነት እያለቀ ተችገረዋል?
✴️ የተለያዩ ስልቶችን ተጠቅመው የስልክዎን ባትሪ ቢያንስ ሙሉ ቀን እንዲያስጠቅምዎትስ ጥረት አድርገዋል?
✴️በቴክኖሎጂው መስክ የተሰማሩ ባለሙያዎች የስልካችን ባትሪ በፍጥነት እያለቀ የምንቸገረው በሶስት ምክንያቶች መሆኑን ይገልፃሉ።
✴️የመጀመሪያው በስማርት ስልኮቻችን የጫንናቸው መተግበሪያዎች መብዛት እና እያወቅንም ይሁን ሳናውቅ ተከፍተው ባትሪ መብላታቸው
ነው።
✴️የስማርት ስልካችን ላይ ሙጭጭ ብለን አልላቀቅ ማለትም ሌላኛው የባትሪ እድሜን የሚያሳጥር ልማድ ነው።
✴️ሶስተኛው እና ዋነኛው የባትሪ ህይወትን የሚያሳጥረው ተብሎ በባለሙያዎች የተጠቀሰው ደግሞ የሀይል አሞላላችን (ቻርጅ አደራረጋችን መሆኑ ተገልጿል።
✴️ብዙዎቻችን የስማርት ስልካችን ባትሪ ሙሉ በሙሉ ሲያልቅ ቻርጅ ማድረግ እንዳለብን እናምናለን።
✴️በአንዳንዶቻችን ዘንድ ደግሞ ቻርጅ እንደሰካን ሞባይላችንን መጠቀም የባትሪውን አገልግሎት ያራዝማል የሚል አመለካከት አለ።
✴️ይሁን እንጂ የሞባይል ባትሪ እንደ ሰው ልጅ ሁሉ “መጨናነቅን” አይወድም ነው የሚለው ባትሪ ዩኒቨርሲቲ የተሰኘ ኩባንያ።
✴️ስልካችንን ቻርጅ እያደረግን መጠቀም የባትሪውን እድሜ ያሳጥራልም ይላል።
✴️ስለ ስማርት ስልክዎ ባትሪ ከመጨነቅ የሚገላግሉ ናቸው ያላቸውን ነጥቦችም ባትሪ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች አስቀምጧል።
✴️የስልክዎ ባትሪ ሙሉ ቻርጅ ከተደረገ በኋላ ሞባይሉን ከቻርጀሩ ይንቀሉት፡
✴️ኩባንያው እንደሚለው የስማርት ስልካችን ባትሪ ከአቅሙ በላይ ቻርጅ ሲደረግ የረጅም ጊዜ አገልግሎቱ እየወረደ ይመጣል።
✴️ስልካችን 100 ፐርሰንት ቻርጅ ከሆነ በኋላ እንደተሰካ መተው ለከፍተኛ መጨናነቅ በመዳረግ የባትሪውን ሀይል የመያዝ አቅም ይቀንሰዋል።
✴️ (እስከ 100 ፐርሰንት ቻርጅ ማድረግም ለመጀመሪያ ጊዜ ካልሆነ አስፈላጊ አይደለም፡
ከአድካሚ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በኋላ ጡንቻዎችን ማፍታታት እንደሚገባ ሁሉ ስልካችንም ሙሉ በሙሉ በሀይል ከተሞላ በኋላ ከቻርጀሩ መንቀል ይገባል።
✴️ባትሪውን ከሙቀት ይጠብቁት
የስማርት ስልክ ባትሪዎች በቀላሉ በሙቀት ይግላሉ።
✴️ለዚህም ነው አፕል ራሱ የአይፎን ስልኮችን ቻርጅ ስታደርጉ መሸፈኛ (ኬዞቹን ብታወጡት በማለት የሚመክረው።
✴️ስለሆነም ስልካችን ቻርጅ ስናደርግ መሞቁን ካስተዋልን ሽፋኑን ማውጣት ይኖርብናል።
✴️የባትሪያችን ጤና ለመጠበቅ ስማርት ስልካችን ቻርጅ የምናደርግበት አካባቢ የፀሀይ ሙቀት የሌለበት ቢሆንም ጥሩ ነው።
✴️100 ፐርሰንት ላይ እስከሚደርስ መጠበቅ የለብንም፡
✴️እንደ ባትሪ ዩኒቨርሲቲ ገለፃ ከሆነ ከፍተኛ ቮልቴጅ ባትሪውን ስለሚያጨናንቀው ባትሪን መቶ በመቶ ሀይል መሙላት አያስፈልግም።
✴️ስማርት ስልካችን ቀኑን ሙሉ ቻርጅ ማድረግም በባትሪው እድሜ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ብሏል።
ቻርጅ ለማድረግ የባትሪውን ማለቅ አይጠብቁ።
✴️ ስልካችን ቻርጅ ለማድረግ ባትሪው ተሟጦ እስኪያልቅ መጠበቅ የለብንም።
✴️ ባገኘነው አጋጣሚ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን ሀይል ይዞ የመቆየት አቅም ያሳድገዋል።
✴️እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ስልቶች የስማርት ስልካችን ባትሪ ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግል እና ቀኑን ሙሉ ከስጋት ነፃ እንድንሆን ይረዳል።
t.me//tip_4u