#Update
🔔 ለትሬኒ ባንከር የሥራ መደብ አመልካቾች!
ፀሐይ ባንክ አ.ማ. በትሬኒ ባንከር የሥራ መደብ ባወጣው የሥራ መደብ ለጽሑፍ ፈተና እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ አመልካቾች በሙሉ፦
የመጨረሻ ዙር በአካል የጽሑፍ ፈተና የሚሰጠው ቅዳሜ ታህሳስ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በመሆኑ፤ አዲስ አበባ ለመፈተን የመረጣችሁ አመልካቾች መስቀል አደባባይ በሚገኘው ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት ፈተናው የሚሰጥ ሲሆን፤ ባህር ዳር ለመፈተን የመረጣችሁ ተፈታኞች ደግሞ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሚገኘው ዊዝደም ህንፃ ከሰዓት ከ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ፈተናው ይሰጣል፡፡
ማሳሰቢያ
➫ ለመፈተን በምትመጡበት ጊዜ ራሳችሁን የሚገልጽ መታወቂያ እና የምትፈተኑበት ሰማያዊ ስክርቢቶ እንድትይዙ እናሳስባለን፡፡ ከመታወቂያ እና ከስክርቢቶ በስተቀር ማንኛውም ንብረት (ስልክ፣ ካልኩሌተር፣ ቦርሳ፣ መጻሕፍት፣ ወረቀት፣ ወዘተ …) ወደመፈተኛ ቦታ ይዞ መግባት የተከለከለ መሆኑን እናሳወቃለን፡፡
➫ ፈተናው ልክ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ስለሚጀምር ተፈታኞች በሙሉ መታወቂያቸውን በመያዝ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ላይ በመፈተኛ ቦታ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡ ፈተናው ከተጀመረ በኋላ ወደመፈተኛ ቦታ መግባት አይፈቀድም፡፡
➫ ስማችሁ ከዚህ መልዕክት ጋር ከተያያዘው የተፈታኞች ስም ዝርዝር ውጪ የሆነ ማንኛውንም አመልካች የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን፡፡
ፀሐይ ባንክ
ለሁሉ!