👉 ሀገሪቷን ማን በየትኛ ህግ ነው የሚያስተዳድራት ?
ሀገራችን ኢትዮዽያ የምትመራበት ህገመንግስት አንቀፅ 27 የዜጎች የእምነት ነፃነትን ያውጃል ። የዜጎች ሲባል እየአንዳንዱ ዜጋ ማለት ነው ። ይህ ማለት አንድ ሰው የፈለገውን እምነት የመቀበል ፣ እምነቱ የሚያዘውን ነገር የመተገብር መብቱ ማንም ሊነጥቀው የማይችል ወይም በማንም መልካም ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ አለመሆኑና ይልቁንም የዜግነት መብቱ መሆኑን ነው የሚያሳየው ።
በሀገራችን በየትኛውም ደረጃ ያሉ ክልሎችም ይሁን ዞንና ወረዳዎች በዚህ ህገመንግስት ስር ሆነው ነው ክልላቸውን ወይም ዞንና ወረዳቸውን ማስተዳደር ያለባቸው ። ከላይ ያየነው አንቀፅ የአንድን ግለሰብ መብት የሚያስጠብቅ ከሆነ በሺዮች ወይም በመቶ ሺዮች የሚቆጠሩ ዜጎች ሲሆኑ ደግሞ ምን ሊሆን እንደሚችል ግልፅ ነው ። ማንም ተነስቶ የግለሰብን እንኳን ህገመንግስታው መብት የሚጥስ መመሪያ ማውጥት የማይችል ከሆነ የህዝቦችን መብት የሚጥስ መመሪያ ማውጣት አለመቻሉ ከበጋ ፀሀይ የበለጠ ግልፅ ነው ማለት ነው ።
የህገ መንግስቱ መመሪያ ይህ ከሆነና መንግስት የሚሰራው በዚህ ከሆነ በምን ሒሳብ ነው ይህን የህዝቦች መብት ያረጋግጣል የተባለውን መመሪያ አሻፈኝ ብሎ ይህን የሚፃረር መመሪያ ስራ ላይ በማዋል የዜጎች መብት የሚረገጠው ?
በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን ላይ በተለያዩ ክልሎች በግልፅ ይህን ህገመንግስታዊ የዜጎች መብት በጣሰ መልኩ የራሳቸው ህግ በማርቀቅ መብት የሚረግጡ መኖራቸው የአደባባይ ሚስጢር እየሆነ ነው ። ለመሆኑ እነዚህ አካላት ህገ መንግስቱ እኛን አይወክልም የራሳችን ህገመንግስት አለን ባዮች ናቸው ወይስ ከህገ መንግስቱ ውስጥ ለኛ የሚስማማውን ወስደን የማይስማማውን እንተወዋለን ማን ምን አገባው ባዮች ናቸው ? ወይስ ጠያቂ የለም ነው ነገሩ ። ለማንኛውም እንዲህ አይነት ፅንፈኝነት ለማንም አይጠቅምም ።
የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ማንኛውም ተማሪ ሀይማኖትን የሚያንፀባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም በሚል ሙስሊም ሴት ተማሪዮችን ሒጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት እዳይገቡ መከልከሉ ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም እንደሚሉት ነው ። ለመሆኑ እነዚህ አካላት አንገታቸው ላይ ክር አስረው ክርስቲያን መሆናቸውን የሚገልፅ ነገር ያደረጉትንም ጭምር ነው ያባረሩት ወይስ የሙስሊሞችን እስልምና የሚገልፅ ነገር ነው ወንጀል የሆነው ? ለመሆኑ በትግራይ ክልል እንደ አፄዎቹ ዘመን የሙስሊም ኮፍያ መልበስም ወንጀል ነው ? በአክሱም ከተማ እስልምናን የሚገልፅ ነገር እንደ ኮፍያ ፣ ሒጃብ ፣ ጅልባብና የመሳሰሉ መገለጫዎችን የሚያደርጉ ሙስሊሞች አይደለም በሴክተር መስሪያ ቤት ሊሰሩ ለጉዳይም መግባት አይችሉም ሊሉ የሚፈልጉ ይመስላል ።
የሚገርመው በሒጃብ ዙሪያ እንደሀገር ሙስሊም ሴት ተማሪዮች ከዩኒፎርም ጋር የሚመሳሰል ሒጃብ ለብሰው መማር የሚችሉ መሆኑን የሚገልፅ መመሪያ እንደ ኢትዮዽያ አቆጣጠር በ2000 ወጥቶ በስራ ላይ የዋለ መመሪያ አለ ። ይህ ከህገመንግስቱ የፈለገችውን የመልበስ መብት ማረጋገጥ በተጨማሪ ማለት ነው ። ታዲያ የአክሱም ከተማ ፅንፈኞች ለየትኛው ህግ ይሆን የሚገዙት ? ወይስ የኋሊዮሽ ተመልሰው የአፄዎቹ ዲስኩር መንዛት ነው የተያያዙት ?
በአሁኑ ጊዜ የዜጎች መብት መረገጥ በሌሎችም የእምነት ተቋማትም እየታየ ነው ። ከላይ የተጠቀሰውን አንቀፅና እንዲሁም ማንኛውም ዜጋ ለህጋዊ አላማ የመደራጀት መብቱ የተጠበቀ ነው የሚለውን የህገ መንግስቱ አንቀፅ 32 እንዲሁም መጅሊሱ በአዋጅ ሲፀድቅ ከዚህ በፊት የተቋቋሙ ወይም የተደራጁ ማህበራትን መከልከል አይችልም የሚለውን አዋጅ በመፃረር የአሁኑ የመጅሊስ አመራሮች በቁርኣንና ሀዲስ ሳይሆን በራሳቸው ልብ ወለድ የሚመሩት መጅሊስ ስር ያልሆነን ዜጋ አይደለም እስከ ማለት ደርሰዋል ።‼ እነዚህን ከላይ የተገለፁ የዜጎችን መብት የሚረግጡ መመሪያዎችን የሚቃረን መመሪያ በማውጣት ይህን ተቀብሎ ተግባራዊ የማያደርግ በዚህች ሀገር መኖር አይችልም ሀገሩን ይፈልግ እስከማለት ደርሰዋል ።
ይህ ነው ይህች ሀገር ማን በየትኛው ህግ ነው የሚያስተዳድራት የሚል ጥያቄ የሚያስነሳው ። ዜጎች በጣም በሚገርም ተስፋ የጠበቁት ብልፅግና እንደነዚህ አይነት ተግዳሮቶችን በመዋጋት ወረቅት ላይ ያሉትን ፍትህ የናፈቃቸው ቃላት መሬት ላይ ወርደው ስራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ የመጀመሪያ ተግባሩ ሊሆን ይገባል እላለሁ ።
ፍትህ ለአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዮች ።
https://t.me/bahruteka