ቅድመያ ለተውሒድ ቦታ ስጥ !!abdul menan emam


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ኢብኑል ቀይም ( ረሒመሁላህ ) እንዲህ ይላሉ ፦ ቀልብ ከአላህ ተውሒድ ከተራቆተ ይደርቃል ።( አስራሩ ስሶላት ፡ 1/3 )
Tewhid the first

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


አዲስ ሙሃዶራ

ርእስ:- የሰዎች ክብርና ግርማ ሞገስ ሐቅን ከመናገር አይከለክልህ!!

🎙በሸይኽ አቡ ዘር (ሀፊዘሁላህ)

በስልጤ ዞን አሊቾ ወረዳ ኮንፈረንስ ላይ በቀጥታ ስርጭት ያስተላለፉት

🗓 ረጀብ 19/1446 ዓ.ሒ

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


ሐቅን የማጠልሸት ዘመቻ
--------------------------------------

🎙 آلأُسْتَاذ بَحْرُو تَكَا أَبُو عٌبَيْدَة «حَفِظَهُ الله»
🎙 በኡስታዝ ባህሩ ተካ አቡ ዑበይዳህ አላህ ይጠብቀው!


🏖 ❝ እነርሱ ጠይዎች ሲኾኑ እውነቱ እስከመጣና የአላህም ትዕዛዝ እስከተገለጸ ድረስ ከዚህ በፊት ሁከትን በእርግጥ ፈለጉ፡፡ ነገሮችንም ሁሉ አገላበጡልህ፡፡❞
   📚 [አት-ተውባ]

🏝 በአሊቾ ዊሪሮ ወረዳ በገደራት ቀበሌ ልዩ ስሙ ጮል በተሰኘችው መንደር በአል-አቅሳ መስጂድና መድረሳ የቀረበ

🗓
እለተ-ቅዳሜ [ጥር 10/2017]

t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy


👉ለሚስትህ የሚከሉትን ሁንላት!
     ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

1ኛ ፍቅርህን አክብሮትህን ለሷ ያለህን ቦታ ምኞትህን ወዘተ በተግባርም በቃልህም ግለፅላት!

2ኛ ከየትኛውም አካል የበለጠና የተሻለ አቀራረብ ቅረባት፤ የደስታዋም ሆነ የሀዘኗ የመጀመሪያ ተካፋይ ሁን!

3ኛ በአንተ እርግጠኛ እንድትሆን አድርጋት፣ ሁሌም የኔ ነው፤ ከጎኔ ነው የሚል ስሜት እንድሰማት ማድረግ አለብህ!

4ኛ ግልፅ ሁንላት የምታስበውን፣ የምታደርገውን በቃ የትኛውንም እንቅስቃሴህን ግልፅ ሁነህ አሳውቃት በአንተ እርግጠኛ ትሆናለችና

5ኛ ቃል የምትገባላትን ነገር በተግባር አሳያት ሴቶች ወሬው ከተግባሩ የሚቀድም ወንድ አይወዱም። ስለዚህ የምትችለውን ቃል ገብተህ ፈፅመህ አሳያት!

6ኛ ቋሚ የሆነ ሁኔታ ይኑርህ ማለትም ስትፈልግ አትዝጋት ስትፈልግ አትቅረባት፣ የእውነት ከፈለካት  ቋሚ ደስ የሚል ባህሪ ይኑርህ፤ ያኔ በቀላሉ መግባባት ትችላላችሁ!

7ኛ ጨዋ ሁንላት በዙሪያዋ ያሉ ሰዎችን አክብርላት ውደድላት፤ የኔ ባል ከሁሉም የበለጠ ምስጉን ጨዋ እና ክቡር ነው በማለት እስከምታምን ድረስ ተስተካከልላት!

8ኛ ትእግስተኛ ሁንላት ስትቆጣ አትቆጣ ወንድ ነኝ አትነጫነጭ የሚል ሁኔታ አይኑርህ ተረዳት፤ በተለይ በወር አበባ በእርግዝና እና በህመም ወቅቶች የተለየ ባህሪ ብታሳይህም ግን አንተ ታጋሽ ሆነህ ስሜቷን ተገንዘብላት ሲሻላት በጣም ታከብርሃለችና

9ኛ ነገሮችን ተቆጣጣሪ ሁን፤ ዝርክርክነት መለያህ እንዳይሆን ቤትህን ሚስትህን ገንዘብህን ጊዜህን እውቀትህን ወዘተ በአግባቡ ተቆጣጠር። ባሌ ካለ ምንም የሚዛባ ነገር አይኖርም እስከምትል ተቆጣጣሪ ሁን

10ኛ አክብራት ማለትም ሀሳቧን ስትነግርህ አክብርላት ሀሳቧ ስህተት እንኳን ቢሆን አዳምጣት፣ አትሳለቅባት፤ አትሳቅባት፤ እንደውም አበረታታት በሀሳቧ እንዲትሸማቀቅ ሳይሆን እንድትኮራ አድርጋት። ሀሳቧን ማክበር እሷን ማክበር ነው። ሀሳቧን መንቀፍ እሷን መንቀፍ ነው። ስህተት ከሆነም በአግባቡ አስረዲተህ ግን አደናንቀህ እለፋት!

11ኛ ማንነቷን ተቀበልላት ደካማ ጎኖቿን መነሻ አድርገህ የትችት አውድማ አታድርጋት ክፍተቶቿን እንዲታስተካክል አግዛት እንጂ አታዋርዳት!

12ኛ ቆንጆ እንደሆነች ንገራት ከእርሷ ውጭ ማንንም እንደማትፈልግ ንገራት አሳያት፤ የምትተማመንብህና የምትወዳት መሆኖኑን እስከምታምን ተንከባከባት!

13ኛ ደስተኛ አድርጋት ባላችሁ ነገር ደስተኛ ሁኑ። ብዙ ሀብት ግደታ አይደለም ለምሳሌ ስጦታ በመግዛት፣ 5 ብር ከረሜላም እንኳ ቢሆን ዋናው አንተ እሷን ማሰብህ ነው።

14ኛ ወሬዋን ጆሮ ሰጥተህ እንድትሰማት ትፈልጋለች። ስለዚህ ልታወራህ ስትል አፍ አፏን አትበላት ተዋት ታውራህ! ልታስቅህ ከፈለገች ባያስቅህም ሳቅላት። ሀሳቧን አታቋርጣት አታስደንግጣት። ጊዜ ሰጠህ ስታዳምጣት ትልቅ ቦታ እንደሰጠሃት ትረዳሃለች!

15ኛ በአጠቃላይ ለሚስትህ ጥሩ ባል መሆንህ እሷም ጥሩ ሚስት ትሆንልሃለችና ትኩረት ስጥ! ከላይ የተጠቀሱልህን በመተግበር ስኬታማ የትዳር ህይወት ኑሩ!!!

⚙ ከተወሰነ ማስተካከያ ጋር የቀረበ
https://t.me/AbuImranAselefy/9605

▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴
⚙ 📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

---------------⫷⫸-----------------
🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
⫷⫸⫷~⫸⫷⫸⫷~⫸⫷⫸⫷~⫸


🔷 በዚ ዘመን ነው እንዴ የሚያሰኝ ታሪክ

በሶሞኑ የሓራና ሀሮ ጉዞዬ በጣም የሚገርምና በሐዘንና የአድናቆት የተደበላለቀ ስሜት የእንባ ቧንቧ የሚከፍት እውነተኛ ታሪክ ሰምቼ ላካፍላችሁ ወደድኩኝ ። ታሪኩንም እንደሚከተለው አቀርብላችኋለሁ : –
ክስተቱ በወሎ ዞንተንታ በምትባለው የሀገራችን ክፍል የተከሰተ ነው ። እንደሚታወቀው ሀገራችን ውስጥ በተለያዩ ክልሎች የተለያዩ የሽርክ አይነቶች ይሰራሉ ። ሽርክ ደግሞ ደረካቱ ይለያያል ። የሽርክ አይነቶች ሁሉ እኩል አይደሉም ። በጣም አሰከፊ የሽርክ አይነት ከሚካሄድባቸው አካባቢዮች አንዱ የወሎ ዞን ነው ። ወሎ አካባቢ የሽርክ ኮተትና ግሳንግስ ሲሆን የሚሰሩ የሽርክ አይነቶች የህፃናት ፀጉር የሚያሸብቱ ናቸው ። ሽርክ መሰራቱ ብቻ ቢሆን ባልከፋ ነበር ነገር ግን እነዚህ የሽርክ ተግባር የሚሰሩ አካላት ከእነርሱ ጋር አብሮ ያልሰራን ወሀብይ በሚል የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ ባይተዋር እንዲሆን ማእቀብ በመጣል ራሱን እንዲጠላ ያደርጋሉ ።
የዘህ ግፍና በደል ገፈት ቀማሽ ከሚሆኑት የአላህ ባሮች ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ደቡብ ወሎ ተንታ በምትባለዋ መንደር ውስጥ ነዋሪ የሆኑት ሸይኽ አሕመድ ዐ/ወሀብ አንዱ ናቸው ። እኝህ ሸይኽ ሽርክን በአይነቱ አውግዘው አድባር ቆሌ አልገዛም ፣ የሙታንን መንፈስ አልለማመንም ፣ ፍጡርን ድረሱልኝ ብዬ ከጌታዬ ደጃፍ መባረር አልመርጥም ፣ በቂዬ አላህ ነው እሱን ብቻ ነው የማመልከው ፣ የምከጅለውና የምለምነው ፣ ከጭንቅ አውጣኝ ፣ ተምኪን ፈልጌያለሁ ብዬ እጄን ምዘረጋው ወደርሱ ብቻ ነው በማለታቸው ከአካባቢ ማህበረሰብ እንዲገለሉ ተደረጉ ። በዚህ አላበቃም ማእቀቡ ቢታመሙም ቢታመምባቸውም እንዳይጠየቁ ፣ ቤተሰባቸውም ሆነ እሳቸውም ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ፣ ቢሞቱ እንዳይቀበሩ ፣ ቢሞትባቸውም እንዳይቀበርላቸው ፣ ምንም አይነት ችግር ቢገጥማቸው ማንም እንዳይረዳቸው ተወሰነባቸው ።
ይሁን እንጂ እኚህ ሸይኽ ከማህበሰቡ የተጣለውን ማእቀብ ከቁብ ሳይቆጥሩ ልጆቻቸውንና ባለቤታቸውን ይዘው በማህበረሰቡ የተወገዙና የተረገሙ እየተባሉ አላህ በቂያችን ነው ብለው የህይወትን ጉዞ ጀመሩ ። ይህ ሲሆን የሱና ሰዎችን ለማግኘት ደርሶ መልስ የ6 ሳአት መንገድ የሚሆን ቦታ ሄደው እየመጡ የባይተዋርነት ስሜታቸውን እያቀጨጩ ነበር ።
እኚህ ጉደኛ ሸይኽ አላህ ይህን ፅናታቸውን የሚፈታተን ፈተና እንዲገጥማቸው ፈለገ ። ልቻቸው በጠና ታመመ ። ልጃቸውን ሐኪም ቤት አስገብተው ያለ ጠያቂና ያለ ተተኪ ሲያስታምሙ ቆዩ ። የአላህ ውሳኔ ሆነና ልጃቸው ወደ አኼራ ሄደ ። ቤታቸው ከሐኪም ቤቱ በእግር የ3 ሳአት መንገድ ያስኬዳል ። መኪና ለመከራየት አቅም አልነበራቸውም ። አብሽር ብሎ የሚያፅናና ቤተሰብም ሆነ ጎረቤት አጠገባቸው የለም ። የልጃቸውን ጀናዛ ተሸክመው የሶስት ሳአት መንገድ ተጉዘው ቤታቸው ደረሱ ። እናትና አባት የልጃቸውን ጀናዛ አጥበው ከፍነው ተሸክመው ወስደው ቀበሩ ።‼ሱብሓነ ላህ ለስሙ በሙስሊም ማህበረሰብ ውስጥ ነው ያሉት ነገር ግን አላህ በቂያችን ነው እንዴት ትላላችሁ ተብለው በዚህ መልኩ ታሪክ የማይረሳው አላህ ፊት አሳፋሪ የሆነ ተግባር ተፈፀባቸው ።
እኚህ ጉደኛ አባትና እናት ልጃቸውን ቀብረው ተመልሰው አላህ በቂያችን ነው ይህ ለተውሒድ ከሚከፈል ዋጋ አንፃር ኢምንት ነው አሉ ። አላህ የፈለገውን ይሰራል ልጃችንን እኛ ቀብረነዋል ሁላችንም ሞተን ሬሳችን አውሬ ቢበላውም አላህን ከማምለክ ሊያግደን የሚችል አይኖርም ይላሉ ።
ከዚህ መራራ ፈተና በኋላ ግን ሶብራቸውና ፅናታቸው ፍሬ አፍርቶ ትላልቅ መሻኢኾች እንደነ ሸይኽ ኢስማኢል ፣ ሸይኽ ዐ/ ሰመድ ፣ ሸይኽ ሙሐመድ ሓያትና ሌሎችም ወደ ተውሒድ ተመልሰው በአሁነ ሳአት ተንታ አካባቢ በሸይኽ ኢስማኢል አማካይነት የተውሒድና ሱና ዳዕዋ እየተስፋፋ ነው ። ኪታቦች ይቀራሉ ፣ ሙሓደራዎች ይደረጋሉ ፣ ልጆች ተውሒድና ሱና ይማራሉ ፣ ባጠቃላይ የሰለፍያ ዳዕዋ ችግኝ እያበበ ነው ።
ይህ የሆነው በተጣለባቸው የግፍ ማእቀብ ለ30 አመት አካባቢ በፅናት የታገሉት ሸይኽ አሕመድ ዐ/ወሃብ በህይወት እያሉ ነው ። በአሁኑ የሓሮ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ እንደሚመጡ ሸይኽ ሙሐመድ ሓያት ደውለው ከነገሯቸው በኋላ ጉዳይ ገጥሟቸው መጥተው ለማየት ሳንታደል ቀርተናል ። እስኪ ይህን ታሪክ የምናነብ ወደራሳችን እንመልከት እኛ ለነብዩ ዲን ምን የከፈልነው ዋጋ አለ ? አላህ ይዘንልን ።

https://t.me/bahruteka


ወሳኝ ጣፋጭ እና አንገብጋቢ ሙሓደራ

=========================

ርዕስ :- ሰዎች ለምን መንሐጀ ሰለፍን ይዋጓታል ??

💫ከተዳሰሱት ነጥቦች መሃል

✔️ ከሰለፍያ መንሓጅ ሰዎችን ለማስበርገግ ለሰለፊዮች ሌላ ስም ስለመለጠፍ ለምሳሌ ጉላቱል ጀርህ ፣ መድኸሊያ ፣ ሙተሰሪዓዎች ስለማለት

✔️ ስለ ጀርህ ወተዕዲል በሰፊው ተዳስሶበታል

✔️ ጀርህ ወተዕዲል ፈርዕ ሳይሆን ዋና ወይም ኡሱል እና አስኳል ነው

✔️ ጀርህ ወተዕዲል ዋና መሆኑን ለማፈን የሚጥሩ ብዙ ሰዎች ስላሉ...!!

✔️ ጀርህ ወተዕዲል መሽሩዕ ለመሆኑ ከቁርዓን ከሃዲስ ማስረጃ

✔️ አንድን ሰው በአደባባይ ሳታዋርዱት መጀመሪያ ለምን በውስጥ አትመክሩትም ለሚሉት ቆራጭ ምላሽ

✔️ ጀርህ ወተዕዲል ኢጅቲሃዲይ ነው ስለሚሉ ሰዎች

✔️ ጀርህ ወተዕዲል ሚን ባቢል አኽባር ነው ተነገረህ ተቀበል !!! አለቀ ኢጅትሃድን የሚቀበል ርዕስ ሳይሆን ከተነገረህ መቀበል ብቻ ነው ግዴታህ !!

✔️ ሰለፊዮችን ሙተሸዲዶች ናቸው እያሉ ሹብሃ ስለመርጨት

✔️ ለሰዎች ማስረጃ ይፈለግላቸዋል እንጂ ማስረጃ አይደረጉም

✔️ ሰለፊዮች ፊቅሃል ዋቂዕን አያውቁም ?

🎙 ሸይኽ አቡዘር ሐሰን ሀፊዘሁሏህ

👌እሁድ በቀን 29/5/2014 ከሚሴ በኢብኑ አባስ ወይም ጀርህ ወተዕዲል ኢጅቲሃዲይ ነው በሚለው በኸዲር ከሚሴ መድረሳ የተደረገ ወሳኝ ሙሓደራ

👌 ሃቅ ሃቅ ነው ምናልባት ይህ ውብ ሙሓደራ እንዳይሰራጭ ፈልገው ከፊል ሰዎች የደበቁት ቢሆንም ሃቅ ፈላጊዎች ሁላችሁም ሼር አድርጉት ባረከላሁ ፊኩም

     👇👇

@UstazAbuzarhassenAbutolha
@UstazAbuzarhassenAbutolha
@UstazAbuzarhassenAbutolha


Репост из: የ ሸይኽ ሙሐመድ ሀያት ቻናል
✅  ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በሃሮ ከተማ

      ውድ የሱና ቤተሰቦቻችን የነብያት ውርስ የሆነው የተውሒድ ዳዕዋ በሰሜን ወሎ የነብያት አደራ ተረካቢ በሆኑ መሻኢኾች እያበበና አድማሱን እያሰፋ መሆኑ ይታወቃል ። አሁን ደግሞ የፊታችን እሁድ ታህሳስ 27/04/2017 በሀሮ ከተማ የተውሒድን ችግኝ ለመትከል ቀጠሮ ተይዟል ። በዚህ ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም ላይ ከሰሜን ወሎ መሻኢኾች በተጨማሪ ሌሎች መሻኢኾችና ኡስታዞች ይካፈላሉ ።
     እነማን ካላችሁ የሚከተሉት ይገኙበታል ።

1 – ከስልጤ ዞን ሸይኽ ዐ/ሐሚድ አልለተሚ
2 – ከወልቂጤ   "  "  ሙባረክ ሑሰይን
3 – ከኮምቦልቻ  "  "  ሙሐመድ ጀማል
4 – ከሓራ          "  "    ሙሐመድ ሐያት
5 –  "  "            "   "    ሑሰይን ከረም
6 –  ከተንታ        "  "    ኢስማኢል ዘይኑ
7 –  ከወርቄ       "   "   ሑሰይን ዐባስ 
8 –  ከሃሮ          "    "    ሙሐመድ ስራጅ
9 —  ከሓራ        "   "      ሰዒድ ሙሐመድ
10 – ከኮምቦልቻ ኡስታዝ  ሙሐመድ ኑር
11 – ከአ/አ        "    "     ኡስታዝ ባሕሩ ተካ
12 – ከባሕር ዳር "   "    አቡ በከር
13 – ከመርሳ      "   "       ዐ/ራሕማን
14 –  ከኮምቦልቻ "   "      ኸድር ሐሰን
15 – ከመርሳ       "   "    ኑር አዲስ
16 –  ከሓራ         "   "    ሙሐመድ ሰልማን
17 – ከሸዋሮቢት  "   "    ሙሐመድ አሚን

      በዚህ ፕሮግራም ላይ የሃሮ አልፉርቃን መስጂድን ለማቋቋሚያ የሚሆን ተጨማሪ ፕሮግራም ይኖራል ። በመሆኑም የሱና ቤተሰቦች በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በመሳተፍ  አሻራችሁን አኑሩ ይላል ጀማዓው ።

     ለሴቶች በቂ ቦታ ተዘጋጅቷል እንዳታስቡ ።

አላህ ካለ ፕሮግራሙ የሚጀመረው
          ከጠዋቱ  2 : 30 ይሆናል ።
     የእሁድ ፕሮግራማችን ከነቤተሰባችን ሃሮ ፉርቃን መስጂድ እናድርግ ።

   ለበለጠ መረጃ : –
     ስልክ ቁጥር     0920474161
                           0929732296
0935212614

https://t.me/hussenhas

https://t.me/heroselefi


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


👉 በሙስሊምነትህ አትፈር

ወንድሜ አላህ በባሮቹ ላይ ከዋለው ፀጋ ወደር የሌለው የእስልምና ፀጋ ነው ። ይህን የሚያውቀው ከኩፍር ፅልመት ወጥቶ ወደ ኢስላም ብርሃን ተሸጋግሮ በአይነ ህሌናው ያለፈውን ፅልመት እያየ የሰራ አካላቱ ከሚወረው አስፈሪ ጭንቀት ራሱን በኢስላም ብርሃን ላይ የሚያገኝ ሰው ነው ። በዚህን ጊዜ የትኞቹም ቃላቶች ለአላህ የሚገባውን ምስጋና ለማቅረብ አቅም ያጥራቸውና አልሐምዱ ሊላህ የሚለው አላህ ራሱን ያመሰገነበት ቃልን ተጠቅሞ እሱን ሲያመሰግን ነው በፍስሓ የሚሞላው ።
የኩፍርን ጨለማ ያላየ የኢስላምን ብርሃን ምንነት ለመረዳት ቀላል አይሆንለትም ። በጣም የሚገርመው ግን በዚህ ኢስላም የሚያፍር ማየት ነው ። ወንድሜ በየትኛውም የእውቀትና ክህሎት ላይ ብትሆን ሙስሊም ሆነህ ነው ወደዛ ደረጃ የደረስከው ። ታዲያ ለምን ታፍራለህ እስኪ ራስህን ጠይቅ መልሱን የምታውቀው አይመስለኝም ። ያንተ በእስልምናህ ማፈር ምክንያት ከየት እንደመጣ በኔ እይታ ምን እንደሆነ ልንገርህ ። የአፄአዊያኑ ተፅኖ ውጤት ነው ። አፄዎቹ የተማረ ሙስሊም እንዳይኖር ፣ በየትኛውም የመንግስት ስልጣን ውስጥ እንዳይሳተፍ ፣ ራሱን እንደሁለተኛ ዜጋ እያየ በእነርሱ መልካም ፈቃድ እየኖረ መሆኑን እንዲያስብ ማድረጋቸው ነው ። ሙስሊም ተማሪ ፣ ሙስሊም የቢሮ ሰራተኛ ፣ ሙስሊም አስተማሪ ፣ ሙስሊም የጦር መሪ ፣ ሙስሊም ሐኪም እንዳይታሰብ አድርገው ስለነበር ከላይ በተጠቀሱ ዘርፎች ላይ አልሐምዱ ሊላህና አሰላሙ ዐለይኩም የሚል አልነበረም ። የእነዚህ አካላት የኩፍር አስተሳሰብ ፅልመት ከተገፈፈ በኋላም የስነልቦና ጫናው ቶሎ አለቀቀም ። እስከ ዛሬም እያየነው ነው ። ብዙ በመንግስት መስሪያ ቤት ላይ በተለያየ እርከን ያሉ ሙስሊሞች አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ሲባሉ ወዐለይኩሙ ሰላም ለማለት ያፍራሉ ።‼ እንዴት ናችሁ ሲባሉ እግዚአብሄ ይመስገን ወይም በድፍኑ ምስጋና ይገባው ይላሉ ። !!! ትንሽ ደህና የሆኑት ስለወደፊት ሲያወሩ ፈጣሪ ካለ ይላሉ ። ይህ በአብዛኛ አ/አ ላይና አማራ ክልል ላይ ይስተዋላል ። ይሁን እንጂ ሌላ ቦታ የለም ማለት አይደለም ።
በፖለቲካው አለም ታዋቂነትን ያገኙ ሙስሊሞችም ቢሆን አንገታቸውን ቀና አድርገው በእስልምናቸው ሳያፍሩ አልሐምዱሊላህ ፣ አላህ ካለ ሲሉ አይሰማም ። የዚህ አይነቱ የሙስሊሞች የስነልቦና ልሽቀት በጣም ያሳምማል ። ሰው እንዴት በሙስሊምነቱ ያፍራል ? በእውቀትም ፣ በሀብትም ፣ የትም ቢደርሱ የአላህ ፀጋ ነው ። አንድ ሙስሊም አላህ በለገሰው ፀጋ እንዴት ሌላውን ያወድሳል ? እንዴት ሌላውን ያመሰግናል ? እንዴት እሱን ለማመስገን ያፍራል ?
ለማንኛውም አንተ አላህ የእስልምና ፀጋ ያጎናፀፈህ ወንድሜ ሆይ ራስህ ላይ ያለውን ዘውድ ተመልከተው !!! ለዚህ የሚረዳህ ኢስላምን ማወቅና መረዳት ነውና ሲሉ ሰማሁ ብዬ እንዳይሆንብህና ፀፀት በማይጠቅምበት ቀን ከምትፀፀት ዛሬ ከተጫነብህ የጘፍላ ሸክም ተላቀቅ ።
አንተ ሙስሊም መሆኔን ማወቅ የለበትም ብለህ የምታፍረው አካል ማለት ካልነበረበት ያስገኘውን አላህን የካደ የዚህን ረቂቅ ፍጥረተ ዐለም ፈጣሪን ያስተባበለ ከህሊናው ጋር የተጣለ ነው ። እሱ ነበር እንጂ በአላህ ላይ በመካዱ ማፈር የነበረበት እንዴት አንተ ታፍራለህ ? ቶሎ ካልተመለስክና ራስህን መሆን ካልቻልክ ጎሳም ፣ ሀብትም ፣ ዘመድም ፣ ስልጣንም በማይጠቅምበትና ከሀዲ ሁሉ ምነው አፈር ሆኜ በቀረሁ ብሎ በፀፀት አካሉን በሚበላበት ቀን አብረህ ትከስራለህ ።
አንተ አላህ ፀጋውን ያንቧቧብህ ባሪያ ሆይ የተኛ መሰሎ የተሸነፈውን ማንነትህን ቀስቅሰው ። ወደ ልቅናው አመላክተው ። የተዘጋጀለትን የክብር ልብስ አጥልቅ አንገትህን ቀና አድርግ በለው ። አሁኑኑ ወደ ራሱ ተመልሶ ከብርሃን ያራቀውን አለማወቅ አውልቆ ጥሎ ወደ ማወቅ ለመሸጋገር እንዲወስንና ወደ ተግባር እንዲገባ ሰበብ ሁነው አላህ ይርዳህ ።

https://t.me/bahruteka


ሒጃብ የሚከለክል አዋጅ፣ ደንብ ወይም መመሪያ የለም
➩➩➩➩➩


🎙 አቶ ብርሃኑ እንዲህ አሉ፦ «በትምህርት ፖሊሲው ሒጃብ መልበስ የተከለከለ ነገር የለውም።»
ታዲያ በአክሱም ያሉት የትምህርት ቤት አስተዳደሮች በየትኛው ፖሊሲ እየተመሩ ነው? ተናበቡንጂ ጋሼ!

🎙 «በኒቃብና በጅልባብ መካከል ያለው ልዩነት...»
ተው በማይመለከትዎ አይግቡ በልኩ ሆኑ ኒቃብም እንደማንኛውም መብታችን የሚከበርልን የእምነታችን አካል ነው። security የሚሉትን ጉዳይ ሌላ መፍትሔ ፈልጉለት! ለመሆኑ ኒቃሲስቷ የምታመጣው አደጋ ካለ በሌሎቹ ምን ዋስትና አለ? ወይስ የሴኩሪቲው ጉዳይ ያለው በፊቷ ነው?

🎙 «በሒጃብ ደረጃ የተከለከለ የለም። ማንም ይሄንን የሚከለክለው አዋጅ የለም፤ ደንብ የለም፤ ይህንን የሚከለክል መመሪያ በትምህርት ሚኒስተር በኩል የወጣ የለም።»
እውነታው ይህ ከሆነ ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ ቀጥሎም አሁን በአክሱም እየተሰራ ያለው ምንን ተመርኩዞ ነው? ስንት አስተዳዳሪዎች ናችሁ? ሲከሰትስ በፍጥነት መልስ አትሰጡም?

🏝 ተናባችሁ የምትሰሩ ከሆነ ሞክሩ ካልሆነ ሙስሊሞችን እየነካካችሁ መውደቂያችሁን አታመቻቹ! የተደበላለቀ አካሄድ ይዞ ዜጎችን መረበሽ አላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመሆኑ ራሳችሁን መርምሩ!!!

▵▮▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▯▴
⚙ 📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy


“የአይሁዳውያን ክፋት...”

⭕️ የአይሁዶች እኩይ ብክለት

⭕️ አይሁዶች አለቅጥ አምባገነን ስለመሆናቸው

⭕️ የአይሁዳውያን ፈለስጢን ላይ ከዚህ ቀደም መጥፎ የሆነ ብክለትን እንዳካሄዱ

⭕️ ዘከሪያን (ዐለይሂ ሰላም) ስለመግደላቸው

⭕️ የህያን (ዐለይሂ ሰላም) ስለመግደላቸው

⭕️ ዒሳን (ዐለይሂ ሰላም) ለመግደል እንቅስቃሴ መጀመራቸው

ከሱረቱል ኢስራእ ቀርኣን ተፍሲር የተቀነጨበ

🎙🎙 በሸይኽ #አቡ_ዘር (ሀፊዘሁሏህ)

https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha/8891


👉 ሀገሪቷን ማን በየትኛ ህግ ነው የሚያስተዳድራት ?

ሀገራችን ኢትዮዽያ የምትመራበት ህገመንግስት አንቀፅ 27 የዜጎች የእምነት ነፃነትን ያውጃል ። የዜጎች ሲባል እየአንዳንዱ ዜጋ ማለት ነው ። ይህ ማለት አንድ ሰው የፈለገውን እምነት የመቀበል ፣ እምነቱ የሚያዘውን ነገር የመተገብር መብቱ ማንም ሊነጥቀው የማይችል ወይም በማንም መልካም ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ አለመሆኑና ይልቁንም የዜግነት መብቱ መሆኑን ነው የሚያሳየው ።
በሀገራችን በየትኛውም ደረጃ ያሉ ክልሎችም ይሁን ዞንና ወረዳዎች በዚህ ህገመንግስት ስር ሆነው ነው ክልላቸውን ወይም ዞንና ወረዳቸውን ማስተዳደር ያለባቸው ። ከላይ ያየነው አንቀፅ የአንድን ግለሰብ መብት የሚያስጠብቅ ከሆነ በሺዮች ወይም በመቶ ሺዮች የሚቆጠሩ ዜጎች ሲሆኑ ደግሞ ምን ሊሆን እንደሚችል ግልፅ ነው ። ማንም ተነስቶ የግለሰብን እንኳን ህገመንግስታው መብት የሚጥስ መመሪያ ማውጥት የማይችል ከሆነ የህዝቦችን መብት የሚጥስ መመሪያ ማውጣት አለመቻሉ ከበጋ ፀሀይ የበለጠ ግልፅ ነው ማለት ነው ።
የህገ መንግስቱ መመሪያ ይህ ከሆነና መንግስት የሚሰራው በዚህ ከሆነ በምን ሒሳብ ነው ይህን የህዝቦች መብት ያረጋግጣል የተባለውን መመሪያ አሻፈኝ ብሎ ይህን የሚፃረር መመሪያ ስራ ላይ በማዋል የዜጎች መብት የሚረገጠው ?
በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን ላይ በተለያዩ ክልሎች በግልፅ ይህን ህገመንግስታዊ የዜጎች መብት በጣሰ መልኩ የራሳቸው ህግ በማርቀቅ መብት የሚረግጡ መኖራቸው የአደባባይ ሚስጢር እየሆነ ነው ። ለመሆኑ እነዚህ አካላት ህገ መንግስቱ እኛን አይወክልም የራሳችን ህገመንግስት አለን ባዮች ናቸው ወይስ ከህገ መንግስቱ ውስጥ ለኛ የሚስማማውን ወስደን የማይስማማውን እንተወዋለን ማን ምን አገባው ባዮች ናቸው ? ወይስ ጠያቂ የለም ነው ነገሩ ። ለማንኛውም እንዲህ አይነት ፅንፈኝነት ለማንም አይጠቅምም ።
የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ማንኛውም ተማሪ ሀይማኖትን የሚያንፀባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም በሚል ሙስሊም ሴት ተማሪዮችን ሒጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት እዳይገቡ መከልከሉ ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም እንደሚሉት ነው ። ለመሆኑ እነዚህ አካላት አንገታቸው ላይ ክር አስረው ክርስቲያን መሆናቸውን የሚገልፅ ነገር ያደረጉትንም ጭምር ነው ያባረሩት ወይስ የሙስሊሞችን እስልምና የሚገልፅ ነገር ነው ወንጀል የሆነው ? ለመሆኑ በትግራይ ክልል እንደ አፄዎቹ ዘመን የሙስሊም ኮፍያ መልበስም ወንጀል ነው ? በአክሱም ከተማ እስልምናን የሚገልፅ ነገር እንደ ኮፍያ ፣ ሒጃብ ፣ ጅልባብና የመሳሰሉ መገለጫዎችን የሚያደርጉ ሙስሊሞች አይደለም በሴክተር መስሪያ ቤት ሊሰሩ ለጉዳይም መግባት አይችሉም ሊሉ የሚፈልጉ ይመስላል ።
የሚገርመው በሒጃብ ዙሪያ እንደሀገር ሙስሊም ሴት ተማሪዮች ከዩኒፎርም ጋር የሚመሳሰል ሒጃብ ለብሰው መማር የሚችሉ መሆኑን የሚገልፅ መመሪያ እንደ ኢትዮዽያ አቆጣጠር በ2000 ወጥቶ በስራ ላይ የዋለ መመሪያ አለ ። ይህ ከህገመንግስቱ የፈለገችውን የመልበስ መብት ማረጋገጥ በተጨማሪ ማለት ነው ። ታዲያ የአክሱም ከተማ ፅንፈኞች ለየትኛው ህግ ይሆን የሚገዙት ? ወይስ የኋሊዮሽ ተመልሰው የአፄዎቹ ዲስኩር መንዛት ነው የተያያዙት ?
በአሁኑ ጊዜ የዜጎች መብት መረገጥ በሌሎችም የእምነት ተቋማትም እየታየ ነው ። ከላይ የተጠቀሰውን አንቀፅና እንዲሁም ማንኛውም ዜጋ ለህጋዊ አላማ የመደራጀት መብቱ የተጠበቀ ነው የሚለውን የህገ መንግስቱ አንቀፅ 32 እንዲሁም መጅሊሱ በአዋጅ ሲፀድቅ ከዚህ በፊት የተቋቋሙ ወይም የተደራጁ ማህበራትን መከልከል አይችልም የሚለውን አዋጅ በመፃረር የአሁኑ የመጅሊስ አመራሮች በቁርኣንና ሀዲስ ሳይሆን በራሳቸው ልብ ወለድ የሚመሩት መጅሊስ ስር ያልሆነን ዜጋ አይደለም እስከ ማለት ደርሰዋል ።‼ እነዚህን ከላይ የተገለፁ የዜጎችን መብት የሚረግጡ መመሪያዎችን የሚቃረን መመሪያ በማውጣት ይህን ተቀብሎ ተግባራዊ የማያደርግ በዚህች ሀገር መኖር አይችልም ሀገሩን ይፈልግ እስከማለት ደርሰዋል ።
ይህ ነው ይህች ሀገር ማን በየትኛው ህግ ነው የሚያስተዳድራት የሚል ጥያቄ የሚያስነሳው ። ዜጎች በጣም በሚገርም ተስፋ የጠበቁት ብልፅግና እንደነዚህ አይነት ተግዳሮቶችን በመዋጋት ወረቅት ላይ ያሉትን ፍትህ የናፈቃቸው ቃላት መሬት ላይ ወርደው ስራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ የመጀመሪያ ተግባሩ ሊሆን ይገባል እላለሁ ።

ፍትህ ለአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዮች ።

https://t.me/bahruteka


Репост из: abdul Menan Emam
🔷 ለጥንቃቄ

በቴሌግራም መረጃዎች እየተመዘበሩ እንደሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር / ኢንሳ አሳውቋል።

ኢንሳ በዛሬው ዕለት በቴሌግራም መረጃዎች እየተመዘበሩ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል አሳስቧል።

ኢንሳ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች በተለያዩ ማስገሪያ (ፊሺንግ ሊንክ) አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ እንደሆነ ገልጷል።

በመሆኑንም ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከሚያውቁትም ሆነ ከማያውቁት) ግለሰብ ሊንክ ቢላክ መክፈት ተገቢ እንዳልሆነ እና ወዲያውኑ ማጥፋት እንደሚገባ አሳስቧል።

መረጃው የቲክቫህ ኢትዮዽያ ነው ።

https://t.me/bahruteka


Репост из: abdul Menan Emam
🔷  የዶክተር ጀይላን ጓደኛ

       የመካ ገጠመኜ ትውስታ
          
      ዛሬ ጀማደ ሳኒ 21/1444 በተከረው ከተማ መካ ሐረም ላይ ከዐስር ሶላት በኋላ አንድ ከጎኔ የሰገደ እድሜው 70ዎቹ አካባቢ የሆነ ፂሙ ነጭ ሆኖ በጣም ደስ የሚል ዐረብ ስሙ ኩንያው አቡ አሕመድ ስሙ ሙሐመድ የሆነ ስው ሞቅ ባለ ፈገግታ ሰላም አለኝ ። እኔም በተመሳሳይ መለስኩለት ።
    ቀጥሎ ከየት ሀገር ነህ አለኝ ከኢትዮዽያ አልኩት ። ከመጀመሪያው በበለጠ ፈገግታ ከዋና ከተማው ወይስ ከገጠሩ አለኝ እኔም ገጠር ተወልጄ ከተማ ነው ያደኩት አልኩት ። ቀጠለና ከየትኛው አቅጣጫ አለኝ ከደቡብ አልኩት ።
     ወሬው ሞቅ ብሎ ቀጠለ ደቡብን አላውቀውም ወራቤን ነው የማውቀው አለኝ ‼።  እኔም ወራቤ እኮ በደቡብ ነው ያለው አልኩት ። ጊዜ ማጥፋት የፈለገ አይመስልም ዶክትር ጀይላንን ታውቀዋለህ ወይ አለኝ ። እኔም በማወቅ ደረጃ አውቀዋለሁ ግን እቃረነዋለሁ አልኩት ። ያ ፈገግታ ደመና ወረሰው ።
   ለምን አለኝ ከአሕባሽና ሱፍይ ጋር ስለተደመረ አልኩት ። በቃ አታውቀውም ማለት ነው ። እሱ እኮ የሐበሻ ሙፍቲ ነው አለኝ ‼ ። ደግሞም ከጃሚዓ ተመርቋል አለኝ ። እኔም ያውም በዶክተርነት ከዐቂዳ ፋካሊቲ ነው አልኩት ።
     ቀጠለና አንተ ማንን ነው የምትከተለው አለኝ ? እኔም ሰለፎችን ነው አልኩት ። በጣም በሚገርም መልኩ የሰለፎች መዝሀብ ማን ነው የደነገገው አለኝ ? ሰለፎች የራሳቸው መመሪያ የላቸውም መመሪያቸው ቁርኣንና ሐዲስ ነው አልኩት ። በሙሉ ድፍረት አይደለም እናንተ ሰለፎችን ሙሸሪዕ አድረጋችኋል በዚህም ሙሽሪኮች ናችሁ አለኝ ።‼
      እኔም ልቆጣጠረው የማልችለው ስሜት እየታገለኝ እንደምንም ራሴን ተቆጣጥሬ ያንተ መዝሀብ ምንድነው አልኩት ።
   በቀላሉ የኢኽዋነል ሙስሊሚን መዝሀብ ነው አለኝ ።‼  ከዛ ቀጠለና አላህ ሙስሊሞች ብሎ ጠርቶናል ብሎ የቁርኣን አንቀፆችን ደረደረ ። እኔም በዐለም ላይ ያሉ ሙስሊሞች ሁሉ እስልምናቸው አንድ አይነት ነው ወይ አልኩት ? እሱም በሙሉ ድፍረት አው አለኝ ።‼
   እሺ አሁን እዚህ ካዕባ ጋር ሆነው ከአላህ ውጪ ሙታኖችን የሚጠሩ አሉ የእነርሱ እስልምናና ያንተ እስልምና አንድ አይነት ነው ወይ አልኩት ? እሱም አይ የእነሱ ሽርክ ነው አለኝ ። ካፊሮች ናቸው ወይስ ሙስሊሞች ናቸው አልኩት ? እሱም እኔ ማንንም አላከፍርም አለኝ ። እሺ ሙስሊሞች ናቸው ማለት ነዋ አልኩት ። አው ጃሂሎች ናቸው እናስተምራቸዋለን አለኝ ።
   በጣም ቆንጆ የጥያቄዬን መልስ ስጠኝ ያንተ እስልምናና የእነርሱ እስልምና አንድ ነው ወይ አልኩት ? ግግም ብሎ አላህ ሙስሊሞች ብሎናል አለኝ ። አው ግን ምን አይነት ሙስሊም አልኩት ? ይህ የናንተ ቢዳዓ ነው አላህ የዚህ አይነት የዚህ አይነት አላለም አለኝ ።
   እኔም የኛ ቢዳዓ አይደለም የአላህ ትእዛዝ ነው ምክንያቱም አላህና መልእክተኛው እኛን የሙሀጂሮችንና የአንሷሮችን መንገድ እንድንከተል አዘውናል ብየው የሚከተለውን የቁርኣንና ሐዲስ መረጃ አመጣሁለት : –

وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ
                         التوبة (  100)
" ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል ፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል ፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው "፡፡

« وَمَن يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا »

                   النساء   ( 115 )

" ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን ፤ ገሀነምንም እናገባዋለን ፡፡ መመለሻይቱም ከፋች ! "
ከምእምኖች መንገድ ሌላ የተባለው ከሶሓቦች መንገድ ሌላ ለማለት ነው የነኛ ሰለፎች ሶሓቦች ናቸው ። የዶክተር ጓደኛ ግን ሰለፉ ሐሰነል በና ነው ።!!!
      ሌላኛው እነ አቡበከርና ዑመርን መከተል ግዴታ መሆኑ ከሚያመላክቱ ሐዲሶች ውስጥ የሚከተለውን አንድ  ሐዲስ ማየት በቂ ነው :  –

عن العرباض بن سارية رضي الله عنه،
قال: صلى بنا رسول الله – صلى الله عليه وسلم–
" الصبح ذات يوم، ثم أقبل علينا، فوعظنا موعظة بليغة، ذرفت منها العيون، ووجلت منها القلوب، فقال قائل: يا رسول الله، كأن هذه موعظة مودع، فأوصنا،
فقال :
«أُوصِيكُمْ بِتَقْوَى اللَّهِ، وَالسَّمْعِ وَالطَّاعَةِ، وَإِنْ كَانَ عَبْدًا حَبَشِيًّا، فَإِنَّهُ مَنْ يَعِشْ مِنْكُمْ بَعْدِي فَسَيَرَى اخْتِلَافًا كَثِيرًا، فَعَلَيْكُمْ بِسُنَّتِي وَسُنَّةِ الْخُلَفَاءِ الرَّاشِدِينَ الْمَهْدِيِّينَ، تَمَسَّكُوا بِهَا، وَعَضُّوا عَلَيْهَا بِالنَّوَاجِذِ، وَإِيَّاكُمْ وَمُحْدَثَاتِ الْأُمُورِ، فَإِنَّ كُلَّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ، وَكُلَّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ».

أخرجه الإمام أحمد وأبو داود وغيرهما

    ቀጥዬ የነብዩ ሱና ትክክለኛ እስልምና መሆኑን ታምናለህ ወይ አልኩት? አው አለኝ ። የኹለፋዎቹስ አልኩት ?  ይህ የናንተ ተፍሲር ነው የሰለፎች መዝሀብ እሱ አይደለም አለኝ ።
    ሰለፍ ማለት ምን ማለት ነው አልኩት ሊመልስልኝ ፈቃደኛ አልነበረም ። በጣም በሚያስጠላ መልኩ እናንተ ሰለፎችን ነው የምትገዙት በአላህ ዲን ላይ ደንጋጊ አደረጋችኋቸው አለኝ ።
     እኔም አንተ የምትፈልገው ሙስሊሞችን ከአቡበከር ፣ ዑመር ፣ ዑስማንና ዐልይ ረዲየላሁ ዐንሁም  መንገድ አውጥተህ ወደ ሐሰነል በናና ሰይድ ቁጥብ ፍልስፍና ማስገባት ነው ብዬው ተለያየን ።
    ይህ ነው የዶክተር ጀይላን ጓደኛና ኢትዮዽያ ላይ ያሉ ሙስሊሞች ዶክተር ጀይላንን እንዲከተሉ የሚጣራው ጉደኛ
      አላህ ሐቅን አውቀን የምንከተለውና ባጢልን አውቀን የምንርቀው ያድርገን ።

ከተወሰነ ጭማሪ ጋር በድጋሚ የተለቀቀ ።

 https://t.me/bahruteka


✅ #አዲስ_ሙሐደራ 
#محاضرة_جديدة

⬅️ بعنوان:-➘➘
↩️ مكانة أهل العلم الشرعي في الإسلام

↪️ የሸሪዓዊ እውቀት ባለቤቶች ቦታና ደረጃ በኢስላም

🎙للشيخ أبي طلحة أبي ذر بن حسن الولوي حَفِظَهُ اللَّهُ

ከተዘረዘሩ አንኳር ነጥቦች በጥቂቱ ይመልከቱ➘

➧ከነብያት የተወረሰ የሆነውን ኢልምን መውደድ ትክክለኛ አሊምንም መወደድ አሏሁ ሱብሃነዎ ተዓላን የሚገዙበት የዲን አካል ስለመሆኑ
➧ሸሪዓዊ እወቀትንና ባለቤቶቹን መጥላት የነብያቶችን ውርስ መጥላት የነብያት ወራሾችንም መጥላት ሰለመሆኑ

➧ዑለማዎች የነብያት ወራሾች ሰለመሆናቸው፦

➧የባህር አሳዎች ለዑለማወች እሰቲغፍር እንደሚያደርጉላቸው

➧ አሁን ላይ የሱና ዑለማዎችን አዛ የሚያደርጉ የሚያብጠለጥሉ የሆኑ ሂዝቢያት መካ ላይ የነበሩ የአሏህ መልክተኛ ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለምን አዛ ያደርጉ የነበሩ ሰዎች አምሳያዎች ሰለመሆናቸው

➧ለዑለማዎች መላይካዎች ክንፍቸውን እንደሚዘረጉላቸውና በየውመል ቂያማም ከነብያቶች ቀጥሎ እነሱ እንደሚያማልዱ

➧የሱና ዑለማዎችን ማክበር መታዘዝ ከእናት ከአባት በፊት እንደሚቀደም እነሱን ማመፅ ሀራም ሰለመሆኑ

➧ የሱና ዑለሞች የጨለማ መብራት ሸይጧን የሚበሳጭባቸው፣ የአማኝ ልቦች ህያው የሚሆኑባቸው የጥመት ሰዎች ልብ ደግሞ የሚሞቱባቸው ሰለመሆኑ ምሳሌያቸውም ሰማይ ላይ እንዳሉ ከዋክብቶች ሰለመሆኑ

➧ከሶስቱ በሽታዎች በአንዱ በሽታ የወደቀ ቢሆን እንጅ በትክክለኛ የሱና ዑለሞች ክብር ላይ የሚወድቅ አለመኖሩ

➣ማንቂያ ይህ ሁሉ የተባለው ለውነተኛ ዑለማዎች መሆኑ እንዲሰመርበት ይፈለጋል‼️

የሸይኹን ቻናል join በማለት ተጨማሪ እውቀቶችን ይሸምቱ ይጠቀሙ‼️
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha


👆👆👆
🔈
#ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ከእሳት ጠብቁ፡፡

🔶
በአዲስ አበባ በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል የተደረገ ሙሐደራ።

🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)

📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ
👇👇👇
🌐 https://t.me/shakirsultan


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ሙብተዲዕ ላይ መጠንከር

➲ በተመዩዕ ወስዋስ የተለከፉ ሁሉ ይህን የኢብኑል ቀይም ንግግር ተረድተውት ይሁን!?

➲ የቢድዓህ እና የሙብተዲዕ አደገኝነት ተጠቅሷል።

🎙للشيخ أبي طلحة أبي ذر بن حسن الولوي «حَفِظَهُ اللَّهُ»
🎙 በሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ ሀፊዘሁሏህ

https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha


👆👆👆
🔈
#ለሞት የመዘጋጀት ግደታነት እና የቀብር ጥያቄ

🔶
በማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን በምስራቅ አዘርነት በርበሬ በቅልጦ  ወረዳ በሾሞ ቀበሌ የተደረገ ሙሐደራ ።

🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)

📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ
👇👇👇
🌐 https://t.me/shakirsultan


Репост из: ዳር አስ-ሱንና Dar As-sunnah Channel
🔹 ታላቅ የሙሃዶራ ዝግጅት
በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል


በአላህ ፈቃድ የፊታችን እሁድ ታህሳስ 6/2017 በአይነቱ ልዩ የሆነ የሙሃዶራ ዝግጅት ተሰናድቷል

🕰 ሰዓት:- ከጠዋቱ 3:00 እስከ 6:30 (በጊዜ ይገኙ)

ተጋባዥ እንግዶች:-
ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)
ኡስታዝ ዐብዱልቃዲር ሐሰን (ሀፊዘሁላህ)
ኡስታዝ ሻኪር ሱልጧን (ሀፊዘሁላህ)
በተለያየ ርእስ ይቀርባል

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

አድራሻ:- አዲስ አበባ ኮ/ቀ ክ/ከተማ አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊት ለፊት ባለው ቂያስ ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን መንገድ ከድልዲዩ በስተ ቀኝ ባለው ቂያስ እንገኛለን።
ለተጨማሪ መረጃ:- +251920908031

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444


🔹  ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም

    የፊታችን እሁድ ታሕሳስ 6/2017 በእነሞር ወረዳ ጉንችሬ ክ/ከተማ ጉንችሬ ማዞሪያ ዑመር መስጂድ ላይ ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኃል ።
    ተጋባዥ እንግዶች
1ኛ – ሸይኽ ዐ/ሐሚድ
2ኛ – ወንድማችሁ ባሕሩ ተካ
3ኛ – ኡስታዝ ሱደይስ

    ፕሮግራሙ የሚጀመረው አላህ ካለ ጠዋት 2 : 30 ይሆናል ።
   
https://t.me/bahruteka


የቁርኣን ትርጉም ማብራሪያ የአንዓም ምእራፍ ክፍል 06
አላህ ከመራን በኋላ ከአላህ ውጪ ያለን የማይጠቅምና የማይጎን የኋሊዮሽ እንመለስ ዘንድ እንገዛለን ብለህ በላቸው የሚለው አንቀፅና ሌሎችም የተብራሩበት

Показано 20 последних публикаций.