የትግራይ ህዝብ ያደረጋቸው ጦርነቶች “ህልውናውን ለማረጋገጥ እና ለጭቆና እጅ አልሰጥም በማለት ነው” - ህወሓት
ህወሓት የትግራይ ህዝብ የሰላም ምኞት ዕውን እንዲሆን ሁሉም ገንቢ ሚና ይጫወት ሲልም ጥሪ አቅርቧል።
በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ቡድን "የትግራይ ህዝብ እና የትግራይ ልሂቃን ቀዳሚ ምርጫው ሰላም ነው" ሲል ትላንት ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ጠ/ሚኒስት አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ህወሓት የጠ/ሚኒስትሩን ጥሪ ተከትሎ መግለጫ ያወጣ ሲሆን፤ በመግለጫውም "የትግራይ ህዝብ ቀዳሚ ምርጫ ሰላም ነው" ብሏል።
የትግራይ ህዝብን የሰላም ምኞት አውን ለማድረግ ሁሉም ገንቢ ሚና ይጫወት ሲል ጠይቋል። ከማንኛውም አካል ጋር በሰላም ዙሪያ ለመስራት ዝግጁ ነኝ ሲልም አስታውቋል።
ህወሓት በመግለጫው ባለፉት መቶ አመታት የትግራይ ህዝብ ያደረጋቸው ጦርነቶች “ህልውናውን ለማረጋገጥ እና ለጭቆና እጅ አልሰጥም በማለት ነው” ሲል በመግለጽ፤ “የትግራይ ህዝብ ያደረጋቸው ተጋድሎዎች ያኮሩታል እንጂ አያስቆጩትም” ብሏል።
https://t.me/voa_amharic1