የትግራይ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ የክልሉ ታጣቂ ኃይሎች ባለፈው የካቲት 12 ቀን በደቡባዊ ምሥራቅ ዞን፣ በሰሃርቲ ወረዳ፣ አዲስ ዓለም ቀበሌ ከአስተዳደር መዋቅሮች ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ውጥረት አረጋግተው ወደ ቦታቸው በመመለስ ላይ ሳሉ ጥቃት ተፈጽሞባቸው በማለት መግለጫ አውጥቷል።
ቢሮው፣ የጸጥታ ኃይሉ በሕዝብ ላይ የኃይል ርምጃ በመጠቀም ጥፋት ሠርቷል የሚል የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶበታል ብሏል። አንዳንድ የግል ጥቅማቸውን የሚያሳድዱ ኃይሎች የቀበሌዋን ነዋሪ በኹለት ጎራ ከፍለው ውጥረት መፍጠራቸውን ተከትሎ፣ የጸጥታ ኃይሉ አባላት ኹኔታውን እንዲያበርዱ ወደ አካባቢው የሄዱት በነዋሪው ጥሪ እንደነበርም ቢሮው ጠቅሷል። ኾኖም የጸጥታ አባላቱ ውጥረቱን ስኬታማ በኾነ መንገድ አብርደው ሲመለሱ፣ መንገድ ላይ በተፈጸመባቸው ጥቃት መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ቢሮው በመግለጫው አመልክቷል።
https://t.me/voa_amharic1