በአደባባይ የተላለፈ የጥላቻ ንግግርና ሀይማኖታዊ ትንኮሳ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የፈጠረውን ህመም እርምጃ ይወሰድ ሲል ጠቅላይ ም/ቤቱ አሳሰበ፡፡
ከሰሞኑ አንድ ግለሰብ በማህበራዊ ሚዲያዎች ነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) እና እስልምናን መዝለፉ በርካቶችን አስቆጥቷል።
በዚህ ዙሪያም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት መግለጫ አዉጥቷል፡፡
በመግለጫው የጥላቻ ንግግር በማድረግ ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ አሳስቧል።
የእስልምናን መልካም እሴቶች እና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር በመዳፈር ህዝበ ሙስሊሙን የሚያስቆጡ የጥላቻ ንግግሮች በስፋት እየተሰራጩ መሆናቸውን የገለጸው ጠቅላይ ም/ቤቱ፤ እነዚህ አካላት ከዛሬ ነገ ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸው ከጥፋታቸው ይታረማሉ በሚል ቀና እሳቤ ጉዳዩን በትዕግስት ሲከታተል እንደቆየ አስታዉቋል፡፡
ይሁን እንጂ ችግሩን ከዚህ በላይ በትዕግስት መመልከት ውጤቱ የከፋ መሆኑን ጠቁሟል።
የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር የሚነኩ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ከየትኛው አይነት ተግባር ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራም አሳውቋል።
በመሆኑም በተደጋጋሚ ተከስቶ በቸልታ እየታለፈ ያለው የኢስላምንና የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) ክብር የሚነካ የጥላቻ ንግግር ያደረጉ ግለሰቦች አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የፍትህ፣ የፀጥታና የደህንነት አካላት የህግ ተጠያቂነትን ለማምጣትና መሰል ጥፋቶች እንዳይደገሙ ከመቼውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንዲሰሩ ም/ቤቱ አሳስቧል።
የምክር ቤቱ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል👆👆
https://t.me/voa_amharic1