የሶማሌ ክልል መንግስት የቀረበበትን “የሙስና” ክስ “ሀሰት እና ስም የማጥፋት ዘመቻ ነው” ሲል ውድቅ አደረገ!
የሶማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ “በክልሉ ሙስና ተንስራፍቷ፤ ፕሮጀክቶች ተንጓተዋል” ሲል ያቀረበውን ክስ የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ፤ “ሀሰት” እና “ስም የማጥፋት ዘመቻ” ሲል ውድቅ አደረገ።
የሶማሌ ፌዴራሊስት ፓርቲ ባሳለፍነው ሳምንት ባወጣው መግለጫ፤ “በክልሉ ለልማት ስራዎች የተመደበው ከፍተኛ ገንዘብ አላግባብ ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሚገኝ ገልጿል። ፓርቲው በመግለጫው “ሙሉ ክፍያ ተከፍሎ ነገር ግን ፕሮጀክቶቹ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ሳይገነቡ” እንደቀሩም ገልጿል።
የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው ደብዳቤ፤ “በሙስና እና ፕሮጀክቶች መንጓተት” ላይ የቀረበው ወቀሳ “መሬት ላይ ያለውን እውነታ የማያሳይ ነው” ብሏል። የህዝብ ገንዘብ አላግባብ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው በሚል በፓርቲው የቀረበውን ቅሬታ ውድቅ በማድረግ የግንባታ ስራዎች ጨረታ "በግልፅ በጋዜጣ ታትመዋል" እና የግንባታ ስራውም በውድድር ብቁ ለሆነ የግንባታ ተቋራጭ ተሰጥቷል ብሏል።
https://t.me/voa_amharic1