የጊዜያዊ አስተዳደሩ በሶስት ጄነራሎች ላይ ያሳለፈው የእግድ ውሳኔ ተቋማዊ አሰራርን እና ህግን ያልተከተለ ነው” - የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ በተለያዩ ግንባሮች አዛዦች መሆናቸው የተገለጸ ሶስት ጄነራሎችን፤ ሜጀር ጀነራል ዮሃንስ ወ/ጊዮርጊሰ፣ ሜጀር ጀነራል ማሾ በየነ እና ብርጋዴር ጀነራል ምግበይ ሀይለ በግዜያዊነት ማገዳቸውን አስታወቁ።
በፕሬዝዳንቱ የተጻፈው ደብዳቤ እንደሚያሳየው ጄነራሎቹ በግዜያዊነት የታገዱት “ከመንግስት ውሳኔ ውጭ መላ የክልሉን ህዝብ እና ወጣቱን ወደ ግርግር፣ የጸጥታ ሀይሉን ወደ እርስ በርስ ግጭት የሚያስገባ እንቅስቃሴዎች እያደረጉ በመሆኑ ነው” ብሏል፤ የጀነራሎቹ እንቅስቃሴ “ህዝቡ ወደማይወጣው አዘቅት የሚከት ነው” ሲል አስታውቋል።
የፕሬዝዳንቱን ውሳኔ ተከትሎ የክልሉ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ “የወንጀለኞች ጠበቃ መሆን ይብቃ” በሚል ርዕስ ዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ውሳኔውን እንደማይቀበለው አስታውቋል፤ “ያልሾመውን ያወረደ ነው” ሲል ገልጿል።
በተመሳሳይ በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ባወጣው መግለጫ የጉዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ውሳኔን ህገወጥ ሲል ኮንኗል፤ “የትግራይ ሰራዊትን ለማፍረስ ሲያደርግ የነበረው ሴራ ወደ ከፍተኛ እና አደገኛ ደረጃ አሸጋግሮታል” ሲል ገልጿል።
https://t.me/voa_amharic1