በደብረጺዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ሕወሓት፣ ፌደራል መንግሥት የትግራይ ግዛቶችን በኃይል የያዙ የታጠቁ ኃይሎችን ባስቸኳይ እንዲያስወጣ ትናንት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።
ቡድኑ፣ የትግራይን መሬት በኃይል የተቆጣጠረው አካል "የተከዜ ዘብ" የሚላቸውን አዳዲስ ታጣቂዎች እያስመረቀ በትግራይ ላይ "የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ ይገኛል" በማለትም ከሷል።
ይህ ዓይነቱ ድርጊት የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት ሙሉ በሙሉ የሚጻረርና ዘላቂ ሰላም እንዳይመጣ እንቅፋት የሚፈጥር ነው በማለትም ቡድኑ አስጠንቅቋል።
የአፍሪካ ኅብረት ፓናል ባፋጣኝ ተሰብስቦ በፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት አጠቃላይ አፈጻጸም ላይ እንዲወያይም ቡድኑ ጠይቋል።
ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ባለመኾኑ፣ የሕዝብ ሞት፣ ሥቃይና ሠቆቃ እንደቀጠለ ይገኛል ብሏል። የፕሪቶሪያው ስምምነት ባለፉት ሁለት ዓመታት ለትግራይ ሕዝብ ትርጉም ያለው ለውጥ አላመጣም ያለው ፓርቲው፣ የታጠቁ ኃይሎች በኃይል በያዟቸው የትግራይ ግዛቶች አኹንም ወገኖቻችን እየተገደሉ፣ እየተፈናቀሉ፣ እየታሠሩና እየተሠቃዩ ይገኛሉ ብሏል።
ቡድኑ፣ የፕሪቶሪያው ስምምነት ተደራዳሪዎችና ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው እንዲመለሱ አስቸኳይ ርምጃ እንዲወስዱም ጥሪ አድርጓል። [ዋዜማ]
🔽 📹
ይህንን በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4