ኢሰመጉ ፤ በአዲስ አበባ በህገወጥ የሚታሰሩ ሰዎችን የመንግሥት ትምህርት ቤቶች በማቆያነት ያገለግላሉ መባሉን ለማረጋገጥ የሚመለከታቸውን አካላት ብጠይቅም ምላሽ አልሰጡኝም አለ
👉🏼 በአዲስአበባ ሕጋዊ ሥርዓትን ያልተከተሉ የጅምላ እስሮች አሁንም ቀጥለዋል ብሏል
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በአዲስ አበባ ከተማ እና በአማራ ክልል በንጹሀን ላይ እየተፈጸሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተባብሰዋል ሲል በትናንትናዉ እለት ባወጣዉ መግለጫ አሳዉቋል።
ኢሰመጉ በአዲስ አበባ ከተማ ሕጋዊ ሥርዓትን ያልተከተሉ እና አንዳንዶቹም አስገድዶ የመሰወር ባህርይ ያላቸው የጅምላ እስሮች መፈፀም መቀጠላቸውንም ተናግሯል። የሚታሰሩ ሰዎችም በተገቢው ጊዜ ፍርድ ቤት እንደማይቀርቡ ፣ የታሰሩ ሰዎች የት እንዳሉ በቤተሰቦቻቸው እንደማይታወቅ አረጋግጫለሁ ብሏል።
ለእነዚህ እስሮች በከተማዋ የሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች እንደማቆያነት እንደሚያገለግሉ የደረሳቸውን መረጃ ለማረጋገጥም አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮን ፣ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን በደብዳቤ ቢጠይቅም ሪፖርቱን እስካወጣበት መስከረም 12/ 2016 ዓ.ም. ድረስ ምላሽ አለማግኘቱን ዳጉ ጆርናል ከመግለጫው ተመልክቷል።
በተጨማሪም አንዳንድ የእስረኞች ማቆያዎች ለዚህ ተግባር ያልተቋቋሙ እና በንጽሕና ያልተያዙ በመሆናቸው ታሳሪዎች ለከፍተኛ የጤና ቀውስ መዳረጋቸውንም ኢሰመጉ በሪፖርቱ ገልጿል።
በተመሳሳይ በአማራ ክልል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኋላም ጋዜጠኞችንና ያለመከሰስ መብት ያላቸውን የምክር ቤት አባላት ጨምሮ መጠነ ሰፊ የጅምላ እስሮች መፈፀማቸውን አስታውሶ፣ የሚመለከታቸው አካላት እነዚህን ከሕግ አግባብ ውጭ የተፈፀሙ እስሮች ለማስቆም እርምጃ ባለመውሰዳቸው አሁንም የጅምላ እስሮች ቀጥለዋል ሲል በመግለጫው ጠቅሷል። ከታሳሪ ቤተሰቦች አገኘኋቸው ባላቸው መረጃዎች በመዲናዋ በርካታ ሰዎች ያለአግባብ እንደታሰሩም አሳዉቋል።
https://t.me/wektawi1mereja