#Update
ራስ ገዟ ሶማሊላንድ የሶማሊያ መንግሥትን አስጠነቀቀች።
ከኢትዮጵያ ጋር የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ለማደናቀፍም ይሁን ለመቃረን የሚሞክር ማንኛውም ግለሰብ ይሁን አካል ላይ እርምጃ ወስዳለሁ ብላለች።
የራስ ገዟ ሶማሌላንድ" የሚኒስትሮች ምክር ቤት " ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ ነበር።
ከስብሰባው በኃላ ባወጣው ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ ፦
- ምክር ቤቱ እ.ኤ.አ. ጥር 1/2024 በአዲስ አበባ የተፈርመውን የመግባቢያ ስምምነት በሙሉ ድጋፍ አፅድቆ እንደተቀበለውና እንደሚያደንቅ ገልጿል።
- ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ " ለሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " ሉዓላዊነት እውቅና የሰጠች የመጀመሪያ ሀገር በመሆኗ ምስጋናውን አቅርቧል።
NB. (የኢትዮጵያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፤ ስምምነቱ በሂደት ሶማሌላንድ ዕውቅና ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት በጥልቀት አጢኖ አቋም እንደሚወስድበት መግለፁ ይታወቃል)
- ምክር ቤቱ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሶማሌላንድ ምድሯን፣ አየሯን እና ባህሯን ሙሉ በሙሉ የምትቆጣጠር ነፃ ሀገር ናት ብሏል። በተጨማሪም " በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " ሕገ መንግሥት መሠረት " የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " ከማንኛውም ብሔራዊ ጥቅሟን ከሚያስጠብቅና ከሚጣጣም አካል ጋር ስምምነት የማድረግ ሥልጣን አላት ብሏል።
- ምክር ቤቱ ፤ " በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " እና በኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግስት መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት አስመልክቶ የሶማሊያ መንግስት የሰጠውን መግለጫ እና ድርጊት በጽኑ አውግዟል። የሶማሊያ መንግስት በመሰል ጉዳዮች ከመሳተፍ እንዲቆጠብ አስጠንቅቋል።
- ምክር ቤቱ ከሶማሊያ የወጡት መግለጫዎች " በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " እና በሶማሊያ መንግስት መካከል ከዚህ ቀደም የተደረጉ ስምምነቶችን የሚጻረር መሆኑን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይወቅልኝ ብሏል።
- ምክር ቤቱ ፤ " በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " እና በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ መንግስታት መካከል የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ለማደናቀፍ ወይም ለመቃወም ለሚሞክር ማንኛውም ግለሰብ ወይም አካል ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
- ምክር ቤቱ የሶማሌላንድ ህዝብ ለተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ላደረገው ደማቅ አቀባበል እና ድጋፍ ያለውን አድናቆት ገልጿል።
- ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክን አርአያነት በመከተል በዓለም ዙሪያ ያሉ መንግስታት " ለሶማሌላንድ ሪፐብሊክ " እውቅና ለመስጠት ድፍረት እና ጥበብ እንዲያሳዩ አሳስቧል። ይህን መሰሉ ዕውቅና ለአህጉራዊ መረጋጋት፣ ለደህንነት እና ለአፍሪካ ቀንድ የዴሞክራሲ መርሆች መሻሻል አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ አጽንኦት ሰጥቷል።
ℹ ሶማሊላንድ ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት እራሷን እንደ አንድ ነፃ ሀገር የምትቆጥር ሲሆን የራሷ ህገመንግስት፣ የመገበያያ ገንዘብ፣ የፀጥታ ኃይል፣ ራሱን የቻለ የፖለቲካ ስርዓት አላት። እስከዛሬ ግን ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘት አልቻለም። ሶማሊያ እንደ አንድ የራሷ ግዛት ነው የምታያት።
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማየት የቴሌግራም ገፃችንን ይመልከቱ!👇
https://t.me/wektawi1mereja