"ለውለታኽ"
ምድር መጻፊያ ብትሆነኝ፤
ሰማይ ቀለሟን ብትለግሰኝ፤
ከዛፎች መሀል ረዥሙን፡ወስጄ ቢሆነኝ ብዕር፤
በውሀ አጥቅሼ ልፅፍ፡ብራና ሆና ምድር፤
ካደረክልኝ ከሆንክልኝ ከሰራክልኝ፡ከውለታኽ ጋር አይነፃፀር፤
ባለውለታዬ የይሁዳ አንበሳ፤
ውለታኽን ልፅፍ ስነሳ፤
የሰማይ ቀለሟ የፈዘዘ፤
ውበት የሌለው የደበዘዘ፤
ምድር አንድ መስመር፤
የማትበቃ ስንኝ ለመደርደር፤
የምታንስ ውለታኽን ለመዘርዘር፤
ባህር ትንሽ ጠብታ ውሀ፤
ፀሀይ የሚነግስበት ሰፊ በረሀ፤
እንኳን ለማጥቀስ የማትበቃ ለመጠጥ ውሀ፤
ውቅያኖስ ትንሽ አጭር፤
የምሻገራት ዘልዬ በእግር፤
ሀይቁ ባዶ ጉድጓድ፤
የተገኘ በመሀል መንገድ፤
ምንጩ ባዶ ደረቅ መሬት፤
የውሀ ጠብታ 'ኳን የማይታይበት፤
ይሆንብኛል ሁሉ ያንስብኛል፤
ቃላት ያጥረኛል ይሳሳብኛል፤
ውለታኽን መግለፅ ያቅተኛል፤
ግን እንዲሁ በደፈናው ተመስገን ልበል፤
ላደረክልኝ ነገር ሌላ ምን ልከፍል፤
ምን ልስጥ እጅ መንሻ፤
ለውለታኽ ይሆን ዘንድ መካሻ፤
ወርቅ አልማዝ ዕጣን ከርቤ
መሸከም አቃተኝ ጥቂቱን ሰብስቤ፤
በውለታኽ ፍቅርህን አኑረህ በልቤ፤
አንተ ግን!አንተ ግን!
ለእኔ ያደረክልኝን የሆንክልኝን የሰራክልኝን፤
ደግሞም ዕለት ዕለት ምታደርግልኝን፤
አትቆጥርብኝ አታይ ከቶ እንደ ውለታ፤
የፍቅርህ መግለጫ አድርገህ ስጦታ፤
ታደርግልኛለህ መልካሙን ጠዋት ቢሆን ማታ፤
መልካም ቸር ነህ ጥሩ አሳቢ ጌታ፤
ለውለታኽ
ለውለታኽ
ለውለታኽ፤
ተመስገን እንጂ ምን ልበልኽ፤
✍ሰውሁን በለው(አቤኒ)
ምድር መጻፊያ ብትሆነኝ፤
ሰማይ ቀለሟን ብትለግሰኝ፤
ከዛፎች መሀል ረዥሙን፡ወስጄ ቢሆነኝ ብዕር፤
በውሀ አጥቅሼ ልፅፍ፡ብራና ሆና ምድር፤
ካደረክልኝ ከሆንክልኝ ከሰራክልኝ፡ከውለታኽ ጋር አይነፃፀር፤
ባለውለታዬ የይሁዳ አንበሳ፤
ውለታኽን ልፅፍ ስነሳ፤
የሰማይ ቀለሟ የፈዘዘ፤
ውበት የሌለው የደበዘዘ፤
ምድር አንድ መስመር፤
የማትበቃ ስንኝ ለመደርደር፤
የምታንስ ውለታኽን ለመዘርዘር፤
ባህር ትንሽ ጠብታ ውሀ፤
ፀሀይ የሚነግስበት ሰፊ በረሀ፤
እንኳን ለማጥቀስ የማትበቃ ለመጠጥ ውሀ፤
ውቅያኖስ ትንሽ አጭር፤
የምሻገራት ዘልዬ በእግር፤
ሀይቁ ባዶ ጉድጓድ፤
የተገኘ በመሀል መንገድ፤
ምንጩ ባዶ ደረቅ መሬት፤
የውሀ ጠብታ 'ኳን የማይታይበት፤
ይሆንብኛል ሁሉ ያንስብኛል፤
ቃላት ያጥረኛል ይሳሳብኛል፤
ውለታኽን መግለፅ ያቅተኛል፤
ግን እንዲሁ በደፈናው ተመስገን ልበል፤
ላደረክልኝ ነገር ሌላ ምን ልከፍል፤
ምን ልስጥ እጅ መንሻ፤
ለውለታኽ ይሆን ዘንድ መካሻ፤
ወርቅ አልማዝ ዕጣን ከርቤ
መሸከም አቃተኝ ጥቂቱን ሰብስቤ፤
በውለታኽ ፍቅርህን አኑረህ በልቤ፤
አንተ ግን!አንተ ግን!
ለእኔ ያደረክልኝን የሆንክልኝን የሰራክልኝን፤
ደግሞም ዕለት ዕለት ምታደርግልኝን፤
አትቆጥርብኝ አታይ ከቶ እንደ ውለታ፤
የፍቅርህ መግለጫ አድርገህ ስጦታ፤
ታደርግልኛለህ መልካሙን ጠዋት ቢሆን ማታ፤
መልካም ቸር ነህ ጥሩ አሳቢ ጌታ፤
ለውለታኽ
ለውለታኽ
ለውለታኽ፤
ተመስገን እንጂ ምን ልበልኽ፤
✍ሰውሁን በለው(አቤኒ)