(አንተን ከኔ ማራቅ)
እኔን ካንተ ማራቅ
አውለብልቦ ሙዳ ስጋ
አንበሳን ማስከተል ከዚህ እስከ እዚያ ጋ
አንተን ከኔ ማራቅ
ከአንበሳው ታግሎ በሳምሶን ትክሻ
ያንን ሙዳ ስጋ
ተፍጨርጭሮ መንጠቅ ከጥርሱ ንክሻ።
እንደዚህ ነው እግዚሐር
እኔን ካንተ ማራቅ ውስን አያለፋም
አንተን ከኔ ማራቅ፣ ኑሮ ነው አይገፋም።
(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)
(ልቀቀኝ!..አለቅም!)
መስመር አለ ከግሬ' ላይ፣ በደል ሰፈር ሀጢያት ስቀኝ
ካለሁበት ድረስ መጥተህ፣ በህይወት ቃል የጠፈርከኝ
ሰንበር አለ ከእጄም ላይ፣ ስፍጨረጨር የሰነኩት
አለቅህም ያልከኝ ለታ'፣ እንድትለቀኝ የታገልኩት።
;
እኔን መከተል ነው፣ ያንተ የለት' ፍዳ
ካንተ ለማምለጥ ነው፣ የኔ ደሞ እዳ
ግና በዚህ ሁሉ
አልልህም ለምን ፤ እንዴት አትለቀኝም
ጥያቄ ነው እንጂ መልስስ አያልቀኝም
ያኔ...ድሮ....ድሮ
ልቤ ካንተ አድሮ
የደከምኩ ለታ
እንዳትለቀኝ ብዬ የፀለይኩት ፀሎት
መልስ ይሆናልና መጥቶ ከፀባኦት።
(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)
እኔን ካንተ ማራቅ
አውለብልቦ ሙዳ ስጋ
አንበሳን ማስከተል ከዚህ እስከ እዚያ ጋ
አንተን ከኔ ማራቅ
ከአንበሳው ታግሎ በሳምሶን ትክሻ
ያንን ሙዳ ስጋ
ተፍጨርጭሮ መንጠቅ ከጥርሱ ንክሻ።
እንደዚህ ነው እግዚሐር
እኔን ካንተ ማራቅ ውስን አያለፋም
አንተን ከኔ ማራቅ፣ ኑሮ ነው አይገፋም።
(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)
(ልቀቀኝ!..አለቅም!)
መስመር አለ ከግሬ' ላይ፣ በደል ሰፈር ሀጢያት ስቀኝ
ካለሁበት ድረስ መጥተህ፣ በህይወት ቃል የጠፈርከኝ
ሰንበር አለ ከእጄም ላይ፣ ስፍጨረጨር የሰነኩት
አለቅህም ያልከኝ ለታ'፣ እንድትለቀኝ የታገልኩት።
;
እኔን መከተል ነው፣ ያንተ የለት' ፍዳ
ካንተ ለማምለጥ ነው፣ የኔ ደሞ እዳ
ግና በዚህ ሁሉ
አልልህም ለምን ፤ እንዴት አትለቀኝም
ጥያቄ ነው እንጂ መልስስ አያልቀኝም
ያኔ...ድሮ....ድሮ
ልቤ ካንተ አድሮ
የደከምኩ ለታ
እንዳትለቀኝ ብዬ የፀለይኩት ፀሎት
መልስ ይሆናልና መጥቶ ከፀባኦት።
(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)