የስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የዘርፉን የ2016 ዓ.ም አፈጻጸም እና የ2017 ዓ.ም እቅድ ገመገመ፡፡
(ነሀሴ 30/2016 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የክፍለከተማ የስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎችን ጨምሮ የወረዳ ስርአተ ትምህርት ትግበራ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ ውይይቱ በ2016 ዓ.ም ስርአተ ትምህርቱ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን የተከናወኑ የድጋፍና ክትትል ተግባራት አፈጸጸም ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በመገምገም በአፈጻጸም የተስተዋሉ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልም ሆነ በሂደት ያጋጠሙ ክፍተቶችን በማረም በ2017ዓ.ም የተሻለ ስራ ለመስራት ታስቦ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
ዳይሬክተሩ በ2016 ዓ.ም በዘርፉ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን የተመለከተ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን የተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍና የመምህር መምሪያ ብቃትን በማረጋገጥ ለትምህርት ቤቶች እንዲሰራጭ መደረጉን ፤በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን፤የመምህራንን እለታዊና አመታዊ እቅድ አዘገጃጀት እና የቤተ ሙከራ አደረጃጀትን በተመለከተ በየትምህርትቤቱ የድጋፍና ክትትል ስራ መሰራቱን እንዲሁም በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርትቤቶች ስርአተ ትምህርቱ በአግባቡ ተግባራዊ መደረጉን በቼክሊስት የማረጋገጥ ስራ መሰራቱን በሪፖርታቸው ከተጠቀሱ ነጥቦች መካከል የተወሰኑት ናቸው፡፡