በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ መምህራንን አጠቃላይ መረጃ ወደ ኢ-ስኩል ሲስተም ለማስገባት በሚያስችል አሰራር ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡
(ጷጉሜ 1/2016 ዓ.ም) በውይይቱ ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ የቢሮውና የክፍለከተማ የአይ ሲቲ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ሲስተሙን ባበለጸገው ትሪያ ትሬዲንግ አማካይነት የመምህራኑን መረጃ እንዴት ወደ ሲስተም ማስገባት እንደሚቻል ገለጻ ተደርጉዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሶፍት ዌርና ሲስተም ልማት ቡድን መሪ ወይዘሮ ሰላም ተስፋዬ የመምህራኑ አጠቃላይ መረጃ ወደ ሲስተም መግባቱ ወጥ የሆነ እና ተአማኒነት ያለው መረጃ ለሚመለከተው አካል ተደራሽ ለማድረግ እንደሚረዳ አስታውቀዋል፡፡
ቡድን መሪዋ አክለውም ቢሮው የኢ-ስኩል ሲስተሙን በመጠቀም በከተማ አስተዳደሩ በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች የ2017 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባን ኦን ላይን ማካሄዱኑ ጠቁመው በቀጣይ የመምህራኑን መረጃ ወደ ሲስተም የማስገባትም ሆነ ኦን ላይን የተመዘገቡ ተማሪዎችን በየክፍሉ የመመደብ ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚከናወን መሆኑን ገልጸዋል፡፡