ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች በሒሳብና እንግሊዘኛ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ እንዲሆኑ በተዘጋጀው ስትራቴጂክ እቅድ ዙሪያ የሚደረገው ውይይት ዛሬም ቀጥሎ ተካሂዷል።
(መስከረም 4/2017ዓ.ም) በዛሬው ውይይት የክፍለ ከተማ ስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎችና አስተባባሪዎችን ጨምሮ የወረዳ ስርአተ ትምህርት ቡድን መሪዎች እና በየደረጃው የሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ የተማሪዎች ውጤት ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ እንደሚገኝ እና ዘንድሮ በ12ኛ ክፍል ውጤትም በአዲስ አበባ ደረጃ 21.4% ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ከማስመዝገባቸው ባሻገር በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተስፋ ሰጪ ውጤት መመዝገቡን አስታውቀዋል።
ምክትል ቢሮ ኃላፊው አያይዘውም የተማሪዎች ውጤት መሻሻል እያሳየ ቢገኝም በሒሳብና እንግሊዘኛ የትምህርት አይነቶች የሚፈለገው ውጤት እየተመዘገበ ባለመሆኑ ቢሮው ተማሪዎች በሁለቱ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ስትራቴጂ ነድፎ ወደ ተግባር መግባቱን ጠቁመው ተማሪዎች በሁለቱ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ መሆን ከቻሉ በሌሎች የትምህርት አይነቶች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በስትራቴጂክ ዕቅዱ የተቀመጡ ዝርዝር ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ ወደተግባር መግባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የቢሮ ኃላፊ ተወካይ ወይዘሮ ታጋይቱ አባቡ በበኩላቸው ስትራቴጂው በ2016 ዓ.ም በየትምህርት አይነቱ የነበረውን የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ውጤት ትንተና መነሻ አድርጎ መዘጋጀቱን ገልጸው