የመኖሪያ ቤት የሌላቸው መምህራን በማህበር ተደራጅተው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ተገመገሙ።
(መስከረም 8/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትን ጨምሮ የመምህራን ማህበር አመራሮች እንዲሁም የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር እና የህብረት ስራ ኮሚሽን የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የቢሮ ኃላፊ ተወካይ ወይዘሮ ታጋይቱ አባቡ በውይይቱ ባስተላለፉት መልዕክት የመኖሪያ ቤት የሌላቸው መምህራን ተደራጅተው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ እየተሰሩ የሚገኙ ተግባራትን በመገምገም በቀጣይ በፍጥነት ወደ ግንባታ በመግባት መምህራኑ የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ሁሉም ባለድርሻ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ በበኩላቸው መምህራን የቤት ባለቤት እንዲሆኑ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ከምዝገባ ጀምሮ እስካሁን እያደረጉ ለሚገኘው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው በቀጣይ ማህበራቱን በማደራጀት ወደ ቀጣዩ ስራ መግባት እንደሚገባ አመላክተዋል።
የመንግስት ሰራተኞች የጋራ ህንጻ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት አደረጃጀት እና አፈጻጸም ደንብ ቁ.129/14 መሰረት መምህራኑን ለማደራጀት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት በህብረት ስራ ኮሚሽን አማካይነት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።