የቢሮ የ2017 ዓ.ም የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም አጠቃላይ የቢሮው ሰራተኞች በተገኙበት ተገመገመ።
(ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 ዓ.ም የስድስት ወራት ስትራቴጂክ እና የሪፎርም ስራዎች እቅድ አፈጻጸም የቢሮ ሰራተኞች በተገኙበት ተገመገመ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪና የዘርፍ ሃላፊ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ ቢሮው የ2017 ዓ.ም እቅዱን በሩብ ዓመቱ መጀመሪያ የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍ ውይይት አድርጎ ወደስራ መገባቱን ገልፀው ፤ ከአጠቃላይ እቅዱ በስትራቴጂክ እቅድ የተቀመጡ ግቦች እና በሪፎርም ስራዎች የተከናወኑ ተግባራት በሥራ ክፍሎችና በየዘርፎቹ ተገምግመው የተግባራት አፈጻጸሙ በከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ሪፖርቱ እንደሚያሳይ አብራርተዋል::
አማካሪዋ አክለውም በ6 ወራት አፈፃፀም የታዩ እጥረቶች ላይ ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር መወያየት መልካም ተግባራት የበለጠ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያግዙ ጠቃሚ ሀሳቦች ለመውሰድ እንደሚረዳ አብራርተው እቅዱን ለማዳበር የሚጠቅሙ ገንቢ ሃሳቦች ማንሳት ከተሳታፊዎች ይጠበቃል ብለዋል::
የቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በበኩላቸው ቢሮው በሪፎርም ድጋፍና ክትትል እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራርን አጠናክሮ እየሰራው ያለው ሥራ ሰፊ መሆኑን ጠቅሰው ይህም ለተሻለ ውጤት ያበረከተውን አስተዋፅኦ በማጤን በልዩ ትኩረት ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል :: በተጨማሪም ለስራው ውጤታማነት ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል ::