አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የሚገኘው ብስራት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በሒሳብ ትምህርት ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀ።
(ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም) ትምህርት ቤቱ ተማሪዎችን በሒሳብ ትምህርት ውጤታማ ለማድረግ በአባከስ ትምህርት ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዛሬው እለት ያስመረቀ ሲሆን ተመራቂ ተማሪዎችም በቀጣይ ሌሎች ተማሪዎችን እንደሚያሰለጥኑ ተገልጿል።
ቢሮው በ2017 ዓ.ም ተማሪዎችን በሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ውጤታማ ለማድረግ ያወረደውን ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ ትምህርት ቤቱ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ቶፊቅ ሙሰማ ጠቁመው ለተማሪዎች የተሰጠው የአባከስ ስልጠናም የዚሁ ስትራቴጂ አካል መሆኑን አስታውቀዋል።
ርዕ ሰ መምህሩ አያይዘውም ትምህርት ቤቱ ምክሰኞን የሒሳብ ቀን በሚል ሰይሞ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው ተማሪዎቹ በትምህርቱ ያመጡትን መሻሻል በምዘና የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል።