Репост из: 乙ε ო£Łムk
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ሞዐ ተዋሕዶ
የሞዐ ተዋሕዶ ጥሪ ለኦርቶዶክሳዊያንና በማንኛውም የእምነት መሥመር ውስጥ ለሚገኙ እና ለሰው ልጅ እኩልነት፣ በነፍስ የመኖር መብት፣ የዜግነት ክብር
የማግኘት እና አምልኮተ እግዚአብሔርን በነፃነት የመፈጸም መብት ለምታምኑ ሁሉ፡-
ጉዳዩ፡- የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትናን ማንነት (Cultural and religious identity) እና የኦርቶዶክስ ክርስቲያንን ዘር ማጥፋትን (Orthodox Christian Genocide ) ስለ መከላከል ፡-
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደ አንድ የሃይማኖት ሥርዓታዊ ተቋም ለማዳከምና ተከታዮቿ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ግልጽ ርእዮተ ዓለማዊ፣ ሥርዓታዊና መዋቅራዊ ጥቃት ከተጀመረበት ከ1966 ዓ.ም. እስከ ዛሬ ድረስ ጥቃቱ ቀጥሏል። በአብዮት፣ በብሔር እኩልነት፣ በመንግሥት ለውጥ እና በጎሣ ግጭት ስም ተሸፍኖ ሲካሄድ ቆይቶ በአሁኑ ጊዜ ወደ ግልጽ ጥቃት ተሸጋግሯል።
በተለም ባለፉት 4 ዓመታት በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በደቡብ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል፣ በአዲስ አባባ ከተማ፣ በአማራ ክልል ልዩ ዞኖች፣ በሶማሌ ክልል፣ በትግራይ ክልል አክሱም ዳንግላት ማርያም ወዘተ ኦርቶዶክሳዊያን በሃይማኖታቸው ምክንያት ከፍተኛ ፍጅትና ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፣ አቢያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣ ክርስቲያኖች ተፈናቅለው ተሰዳዋል። ኦርቶዶክሳዊንን ማግለል፣ መግደልና ሁለገብ ጥቃት ሥር ማዋል በግልጽ ቢካሄድም አጥፊዎች ሲቀጡ፣ የዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ የሚገባው የመንግሥት መዋቅር ግዴታውን ከመወጣት ይልቅ ሲሸፋፍን ማየት የተለመደ ሆኗል።
ኦርቶዶክሳዊያንን በገዛ አገራቸው በዘር በቋንቋ እየከፋፈሉ፣ ድብቅ የዘር ፖለቲካ አጀንዳን ወደ ፖለቲካዊ ርእዮት በማሳደግ፣ በመደራጀት፣ በመዋቀርና አመራር በመሥጠት ኦርቶዶክሳውያንን የማጥፋት ሂደቱን ዝም ሊባል ከማይገባው ደረጃ ላይ ደርሷል።
በመሆኑም የፌዴራል መንግሥት እና የክልል መንግሥታት እና መዋቅሮቻቸው የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት የኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ግፊት ለማደርግ የተባበረ ድምጽ ማሰማት ጊዜ የሚሰጠው አይደለም።
እናም “እዚህ ላይ ይበቃል” ማለት ይገባል የምትሉ ሁላችሁ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች እና በሰው ልጅ እኩልነትና ክብር የምታምኑ የሌላ እምነት ተከታዮች ሁሉ ይህን ፔትሽን በመፈረም ለእውነት፣ ለፍትሕ፣ ለሰብአዊነት እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን። እውነትና ፍትሕ ለዘላለም ያሸንፋሉ!!!
አስቸኳይ የመንግሥት ምላሽ የሚፈልጉ የኦርቶዶክሳዊያን ጥያቄዎች
1. በሕገመንግሥት፣ በፖለቲካ ማኒፌስቶ፣ በመደበኛ ትምህርት፣ በሚዲያና መሰል መንገዶች ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮንና ኦርቶዶክሳዊያንን ለጥቃት የሚያጋልጡ መልዕክቶች በአስቸኳይ በሕግ እንዲታገዱ::
2. ኦርቶዶክሳዊያንን ለይቶ ከሥራ፣ ከመንግሥት ኃላፊነት፣ ከሀብት ማፍራት እድሎች የሚያገል ከቀበሌ እስከ ፌደራል የተዘረጋው ሃይማኖታዊ መንግሥትና መዋቅር በአስቸኳይ እንዲቆምና ሃይማኖታዊ ሳይሆን ሕዝባዊ መሆኑን በተግባር እንዲያረጋግጥ::
3. ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን በቋንቋና በተለያዩ ዘውጎች ለመከፋፈል የሚደረገው ፖለቲካዊ ጥረት በጥናትና በምርምር ስም የሚደረጉ የመከፋፈል ዘመቻዎች እና ተግባራት እንዲታደጉ::
4. በኦርቶዶክሳዊያን ላይ ያነጣጠሩ የአካል፣ የሥነልቦና፣ የኢኮኖሚ፣ የማኀበራዊ፣ የፖለቲካ፣ የማፈናቀል፣ ከአገራዊ ተሳትፎ የመገለልና የፍጅት ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ::
5. እስከ አሁን የተፈጸሙ ጥቃቶች በዝርዝር ተገልጾ አጥፊዎች ለሕግ እንዲቀርቡ እና የተጎዱት እንዲካሱ::
6. በመላው አገሪቱ የተፈናቀሉ ኦርቶዶክሳዊያን ወደ ቀደመ ቦታቸው እንዲመለሱ::
7. “አዲሲቷ ኢትዮጵያ” በሚል ሽፋን ኦርቶዶክሳዊ አሻራዎችን የማጥፋት ፖለቲካዊ ሂደት በአስቸኳይ እንዲገታ እና በግልጽ ይቅርታ ተጠይቆ እርምት እንዲወሰድ
https://chng.it/2zsqkZ9QLN