ህዳር ፅዮን 21 እንኳን አደረሳችሁ
በዚህች ቀን የእስራኤላውያን መመኪያ በእመቤታችን ስም የተሰየመችው ታቦተ ጽዮን ዳጐን በተባለው ጣኦት ላይ ኃይሏን ክብሯን የገለጸችበት ቀን ነው፤ ቤተክርስቲያን ጽዮን ማርያም ስትል ዕለቱን ታከብረዋለች።
አክሱም ጽዮን እንደዛሬው ድርቅ ያለ መሬት አልነበረም ባህር ነበር እንጂ ፤ አብርሃና አጽብሃ ለታቦተ ጽዮን ምን ዓይነት ቤተክርስቲያን ነው የምንሰራላት ቦታውስ የት ጋር ነው የሚሆነው እያሉ ሲጨነቁ ጌታችን ተገለጸላቸው ድንጋይ ላይ ቆሞም አዩት፤ ቤተክርስቲያኗን እዚህ ባህር ላይ ስሩት ስሟንም በእናቴ ስም ሰይሟት፤ ይላቸዋል ጌታ ሆይ ይህ እኮ ባህር ነው ይሉታል ቅዱስ ሚካኤልን ከገነት አፈር ይዞ እንዲመጣ ያደርገዋል ባህሩ ላይ ነሰነሰው ደረቀ የዛሬውንም ቅርጽ ያዘ ይላል ጌታችን የቆመበት የእግሩ ምልክት ዛሬም ድረስ ይታያል ፤ ምንጭ ድርሳነ ጽዮን፤ በድንኳን ቅርጽ የተሰራው ቤተክርስቲያን ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ያሳነጹት ሴቶችም ወንዶችም የሚገቡበት።
በመሐል ታቦተ ጽዮን ያለችበት እቴጌ መነን ያሳነጹት ስመ ጥምቀታ ወለተ ጊዮርጊስ በስሩ የጥንቱ ቤተመቅደስ ፍርስራሽ ይታያል በአራት መአዘን ቅርጽ ያለው አፄ ፋሲለደስ ያሳነጹት ሴቶች የማይገቡበት ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ነው።
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯

ታሪክ

ፅዮን ማርያም ባልንበት ፀሎት ልመናችንን ትስማን
©ልቦና ቲዩብ
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯