✞እግዚአብሔር ኃያል ነው✞
እግዚአብሔር ኃያል ነው የሚሳነው የለም
በዙፋኑ ጸንቶ ይኖራል ዘላለም
ማዕበሉን ከፍሎ ሕዝቡን ያሻግራል
ለሰው የሚሳነው ለርሱ ግን ይቻላል
ማዳንና ጥበብ ኃይል በእጁ ሆኖ
ለሰው የማይቻል ለእሱ ቀሊል ሆኖ
ፈጥኖ ይጎበኛል የምስኪኑን ጓዳ
ፈጽሞ አይዘገይም ጌታ ሲሰናዳ
አዝ= = = = =
አንዱን እየሻረ አንዱን እየሾመ
የተዋረደውን ክብር እየሸለመ
ከኋላ ያለውን ከፊት አሳልፎ
በጎ ቀን ያመጣል ጨለማውን ገፎ
አዝ= = = = =
እንደ ቋጥኝ ቢከብድ የሕይወት ፈተና
ሰውን የሚያጽናና አምላክ አለንና
ደስ ያሰኛል እርሱ መከራን አጥፍቶ
ታግሶ የቆመ ማን አፈረ ከቶ
አዝ= = = = =
የሚያስፈራ ጊዜ ቢመጣ ክፉ ቀን
እናልፋለን እኛ እግዚአብሔርን ይዘን
ወራት ከብዶባችሁ ያጎነበሳችሁ
ታሪክ ሆኖ ያልፋል እግዚአብሔር ሲያያችሁ
መዝሙር
ዲያቆን ፍቃዱ አማረ
"እግዚአብሔርን አመስግኑ መዝሙር መልካም ነውና"
መዝ፻፵፯፥፩
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
እግዚአብሔር ኃያል ነው የሚሳነው የለም
በዙፋኑ ጸንቶ ይኖራል ዘላለም
ማዕበሉን ከፍሎ ሕዝቡን ያሻግራል
ለሰው የሚሳነው ለርሱ ግን ይቻላል
ማዳንና ጥበብ ኃይል በእጁ ሆኖ
ለሰው የማይቻል ለእሱ ቀሊል ሆኖ
ፈጥኖ ይጎበኛል የምስኪኑን ጓዳ
ፈጽሞ አይዘገይም ጌታ ሲሰናዳ
አዝ= = = = =
አንዱን እየሻረ አንዱን እየሾመ
የተዋረደውን ክብር እየሸለመ
ከኋላ ያለውን ከፊት አሳልፎ
በጎ ቀን ያመጣል ጨለማውን ገፎ
አዝ= = = = =
እንደ ቋጥኝ ቢከብድ የሕይወት ፈተና
ሰውን የሚያጽናና አምላክ አለንና
ደስ ያሰኛል እርሱ መከራን አጥፍቶ
ታግሶ የቆመ ማን አፈረ ከቶ
አዝ= = = = =
የሚያስፈራ ጊዜ ቢመጣ ክፉ ቀን
እናልፋለን እኛ እግዚአብሔርን ይዘን
ወራት ከብዶባችሁ ያጎነበሳችሁ
ታሪክ ሆኖ ያልፋል እግዚአብሔር ሲያያችሁ
መዝሙር
ዲያቆን ፍቃዱ አማረ
"እግዚአብሔርን አመስግኑ መዝሙር መልካም ነውና"
መዝ፻፵፯፥፩
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯