🔰ጂብሪል ዓለይሂ ሰላም ነቢዩ ሰላሏሁ ዓለይሂ ወሰለምን እኔ ጂብሪል ነኝ ብሏቸዋል??🔰
ነቢያችን ሰላሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ለመጀመሪያ ግዜ በሂራ ዋሻ በመልአኩ አማካኝነት ወህይ ሲመጣላቸው በጣም ፈርተው ደንግጠው ስለነበር ወደ ወረቃህ ሄደው የተከሰተውን ክስተት ሲነግሯቸው ያ ወዳንተ የመጣው ወደ ሙሳ ዓለይሂ ሰላም ይመጣ የነበረው መልአኩ ጂብሪል ነው ብለው ነገሯቸው።(ሀዲሱ ረጅም ስለሆነ ሙሉ ሀዲሱን📚 ቡኻሪይ ሀዲስ 03 ላይ ያገኙታል።
(ለምን እንደፈሩ፣እንደደነገጡ በቀጣይ ርዕሳችን ላይ እናያለን ኢንሻአላህ)
ሙስሊም ያልሆኑ ግለሰቦች ይህንን ሀዲስ በመያዝ ወደ ነቢያችን ሰላሏሁ ዓለይሂ ወሰለም የመጣው አካል መልአኩ ጂብሪል መሆኑን ከአንድ ግለሰብ በመያዝ እንዴት ሊቀበሉ ቻሉ?? መልአኩ እራሱ እኔ ጂብሪል ነኝ ያለበት ማስረጃ ስጡን ይላሉ።
ለዚህ ጥያቄ ብዙ ማስረጃ መጥቀስ ይቻላል። ለምሳሌ
➸ ከቁርአን➸➸👇
قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
(አል-በቀራህ - 97)
ለጂብሪል (ለገብርኤል) ጠላት የኾነ ሰው (በቁጭት ይሙት) በላቸው፡፡ እርሱ (ቁርኣኑን) ከበፊቱ ለነበሩት (መጻሕፍት) አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና፡፡
ከዚህ አንቀፅ ምንረዳው ቁርአንን ወደ ነቢያችን ሰላሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ያወርድ የነበረው መልአኩ ጂብሪል እንደሆነ ስለተገለፀ ያ ወደ ነቢያችን መጥቶ አንብብ እያለ ቁርአንን ያስተማራቸው መልአክ ጂብሪል ነው።
➸➸ ከሀዲስ➸➸
ሀዲስ ➊👇
عن سمرة ابن جندب قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم “ رَأَيْتُ اللَّيْلَةَ رَجُلَيْنِ أَتَيَانِي قَالاَ الَّذِي يُوقِدُ النَّارَ مَالِكٌ خَازِنُ النَّارِ، وَأَنَا جِبْرِيلُ، وَهَذَا مِيكَائِيلُ ”.
ሠሙራህ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “በሌሊት ላይ ሁለት ሰዎች ወደ እኔ ሲመጡ አየሁኝ፥ ከዚያም እንዲህ አሉኝ፦ “ያ እሳት የሚያይዝ “ማሊክ” ሲሆን የእሳት ዘበኛ ነው፥ “#እኔ_ጂብሪል_ነኝ”*። ይህ ሚካኢል ነው”።
📚 ሶሂህ አልቡኻሪይ ሀዲስ 3236
ሀዲስ ⓶ ስለ ኢስራእና ሚዕራጅ በተጠቀሰበት ረጅሙ ሀዲስ ላይ እንዲህ የሚል እናገኛለን
" فاستفتح جبريلُ ، فقيل : من أنت ؟ قال : جبريلُ ، قيل : ومَن معك ؟ قال : محمدٌ
(أخرجه البخاري 3887)
ትርጉሙ:- "ጂብሪል(ዐለይሂ ሰላም) ወደ ሰማይ ሲወስዳቸው መላእክትን ሰማይ ማስከፈትን ጠየቀ።
በሰማዩ ያሉ መላእክትም አንተ ማን ነህ?? ብለው ጠየቁት
እሱም:- እኔ ጂብሪል ነኝ
ካንተጋ ያለውስ ማን ነው?? ብለው ጠየቁት
እሱም:- ሙሀመድ ነው ብሎ መለሰላቸው
📚 ቡኻሪይ ሀዲስ 3887 ላይ ዘግቦታል
በተጨማሪም በታሪኹ ጠበሪይ ቅጽ 2 ገፅ 301 ላይ ያ መልአኩ ለመጀመሪያ ግዜ ከመጣ በኃላ ተለይተዉት ወደነ ወረቃህ ሄደው ከነበረ በኃላ መንገድ ላይ እየተጓዙ ያ ሂራ ዋሻ ላይ መጥቶ የነበረ መልአክ "ሙሐመድ ሆይ አንተ የአላህ መልእክተኛ ነኝ እኔ ጂብሪል ነኝ" ብሎ ሁለት ግዜ ጠራኝ ብለው ተናግረዋል።
📚 ታሪኹ ጠበሪይ ቅጽ 2: ገፅ 301
ከነዚህ ሀዲሶች እንደምንረዳው ጂብሪል በግልፅ እኔ ጂብሪል ነኝ ብሎ እንደነገራቸው እንረዳለን።
ከላይ የጠቀሰኳቸውን ሀዲሶች ከኪታብ በማስረጃ ከፈለጉ ይህንን ይጫኑ👇👇
https://t.me/iwnetlehullu1/403?single
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
➣➣አልሃምዱሊላህ ረቢል ዐለሚን➤➤