የአክሱም ወረዳ ፍርድ ቤት ሒጃብ መልበስ የሚከለክለው መመሪያ ላይ ዕገዳ ጥሏል‼
====================
(በሒጃብ ምክንያት ተማሪዎችን ያገዱ ትምህርት ቤቶች ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ አዟል!)
||
✍ የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት በአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሒጃብ ለብሰው እንዳይማሩ አስተዳደራዊ እግድ ባደረጉ 5 ትምህርት ቤቶች ላይ ክስ መመስረቱ ይታወቃል።
ጉዳዩ በዛሬው ዕለት የአክሱም ከተማ ወረዳ ፍርድቤት ላይ ቀርቦ ውሳኔ ተስጥቶበታል። ፍርድ ቤቱ አስተዳደራዊ እግድ ባደረጉ ትምህርት ቤቶች ላይ እግድ ጥሏል።
ጉዳዩ በተማሪዎቹ ላይ የማይቀለበስ የሰብአዊ መብት ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ተማሪዎቹ ሒጃባቸውን ለብሰው ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የሚል ውሳኔ አስተላልፏል።
በሒጃብ ምክንያት ተማሪዎችን ያገዱ ትምህርትቤቶቹ ለጥር 16/2017 ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ ትእዛዝ ተሰጥቷል።
በተያያዘ ዜና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰጠው ማሳሰቢያ ፥ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ዛሬ ጥር 6/2017 ዓ.ል ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቋል።
የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል አገር አገር አቀፍ ፈተና ለማሳተፍ የሚያስችላቸው ፎርም ሳይሞሉ የተሰጠው የምዝገበ ቀነ ገደብ ዛሬ አልቋል።
© ሀሩን ሚዲያ