በወንድም ሳሚ የተፃፈ
ለመርከዝ ኢብኑ መስዑድ እና ለነሲሓ ቲቪ አመራሮችና አባሎቻቸው
ምላሹንም የምፈልገው ከጠቀስኳቸው አካላት ነው።
በአደባባይ ያመጣሁትም በአደባባይ የሰሩት ነገር ስለሆነ እና ለዳዕዋው በመቆርቆርም ጭምር ነው።
በተረጋጋ መንፈስ ምላሽ ቢሰጥ መልካም ነው። ከነፍሲያ ወጥተን በመሃል ለታዩ ችግሮች ምላሽ አለመሰጣጠት እንዲሁም በእውቀት እና በስርዓት ምላሽ አለመሰጣጠት በመሃል ያለውን ልዩነት ከማጥበብ ይልቅ ልዩነቱን ወደ ማስፋት ያመራል እና በተረጋጋ መንፈስ መተራረሙ መልካም ነው።
ከነቢያችን ﷺ ወዲህ ከስሕተት የተጠበቀ ሼይኽ፣ ኡስታዝ፣ ጣሊበል-ዒልም እንደሌለ መዘንጋት የለብንም። "ሼይኼ ለምን ተነካ?" ሳይሆን "ምን አድርጎ ነው?" ብለን ማጤን አለብን። ስሕተት ካለ ማረም ከሌለ ደግሞ መመከት።
የመጨረሻው ቅድመ-ጥያቄዬ "ለምን ቀርባችሁ አልተመካከራችሁም?" እንዳይባል ቀርበን ሂደን አውርተናል ግን ከመሻሻል ይልቅ እየባሰ የመጣ ችግር ሁኗል።
-------ጥያቄዬ-------
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በ"መስለሓ" ስም ድሮ ስትኮንኗቸው ከነበሩ ሰዎች ጋር መቀራረብን መመስራታችሁ አደባባይ የወጣ እውነታ ነው፤ በተለይም ከዳዕዋ ቲቪ አባላት (እነ ሼይኽ ሙሓመድ ሓሚዲን እና ባልደረቦቻቸው) ጋር።
አሁን ደግሞ ከአፍሪካ ቲቪ አባላት ጋር ለመስራት እየተቀራረባችሁ እንደሆነም እያየን ነው። "መጥተውባችሁ ነው" እንዳይባል ሄዳችሁባቸው ነው። ማስረጃውንም ኮሜንት ላይ አስፍሬዋለሁ።
ጥያቄዬ:
1- ድሮ ለምን እና በምን ጉዳይ ኮነናችኋቸው?
2- አሁን ላይ ከነሱ ጋር መስራት የጀመራችሁት ድሮ ከነበረባቸው ችግር ተመልሰው ነው ወይስ ድሮ ስትኮንኗቸው የነበረው እናንተው ተሳስታችሁ ነው?
3- ከነበረባቸው ችግሮች ተመልሰው ከሆነ የተመለሱበትን መግለጫ በድምፅም ሆነ በፅሑፍ ያቅርቡ ወይም አቅርቡላቸው።
4- "መጀመሪያም ችግር አልነበረባቸውም" ካላችሁ ለስከዛሬው እናንተው መግለጫ አውጡና ጥፋታችሁን አምናችሁ እኛም እነዚህን መሻኢኾች እንጠቀምባቸው፣ አብረናቸውም እንስራ።
አላህ በሚያውቀው አንድነትን አንጠላም፣ አንድነትን የሚጠላ ልቡ ላይ ችግር ያለበት ሰው ነው፣ አሊያም ስለ አንድነት ያለው ግንዛቤ የተዛባ ነው።
👉 አንድነት ሲባል ግን በዓቂዳም በመንሃጅም አንድ ሲኮን ነው፣ ይሄን ነው ያስተማራችሁን። የሰለፎቻችንን ዓቂዳ ይዞ መንሃጁ ከሰለፎቻችን መንሃጅ ውጪ ከሆነ የአካሄድ ችግር አለበት።
እነዚህ እና መሰል ጥያቄዎች የኔ ብቻ ሳይሆኑ ለናንተ የሚወግኑ ወንድም እህቶች ጥያቄዎች ናቸው።
መልሳችሁን 1- 2- 3- 4- ብላችሁ መልሱልን።
እጠብቃለሁ
Sami Abu Meryem