🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ ማኔ
ክፍል 1️⃣2️⃣
በኔ ምክንያት ስትሰደብ ስትገፋ የሰውን አይን ሲገርፋት አንገቷን ደፍታ ስላሳለፈች ነው።
ኮንፊደንስ ያለው ጠንካራ ወይድ አድርጋ ስላሳደገችኝ ነው ገባሽ እማዬን መጥላት ማለት እራሴን መጥላት ነው ።
ደሞ ይቅርታ አድርጊልኝና እህትሽንኮ እኔ አፍቅሪኝ አላልኳትም እኔ እንደሌሎች ወንዶች አፈቅርሻለሁ እወድሻለሁ ብዬ አልሸወድኳትም በህይወቷ በሴትነቷ አልተጫወትኩም እኔን እንደጠላት ማየትሽ እራሱ ተገቢ አደለም።በእርግጥ ሴት ልጅ ላይ እጅ ማንሳት ወንድነት አደለም አጥፍቻለሁ እኔም ካለፈ ቡሀላ ፀፅቶኝ ነበር ግን እኔ እንደሞተች እንደዚህ አይነት አደጋ የደረሰባት ሴት እሷ እንደሆነች አላወኩም አንድ ተማሪ ተገጭታ ሞተች የሚል ወሬ ብቻ ነው የሰማሁት አልኳት።
ዝም አለች በእጇ ሂድ የሚል ምልክት ሰጠችኝ ከዛ በላይ እዛ ቦታ መቆየቴ አስፈላጊነቱ አልታየኝም ስትረጋጋ ባወራት እንደሚሻል አስቤ ተነስቼ ሄድኩኝ ጓደኞቿ ሁላ ገላመጡኝ።
ልክ ከዛ ቤት ለቅቄ እንደወጣሁ ስልኬን ከኪሴ አወጣሁት መጀመሪያ የተደወለልኝ ስልክ 15 ሚስኮል ተደርጓል።
እማዬም ከአስር ጊዜ በላይ ደውላለች ልቤ መምታት ጀመረ እየተንቀጠቀጥኩ መልሼ ደወልኩ አይነሳም የማላቀው ስልክ ላይም ደጋግሜ ደወልኩ አይነሳም እንዴት ብዬ መኪና ውስጥ እንደገባሁ አላቅም ግን ወደሰፈር መሄድ ጀመርኩ መኪና ውስጥ ከገባሁባት ሰአት አንስቶ ያለማቋረጥ እየደወልኩ ነበር ከየትኛውም ስልክ ግን ምላሽ አላገኘሁም መኪና ውስጥ የተቀመጥኩበት ወንበር በረዶ ሰራብኝ።
መኪናው እየተነዳ ያለ አልመስልህ አለኝ ሹፌሩን ተቀብዬ ባበረኩት ብዬ ተመኘሁ።
ሰፈር እንደረስኩ እየተሯሯጥኩ ነው ወደውስጥ የገባሁት ልክ ከሩቅ ቤታችን ሳይ ግርግር የሚሉ ሰዎችን ስመለከት አንዳች የተስፋ መቁረጥ ስሜት ተሰማኝ በደመነፍስ ደረስኩ ግቢው በለቅሶ እየተደበላለቀ ነው በር ላይ የቆሙት ሰዎች አልታይ አሉኝ።
እንዴት አልፊያቸው እንደገባሁ አላቅም ብቻ ስደርስ እናቴ ሞታ ነበር።
ለመሳቅና እናቴንም ቀልዱን ትታ እንድትስቅልኝ አውቃ እንደሆነ እያተናገርኩ ለመቀስቀስ ሞከርኩ እናቴ የምሯን ነው የሞተችው።
ያቺ ውጭ ምግብ ከበላሁ የተጎዳሁ ሚመስላት እናቴ
ያቺ ማታ ትንሽ ሲመሽብኝ ከግቢ ውጭ እየተጎራደደች ተጨንቃ መንገድ መንገዱን እያየች ምትጠብቀኝ ደርባባዋ ሴት ያቺ ዘመድ ያልወለድሽውን ልጅ ለማሳደግ ምን አሰቃየሽ አንቺስ እንደናቱ አትጥይውም ብለው ሲናገሯት እኔን የጎዱባት መስሏት ከሙሉ ዘመዶቿ የተቆራረጠችው እናቴ ያቺ ሳትበላ ሳትለብስ ሙሉ ህይወቷን ክርትት ስትል የኖረችልኝ እናቴ ሞታለች።
በሰአቱ የሰው ልጅ በህይወት ኖሮ እንደሚሞት ተረድቻለሁ እኔ ቆሚያለሁም ሞቻለሁም ።
የእናቴን አስክሬን ለማስለቀቅ ሲሞክሩ አቅፊያት ከሷጋ መሆን እንደምፈልግና ከአጠገቤ እንዳይወስዷት ከሁሉምጋ መጣላት ጀመርኩ።
የእናቴን ፊት ገልጬ ተመለከትኩት አሳዘነችኝ ፊቷ እንደከፋው ነው
እንባዬ ደረቀ ከፊት ለፊቴ ልእልት ቆማ ስትንሰቀሰቅ አየኋት እንደእብድ እየጎተትኩ መኝታ ቤት አስገባኋትና እናቴ ምን እንደሆነች ጠየኳት።
ለማውራት እየተናነቃት እቴቴ ከታመመች ቆይታለች በየተኛውም ሰአት እንዳትጨነቂ ንዴትና ጭንቀት የሞትሽን ቀን ያፋጥኑታል ተብላ በሀኪም ተነግሯት ነበር ቀን ከተፈጠረው ነገር ቡሀላ እቴቴ ደና አልነበረችም የሆነ ሰአት በጣም ሲብስባት ለመረጋጋት ያንተን ድምፅ መስማት ፈልጋ ደጋግሜ ስደውል አታነሳም እሷም እየደወለችልህ አታነሳም በዛ ሰአት ልጄ በንዴት የሆነ ነገር ሆኖብኝ ነው ብላ እንደ እብድ አደረጋት ተነስታ ከቤት ለመውጣ ስትሞክር ወደቀች ግን ደግማ አልተነሳችም አለችኝ።
በቃ የዚህ ሁሉ መንስኤ ፋኖስ ናት እሷ ናት የናቴ ገዳይ እያወራሁ ተቻኩዬ ኪችን ገባሁ ስለት ያለውን ቢላ አንስቼ ከጀርባዬ ሱሪየ ውስጥ ከተትኩት የኔ እናት ሞታ እሷ በህይወት አትኖርም እገላታለሁ ....
ከግቢ ማንም ሳያየኝ በፍጥነት ወጣሁ ወደፋኖስጋ አመራሁ ምን ምኗ ላይ እንደምወጋት ቀጭንቅላቴ እየተመላለሰ ነው እዛ የተደረስኩት ቀኑ እየጨላለመ ነው የቤቷ ፊት ለፊት የደረስኩት ደወለኩላት አታነሳም ያለማቋረጥ ደወልኩ አነሳችው ከቤትሽ ፊት ለፊት ቆሚያለሁ በእህትሽ ይዤሻለሁ አንዴ ውጭ አልኳት።
የሚቆራረጠውን ድምፄን እንዳታውቅብኝና እንዳትጠራጠር ለማድረግ የቻልኩትን እየሞከርኩ ስልኩን ዘጋሁት መንጎራደድ ጀመርኩ ቀና ብዬ ወደሰማይ ተመለከትኩና አንተኮ አታደርገውም አደል አሁን ቤት ስደርስ እናቴን አስቀምጠህ ትጠብቀኛለህ እንዴ.... አታሳዝንህም ምን ቻቃለች እሷ የኔ እናትኮ ምስኪን ናት እኔ ብሆን ጨክኜ አልገላትም አንተም አታደርገውም ከፈጣሪጋ ያለኝን ንግግር ፋኖስ አቋረጠችኝ ከቤቷ ፎጣውን እላይዋ ላይ ጣል እንዳደረገች ወጣች ።
ከኋላ የከተትኩት ቢላ አወጣሁና እጄን ወደኋላ እንዳደረኩ ያዝኩት ልክ አጠገቤ ስትደርስ.....
ይቀጥላል...
🔻ክፍል1️⃣3️⃣ ከ 1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔